Homeዜናጥር ላይ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) ተራዝሟል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ...

ጥር ላይ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) ተራዝሟል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
21/04/2018

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የመውጫ ፈተናው አልተራዘመም በታቀደለት ጊዜ ይሰጣል ሲል አስታውቋል።

ምዝገባ በባለፈው አርብ እለት አስር ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን በክፍያና አንዳንድ ነገሮች ላይ የተቸገሩ እንዲያጠናቅቁ እስከ ዛሬ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ጊዜ እንደተሰጣቸው እና ፈተና የሚሰጥበት ትክክለኛ ቀኑ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

በርካታ ተፈታኞች በ2018 ዓ/ም ጥር ላይ ይሰጣል የተባለው የመውጫ ፈተና ተራዝሟል የሚል አወዛጋቢ መረጃ ደረሰን በሚል ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩ የሚመለከተው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን እንደሆነ አስታውቋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ስማቸው ያልተገለፀ አንድ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራር በሰጡት ምላሽ “ምዝገባው አርብ እለት አይደል እንዴ የተጠናቀቀው፣ አይራዘምም። ቁርጥ ያለ ቀኑን አላሳወቅንም፤ በቅርቡ በቀናት ውስጥ እናሳውቃለን ” ብለዋል።

ፈተናው እንደማይራዘም የገለፁት አመራሩ፣ ” ምዝገባ ደግሞ አርብ እለት ወደ አስር ሰዓት አጠናቀናል። በክፍያና አንዳንድ ነገሮች ላይ ለተቸገሩ እንዲያጠናቅቁ እስከ ነገ ጊዜ ሰጥተናቸዋል፤ ለሁሉም ሳይሆን ለተወሰኑ ጥያቄ ላቀረቡት ሲሉ ተናግረዋል።

እስከዛሬ እንደሚሰጠው ሁሉ ፈተናው በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን፣ የፈተናው ጊዜ ከጥር መጨረሻ፣ የካቲት 2018 ዓ/መ መጀመሪያ ሳምንት አያልፍም የግድ ነው፤ ልጆቹም ይጠብቁናል፤ እኛም ተዘጋጅተናል። አዲስ መረጃ ካለም በቅርቡ እናሳውቃለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አመራሩ “ምዝባ ስላደረግን፣ ስንት ተመሪዎች ተመዘገቡ ? በምን ፕሮግራም ተመዘገቡ ? የትኞቹ ፕሮግራሞች ላይ ይሰጣል ? የትኞቹ ላይ አይሰጥም ? የሚለው ግምገማ ስለሚፈልግ ነው እንጅ ይህን ያልኩት የተያዘ የእቅድ ቀን አለ” በማለት ትክክለኛ ቀኑን ለመግለጽ ያልተቻለበትን ምክንያት አስረድተዋል።   

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

        
ሰዎች በተለያየ ስራ ሆነው ለመፈተን ስለሚያቅዱ እንዳንረብሻቸው በደንብ የተረጋገጠ ቀን ይነገር በማለት ነው ” ያሉ ሲሆን የተመዝጋቢዎች ብዛት አልታወቀም ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ ” ገና፤ ከተመዘገቡ በኋላ ከአግባብነት፣ ከክፍያ… ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር ከትምትርትና ስልጠና ባለስልጣን ጋር እንገመግመዋለን፤ ያ ውሳኔ ላይ ካለፈ በኋላ እናሳውቃለን ሲሉ ገልፀዋል።

………………………………………..

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News