Homeዜናበምሥራቅ ወለጋ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ባደረሰው ጥቃት 19 ሰዎች ተገደሉ

በምሥራቅ ወለጋ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ባደረሰው ጥቃት 19 ሰዎች ተገደሉ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና
24/04/2018

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ “በኦሮሚያ ልዩ ኃይል” ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት 19 ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸውን እና መዘረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። እናት ፓርቲ እና ኢህአፓ ጥቃቱ “በመንግሥት መዋቅር የተፈጸመ” መሆኑን በመግለጽ ሲያወግዙት የክልሉ እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስካሁን ምንም ያሉት ነገር የለም።

በወረዳው የአማራ ተወላጆች ይኖሩበታል በተባለው ጠጋ ጂጊ (ሻሾ በር) አነስተኛ ከተማ ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም. አንድ መነኩሴን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በስለት እና በጥይት “በአሰቃቂ ሁኔታ” ተደብድበው መገደላቸውን የዐይን እማኞች እና የሟች ቤተሰቦችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። ከጥቃቱ ሁለት ቀናት አስቀድሞ በአካባቢው ለወራት የቆየው የመከላከያ ሠራዊት ለቅቆ ሲወጣ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል የሆነው “የኦሮሚያ ልዩ ኃይል (ልዩ ኮማንዶ)” መግባቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ማክሰኞ ታኅሣሥ 14 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በአካባቢው የተኩስ ልውውጥ መጀመሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ የተኩስ ልውውጡ በማን መካለል እንደተደረገ እንደማያውቁ አንድ ነዋሪ ሲናገሩ፤ ሌላ ነዋሪ ደግሞ መሳሪያ አናስረክብም ብለው ጫካ በገቡ እና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች እና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል መካከል ውጊያ መደረጉን ተናግረዋል። በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች ቅርበት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን በአካባቢው ግጭት እንደነበር የሚጠቁም መረጃዎች ወጥተዋል።

ግጭቱ ከመቀስቀሱ አስቀድመው ስጋት ያደረባቸው እና ከተቀሰቀሰ በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ቀበሌዎች መሸሸታቸውን ጠቁመው፤ ውጊያው እስከ እኩለ ቀን ድረስ መቆቱን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ይደርስብናል ያሉትን ዛቻ መሠረት አድርገው ባደረባቸው ስጋት መከላከያ ሠራዊት ሲወጣ ቤተሰባቸው እንዲሸሽ እንዳደረጉ የተናገሩ አንድ የዐይን እማኝ፤ ከሁለት ቀናት በኋላ ሲመለሱ እልቂት እና ውድመት መመልከታቸውን አስረድተዋል። የሁለት ሰዎች አስከሬን ማየታቸውንም ገልጸዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የደረሱ ነፍሰ ጡር በመሆናቸው የተኩስ ልውውጡ ሲደረግ ቤታቸው እንደነበሩ የተናገሩ አንድ የዐይን እማኝ ከሟቾቹ ውስጥ የአምስት ልጆች አባት የሆኑት ባለቤታቸው እንደሚገኙበት አብራርተዋል። ሦስት “አረንጓዴ ቡራቡሬ” የደንብ ልብስ የለበሱ “የኦሮሚያ ልዩ ኃይል” አባላት እና አንድ ሚሊሻ ቤታቸው መጥተው የጉልበት ሠራተኛ የነበሩትን ባለቤታቸውን ዐይናቸው እያየ በአቃቂ ሁኔታ እንደገደሏቸው ተናግረዋል።
“እኔ ድንጋይ ሆንኩኝ፤ ልጆቼ እየተንጫጩ እላዩ ላይ ሲወድቁ፤ ‘አምጣው መሳሪያውን እመታቸዋለሁ’ ሲል እኔ በጥርሴም መሰለኝ ያነሳኋቸው፤ ሦስቱንም [ልጆች] አነሳኋቸው። ተደፍቼ እኔን ግደሉኝ ብዬ ለመንኳቸው” ሲሉ ስለ ድርጊቱ ገልጸዋል።

ባለቤታቸው ቤታቸው በር ላይ በተገደለበት ስፍራ ከተቀበሩ ከአምስት ቀናት በኋላ ሥላሴ በተባለ ቤተ ክርስቲያን ዳግም መቀበራቸውን ተናግረዋል። እማኞች አብዛኞቹ ሟቾች በስለት (ቢላዋ) ተጠቅተው መገደላቸውን እና አስከሬናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተቆራርጦ እና ተጎድቶ መገኘቱን ተናግረዋል።

አንድ የቤተሰባቸው አባል የተኩሱ ልውውጥ ጋብ ሲል ቤታቸውን ለማየት ሲመጡ መንገድ ላይ እንደተገደሉባቸው የተናገሩ ሁለት ሰዎች፤ “አካላትም የለው” ሲሉ አስከሬናቸው ከባድ ጉዳት ደርሶበት ከቀናት በኋላ መገኘቱን ገልጸዋል። “የሞቱትን እንኳ ደርሰን ለመቅበር እና አስከሬን ለማንሳት አልቻለንም። እስከ ቅዳሜ ዕለት ድረስ አስከሬናቸው እንዳልሆነ ሆኖ [አገኘናቸው]” ሲሉ አንድ እማኝ ተናግረዋል።

የአይን እማኞች እና የሟች ቤተሰቦች ውስጥ አራቱ በጥቃቱ የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎችን ቁጥር 19 ነው ሲሉ አንድ ነዋሪ ደግሞ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል። አንድ ነዋሪ ለጥቃቱ ምክንያት ነው የሚሉትን ሲያብራሩ “የእናንተ ልጆች ናቸው ከፊደራል መንግሥቱ ጋር የገጠሙት። ፋኖን ትደግፋላችሁ” በሚል ነው ብለዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

እናት ፓርቲ እና ኢሕአፓ ጥቃቱን አውግዘው ባወጡት መግለጫ ጥቃቱን “በመንግሥት መዋቅር በግልፅ” የተፈፀመ እና “በእጅጉ የሚያሳዝን ተግባር” ብለውታል።
አክለውም ይህ ተግባር “መንግሥት በዓላማና በስውር የሚፈጽም ደባ በመሆኑ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭፍጨፋውን እንዲያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን” የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ፓርቲዎቹ አሳስበዋል።

ባለቤታቸው የተገደለባቸው ነፍሰ ጡር ነዋሪ “መሬት የለኝ፣ ምን የለኝ፤ እሱ ነው የቀን ሥራ ሠርቶ የሚያስተዳድረኝ። አምስት ልጅ ይዤ የምልሰው የምቀምሰው አንድ ነገር እንኳ የለኝም” ሲሉ መፃኢ ሁኔታቸውን በሚመለከት ለቢቢሲ ተናግረዋል። እሱን እንዲህ ሆኖ ስላገኘሁት ምግብ ትቻለሁ፤ ተጎድቻለሁ” ሲሉ አሁን ያሉበትን ሁኔታ አንድ የሟች ቤተሰብ ተናግረዋል።

በአካባቢው መከላከያ ሠራዊት ተመልሶ የገባ ቢሆንም፣ ማኅበረሰቡ ስጋት እና ጭንቅ ውስጥ መሆኑን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
አንድ የሟች ቤተሰብ “አሁንም መጡ እየተባለ ሰው እየተሸበረ ነው ያለው። መኖር አይደለም የምንኖረው። .ስጋት ላይ ነው ያለነው፤ ምጥ ላይ ነው ያለነው” ብለዋል።
“ያለፈው ሳይሆን እኛን እያሳሰበን ያለው ወደፊት የሚመጣው ነገር ነው። አሁንም ቢሆን በቅርብ ርቀት አሉ። መውጫ የለንም፤ ግራ ቀኝ በር ተዘግቷል” ሲሉ ሌላ ነዋሪ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ክልልም ሆነ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ስለጉዳዩ የሰጡት ማብራሪያ የለም። የጊዳ አያና ወረዳ ከዞኑ ዋና ከተማ ነቀምቴ በ100 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚርቅ ወረዳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች እንደተፈጸሙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ወረዳው የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን የሚያዋስን አካባቢ ሲሆን በድንበር አካባቢም ፋኖ ነን የሚሉ ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱ እና ጥቃት እንደሚፈጽሙ አብራርተዋል።

- Advertisement -

…………………………………………

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News