Homeዜናበሰላሌ ህዝብ ላይ የጥላቻ ንግግር ያሰማው ፓስተር በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ ተጀመረ

በሰላሌ ህዝብ ላይ የጥላቻ ንግግር ያሰማው ፓስተር በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ ተጀመረ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
15/04/2018

ነብይ ሄኖክ ግርማ “ሰላሌ የጠንቋይ እና የመተተኛ ሀገር ነው” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ቪዲዮ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።

የማህበረሰብ አንቂዎች የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ቲክቶከሮች እንዲታረሙ እንደፈፀማችሁት መልካም ስራ በእምነት ተቋማት ስር ተቀምጠው በማህበረሰብ ላይ ጥላቻን የሚዘሩ የትልቅ ትንንሾች ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት በፓስተር ሄኖክ ግርማ ሰላሌ ላይ የሕግ ምርመራ ተጀምሯል ተብሏል።

የሰሜን ሸዋ ኮሙኒኬሽን ባወጣው መግለጫ የሰሜን ሸዋ ዞን ዓቃቤ ሕግ መምሪያ፣ የሰላሌን ሕዝብ ክብር የሚነኩ ንግግሮችን አድርገዋል የተባሉትን ፓስተር ሄኖክ ግርማን ለሕግ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የፊቼ ከተማ ዓቃቤ ሕግ እና የከተማዋ ፖሊስ በቅንጅት በጀመሩት ምርመራ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ወይዘሮ ባዩሽ ዓለማየሁ ከበደ የተባሉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዓቃቤ ሕግ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምጦ ጣና በሰጡት መግለጫ ብሔርን መስደብ፣ ስም ማጠልሸትና በሕዝብ መካከል ሁከት የሚፈጥሩ ንግግሮችን ማድረግ በሕግ የሚያስጠይቅ ከባድ ወንጀል ነው።

ፓስተሩ በአሁኑ ወቅት በሌላ ክልል እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ደምጦ፣ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፌዴራል የሕግ አካላት ጋር የቅርብ ክትትልና ንግግር እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የጀግኖች መፍለቂያ፣ የኩሩው ኦሮሞ ሕዝብና የተለያዩ ሃይማኖቶች በክብር የሚኖሩባት ሰላሌ ስም መነካቱ የሕዝብ ቁጣ የቀሰቀሰ በመሆኑ፣ ሕጉ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል ብለዋል ሀላፊው።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ዓቃቤ ሕግ መምሪያው የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንደሚወስድና የምርመራውን ውጤት በየጊዜው ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

…………………………………………………

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News