Homeዜናከቀናት በፊት የንብረት ውድመት የተከሰተባት የሺንሺቾ ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት

ከቀናት በፊት የንብረት ውድመት የተከሰተባት የሺንሺቾ ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
09/04/2018

በዛሬው እለት ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ምክርቤት የዞን እና የከተማዋን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው ማንሳቱ ተገልጿል።

በከምባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ በሰርግ ድንኳን መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ከተከሰተው የመኪና መቃጠል አደጋ ጋር ተያይዞ፣ የከተማዋ ከንቲባና የዞኑ የመንግስት ዋና አስተባባሪ ከስልጣናቸው ተነስተዋል ተብሏል።

የሺንሺቾ ከተማ ጊዜያዊ ሽግግር ምክር ቤት ባካሄደው 10ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፣ አቶ መለሰ ገቡሬን የሺንሺቾ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አድርጎ በመሾም በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

አዲሱ ከንቲባ ለምክር ቤቱ የቀረቡት በከምባታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ በአቶ በፍቅር ታምራት አቅራቢነት ነው ተብሏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አቶ መለሰ ገቡሬ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ በመፈጸም ስራቸውን በይፋ መጀመራቸውን ቦርከና ከዞኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአስተዳደር ለውጡ የተካሄደው በቅርቡ በከተማዋ በሰርግ ድንኳን መንገድ በመዘጋቱ ሳቢያ ለደረሰው ከፍተኛ የንብረት ውድመት፣ የመኪና መቃጠል እና ሱቆች መውደም ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

የሺንሺቾ ከተማ ጊዜያዊ ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ እያካሄደ ይገኛል።

ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ በከምባታ ዞን፣ በሽንሺቾ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ ዋና አስፓልት መንገድ ለሰርግ መልስ ፕሮግራም  እስከ ምሽት በድንኳን ተዘግቶ ውሏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በዚህም ምክንያት በርካቶች መጉላላታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። መንገዱ በመሄጃውም በመምጫውም በኩል ተዘግቶ ስለነበር ተሽከርካሪዎች ማለፍ ሳይችሉ እንደቀሩና እንደተጉላሉ አብራርተዋል።

በዚህ ወቅት አማራጭ መንገድ ተጠቅሞ ውስጥ ለውስጥ ሲሄድ የነበረ ጭድ የጫነ አይሱዙ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪክ ገመድ በመንካቱ የቃጠሎ አደጋ ተከስቷል።

ከዚህ ባለፈ የመንገዱን መዘጋት ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ተኩስም እንደነበር ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

መንገዱ በርካታ ተሽከርካሪዎች የሚተላለፉበት በመሆኑና፣ አምቡላንስም የሚያልፍበት እንደመሆኑ መጠን በመዘጋቱ የሚፈጠረው ችግር ሊታሰብበት ይገባ ነበር ብለዋል።

- Advertisement -

እሁድ ታህሳስ 5 ለሚደረግ የመልስ ፕሮግራም ተብሎ ዋናዉ አስፓልት በድንኳን ከቅዳሜ ለሊት ጀምሮ መዘጋጀቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ተለዋጭ ተብሎ በተዘጋጀዉ መንገድ እየሄደ የነበረው እና ጭድ የጫነው መኪና በተፈጠረው እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ተብሏል።

የመኪናዉ ሹፌር መኪናዉን ነፃ ወደ ሆነ ቦታ በመንዳት ዘሎ በመውጣት ራሱን ማዳኑ እና በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት አለመድረሱም ተገልጿል።

……………………………………………………………

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News