Homeዜናኢሰመጉ በመንግስትና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳሰበ

ኢሰመጉ በመንግስትና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳሰበ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
08/04/2017

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)፣ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ፣ ግጮቶች በውይይት እንዲፈቱ እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

ኢሰመጉ “ሰብዓዊ መብቶች፡ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን መሰረቶች” በሚል መሪ ቃል ባሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 1 ቀን ለ77ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረውን የሰብዓዊ መብቶች ቀን አስመልክቶ ትላንት ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የሰብዓዊ መብቶች ቀን በሚከበርበት በእዚህ ወቅት በአገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት እየተፈጸሙ ይገኛሉ ብሏል፡፡

በአገሪቱ የተወሰኑ ክፍሎች ባለው ግጭት በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካቶች ለሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለእገታ፣ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ሌሎችም ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋልጠዋል ሲል ገልጿል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመግለጫው፣ ምንም እንኳን የሰሜኑ የኢትዮጵያ ግጭት በፕሪቶሪያ ስምምነት ቢቆምም፤ ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቀያቸው ከመመለስ፣ ትጥቅ ከማስፈታት (DDR) እና ከሽግግር ፍትህ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ሙሉ በሙሉ ባለመተግበራቸው ዜጎች አሁንም ለችግር መጋለጣቸውን አብራርቷል።

መንግስት የዜጎችን መብት የማክበርና የማስከበር ሕገ-መንግስታዊ ግዴታውን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምክንያት በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የሚፈለገው መሻሻል ሊታይ እንዳልቻለ የጠቆመው ድርጅቱ፣ በዚህም በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ በተወሰኑ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለው ግጭት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተባብሰው ቀጥለዋል ሲል ጠቁሟል።

ድርጅቱ ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ እንዲሆን መንግስትም ሆነ በግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ታጥቂ ኃይሎች ለግጭት መነሻ የሆኑ ልዩነቶችን የኃይል አማራጭን በመተው በጠረጴዛ ዙሪያ በሰላማዊ ንግግር እንዲፈቱ፤ ለተጀመሩ የሰላም ንግግሮችም ቅድሚያ እና ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቋል።

መንግስት በፖለቲካ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ክስ በማቋረጥ እንዲሁም ለተፈረደባቸው ታራሚዎች ይቅርታ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲያሰፋ እና ግጭት ባለባቸውና ረሃብ በተከሰተባቸው አካባቢዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ እንዲደርስ እንዲሁም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በተጨማሪም በንጹሃን ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡና ኢትዮጵያ እስካሁን ያልፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች እንድታጸድቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በዚሁ መግለጫው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበራትና መገናኛ ብዙሃን ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመጠየቅ በሰላማዊ ሀገር ግንባታ ሂደቱ ላይ የበኩላችውን ሃላፊነት እንዲወጡ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች የሚታወቅ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በመንግሥት ተፅዕኖ ስራውን ለማቆም ተገዶ ከቆየ በኋላ ወደስራ ተመልሷል።

……………………………………..

- Advertisement -

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News