Homeዜናበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባልተለመደ መልኩ ለዘመን መለወጫ በዓል ብር አምጡ እየተባሉ መሆናቸውን...

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባልተለመደ መልኩ ለዘመን መለወጫ በዓል ብር አምጡ እየተባሉ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች ገለፁ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
07/04/2017

የመንግስት የጸጥታ አካላት ለምን ብለው የሚጠይቁ ሹፌሮችን ለመደብደብ ይጋበዛሉ፣ መሳሪያ ይዘው ያስፈራራሉ ሲሉ ተናግረዋል።

የመንግስት የጸጥታ አካላት መንገድ ላይ ገመድ በመዘርጋት ኬላ አዘጋጅተው ከአንድ አሽከርካሪ እስከ 2 ሺህ ብር ድረስ እያስከፈሉ መሆናቸውን አሽከርካሪዎቹ ቅሬታ አቅርበዋል።

አሽከርካሪዎቹ በቅሬታቸው” ለዘመን መለወጫ በዓል እንዴት ገንዘብ አዋጡ እንባላለን ?” ሲሉ በብሶት ገልፀዋል።

አንድ አሽከርካሪ “ከድርጅት የሙዝ ምርት ጭኜ ስወጣ መሽቶ ስለነበር አሸከር ከተማ የደረስኩት 10:00 ነው፣ በቦታው ላይ የነበሩ የታጠቁ ሰዎች መንገድ ላይ ገመድ ዘርግተው የዘመን መለወጫ 1 ሺህ እና 2 ሺህ ክፈል አሉኝ” ሲል የገጠመውን ተናግሯል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

“አልከፍልም የጫንኩት ወደ ሶማሌ ላንድ እና ጅቡቲ ኤክስፖርት የሚደረግ በካርቶን የታሸገ ሙዝ ነው፣ ከድርጅቱ የተሰጠኝ ደብዳቤ አለ፣ በግሌ የማደርገው ነገር የለም፣ ምርቱን በአስቸኳይ ማድረስ አለብኝ ልቀቁኝ ብላቸውም አንሰማም በማለት አስቁመው አሳድረውኛል” ብሏል።

“በሰዓቱ ምርቱን ወደ አዲስ አበባ እንዳደርስ ለላከኝ ድርጅት ማሳወቅ አልቻልኩም፣ ምክንያቱም ማሳወቅ የምችለው ከ2 ስአት በኋላ ነው፣ ከጠዋቱ 2:00 ስአት አካባቢ ሲሆን ሙዙ ከሚበላሽ በማለት ከራሴ ከኪሴ 1 ሺህ ብር ከፍዬ ጉዞየን ቀጥያለሁ” በማለት አብራርቷል።

አሽከርካሪው አክሎም “በስፍራው የነበሩ የመንግስት አካላቶች ሹፌሮችን ለመደብደብ ይጋበዛሉ፣ መሳሪያ ይዘው ነው የሚያስፈራሩት፣ የመንግስት የጸጥታ አካላቶች ናቸው፣ መንገድ ላይ ገመድ ወጥረው ነው እንደዚህ የሚያደርኑት” ያለ ሲሆን “ኬላ ብለው ገመድ በዘረጉበት ቦታ ላይ በርካታ መኪኖች ቆመዋል፣ ከርቀት ቦታ የመጣ አሽከርካሪ አማራጭ ስለሌለው እየከፈለ ነው የሚሔደው፣ በዚያው አካባቢ ያሉት ደግሞ ቆመው ይከራከራሉ” ሲል ተናግሯል።

“በሁሉም ቦታ ትብብር እንዲደረግልን ድርጅቱ የጻፈውን ደብዳቤ እንኳ ማየት አይፈልጉም፣ በየትኛውም ቦታ እስካሁን ኬላ ላይ አስቁመውኝ ተንገላትቼ አላውቅም፣ ኬላዎች እንዲነሱ ከተደረገ በኋላ ግን ዛሬ አንገላቱኝ፣ ለማን አቤት እንበል?” ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ኬላዎች እንዲነሱ እያደረገ ባለበት ሁኔታ ለምንድነው የምንከፍለው ብለን ስንጠይቃቸው “ለዘመን መለወጫ መዋጮ አምጡ ነው” የሚል ተገቢ ያልሆነ መልስ ሰጥተውናል ብለዋል።

አሽከርካሪዎቹ “እኛ መንገደኛ ሹፌሮች ነን፣ መንገዱ የፌደራል ነው፣ የአካባቢው ነዋሪ አይደለንም፣ በዓሉ የሚመለከተው አካል ለምን አያዋጣም? የቀን አበላችን 500 ብር ነው፣ እኛ በአንድ ኬላ 1000 ብር ከፍለን ምን ልንበላ ነው? ስንላቸውም ‘ምን አገባን’ ከማለት ውጪ ምላሽ አይሰጡንም” ሲሉ የደረሰባቸውን አስረድተዋል።

መንግስት በየቦታው ያሉ ኬላዎች እንዲነሱ በመወሰኑ አመስግነን ሳንጨርስ በድንገት በስውር የሚዘረጉ ገመዶች አሉ፣ የቅጣት ተመን የሌላቸው፣ ደስ እንዳላቸው የሚያስከፍሉ፣ ለልማት እንኳ ቢሆን ችግር የለውም፣ የዘመን መለወጫ አዋጡ ማለት ግን ከባድ ነው፣ የአካባቢው ባለስልጣናት በፍጥነት እልባት ሊያበጁለት ይገባል ” ሲሉ ጠይቀዋል።

የማሌ ወረዳ በሰጠው ምላሽ በየአመቱ ለሚከበረው የዶኦሞ የዘመን መለወጫ በዓል ዝግጅት ክፍያ ማስጀመሩን አስታውቋል።

- Advertisement -

የማሌ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኮፒያን ትንብት በቀረበው አቤቱታ ላይ በሰጡት ምላሽ ” አሁን ላይ በማሌ ማህበረሰብ የሚከበረውን በዓል በማስመልከት የባለሁለት እግር አሽከርካሪዎች ከ300 እስከ 500 ብር እና መኪኖች ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ብር እንዲያዋጡ እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ለዘመን መለወጫ በዓል ከአሽከርካሪ መዋጮ መጠየቁን በተመለከተ ኃላፊው በሰጡት ማብራሪያ “ይህን የወሰነው የወረዳው አስተዳደር ነው፣ ህጋዊ በሆነ መንገድ ደረሰኝ እየተቆረጠ ነው መዋጮ የሚከፍሉት፣ ከዚህ በፊትም ለ11 አመታት መዋጮ ስናስከፍል ነበር፣ የዘንድሮውም ለ12ኛ ጊዜ ነው፣ የሚከፍሉት ትንሽ ብር ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

አክለውም ” ይህ መዋጮ አዲስ ነገር አይደለም፣ ለዲሽታ ጊና በዓልም በጅንካ ከተማ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ሲዋጣ ነበር፣ ሁሉም አሽከርካሪ ይከፍላል፣ ይህን መንግስትም የወረዳውም አስተዳደር የሚያውቀው ጉዳይ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የሀገር አቋራጭ አሽከርካሪዎችን እያንገላቱ የሚገኙ ህገወጥ ኬላዎች በአሽከርካሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ሲፈጥሩ ቆይተዋል።

የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች አሽከርካሪዎችን እያስመረሩ ነው ያሏቸው ኬላዎች እንድነሱ መወሰናቸው ይታወቃል።

……………………………

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News