
ከኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሐና ፡ ለንደን ዩኪ
የአብይ የቅማል ትርክት
ጠላቶቼን እንደ ቅማል አራግፋቸዋለሁ ያለው አብይ ጠላት ብሎ ሲጠራ ከድንበር ውጭ ያሉትን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች አይደለም ፡፡ ግብፅን ወይ ኤርትራን ወይ ሱማሊያን ሳይሆን የእሱን ግፍ እና በደል አንቀበልም ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብን ነው ፡፡ ይህን ሕዝብ በይፋ እና በአደባባይ ቅማል ብሎ የጠራ መሪ ለአንድ አፋታም በስልጣን ላይ መኖር አልነበረበትም ፡፡ አንድን ሕብረተሰብ ቅማል ፡ ጅብ፡ በረሮ ወዘተ ብሎ መጣራት የዘረ ማጥፊያ ወንጀል ዋዜማው ነው ፡፡ ይህም በተባበሩት መንግስታት ቻርተር የተወገዘ ነው ፡፡ የጀርመን ናዚዎች የጁዋችን ወደ ጅምላ ግድያ ከመውሰዳቸው በፊት በቅማል እና በበሽታ አስተላላፊት ተውሳክ ይመስሏቸው ነበር ፡፡ በሩዋንዳም በተደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት የቱሲን ማህበረሰብን በረሮ በማለት ሁቱዋች ሲጠሯቸው ነበር ፡፡ በኢትዮጵያም ጅብ ትብሎ የተሰየመ ማህበረስብ አለ፡፡
ዛሬ አብይ ቅማል ብሎ ከጠራቸው ጠላቶቹ መካከል አንዱ አገዛዙ አልገዛም ያለውን የአማራ ሕዝብ ነው ፡፡ አብይ ከጅምሩ እንደ አማራ ሕዝብ የፈራው እና የሚፈራው ሕዝብ የለም ፡፡ አብይ አማራን በጠላትነት በይፋ መፈረጅ የጀመረው ገና የስልጣን መንበር ሳይጨብጥ ፃፋ በተባለው በእርካብ እና መንበር መፅሃፍ ውስጥ ነው ፡፡ አብይ ስልጣን ከያዘ ቀን ጀምሮ ወደ ስልጣን ያመጡትን የአማራ አመራሮች በመግድል ነው የተጠመደው ፡፡ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ ፡ የዶር አምባቸውን ግድያ ፡ የጀነራል አሳምነውን ግድያ ሁሉ የሚያሳየን አብይ በአማራ ሕዝብ ላይ ያለውን ፍራቻ እና ጥላቻ ነው ፡፡ ይህ ፍራቻ እና ጥላቻ ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን ወያኔ ከ14 አመቱ ጀምራ ወስዳ ኮትኩታ በጥላቻ አይኑን አሳውራ ስላሳደገችው ነው ፡፡ የፈራ ደግሞ ብዙ ብዙ በደል እና ጥፋት ያደረሳል ፡፡
አብይ የአማራን ሕዝብ አንገት ለማስደፋት እና ተገዢ ለማድረግ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙትን አማሮች በግፍ በማንነታቸው የሚገደሉበትን ሁኔታ ከማመቻቸቱም በላይ እስካሁን ተሳስቶም በኦሮሚያ ስለሚገደሉት አማሮች እና ክርስቲያኖች ትንፍሽ አላለም ወደፊትም አይልም ፡፡ ያም ብቻ አይደለም አብይ በተወካዮቹ አማካኝነት የአማራ ደም የኦሮሚያን መንግስት ለማዋለድ የሚፈስ ደም ነው እስከማለት የደረሰ መሪ ነው ፡፡ በአብይ ጋር ይሰሩ የነበሩ የኦሮሞ ፖለቲካኞች ፡ አቶ ታዬ ደንደአ፡ ዶር ሚልኬሳ ሚዲጋ ፡ ዶር አንጋሳ ኢብራሂም የመሳሳሉት በኦሮሚያ በአማሮች ላይ የሚደረገውን ግድያ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንግድ በአብይ እና በሰበሰባቸው አካላት የሚመራ እና የሚደገፍ መሆኑን ደጋግመው ነግረውናል ፡፡ በሚያሳዝን መልኩ አብይን የተጠጉ አማሮች ይህንን እውነታ ለመካድ ሲጋጋጡ እናያለን ፡፡ ግን ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ነው ጉዳዩ፡፡ እነሱ እንኳን ባይነግሩን እንደ አገሪቱ ዕርእሰብሄር ወይም መሪ የአንድ ዜጋ ሞት ሊቆረቁረው እና ሊጠይቅ ሲገባው አብይ በተቃራኒው ችግኝ የምተክለው ለሞቱት ጥላ እንዲሆን ነው የሚል ፌዝ በሺዎቹ ነፍስ እና ሞት ላይ የቀለደ ነፍሰ ገዳይ ነው ፡፡
ግፍ የወለደው ሕዝባዊ ፋኖነት
የአማራ ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ግፋ በኋላ ነው ነፍጥ አንስቶ ወደ ትግል የገባው ፡፡ በእርግጥ የአማራ ፋኖ አነሳሱ እንደ ዘመናዊ ትጥቅ ትግል በፖለቲካ በነቁ ሙሁራኖች ከላይ ወደ ታች ተደረጅቶ ወደ ትጥቅ ትግል የገባ ሳይሆን የወገኖቻቸው ሞት ያስከፋቸው ቁርጥ የድሃ ገበሬ ልጆች የተንሳ እቅስቃሴ ነው ፡፡ በአብዛኛው በግል ወኔ እና ድፍርት፡ በራስ ስንቅ እና ትጥቅ የታገዘ ነበር፡፡ ይህም አነሳሥ የራሱ ጥቅም እና ጉዳትን ይዞ መጥቷል ፡፡ ነገር ግን ሁላችንንም የሚያስማማን አማራ ነፍጥ ያነሳው በራሱ ሕዝብ ላይ ለመተኮስ ሳይሆን የአማራን ጠላቶች ለማበርከክ እና የአማራ ሕዝብን ለመታደግ ነው ፡፡ በጥቂት ጎበዞች የተጀመረው የአማራ ሕዝብ እንቅስቃሴ ዛሬ በብዙ ሺ ፋኖዎችን አፍርቷል ፡፡ ነገር ግን ይህ ሂደት ቀጥተኛ እና ችግር አልባ አልነበረም ሊሆንም አይችልም፡፡ በአንድ በኩል ከአመሰራረቱ ዘመናዊ የፖለቲካ እና የትጥቅ ትግል አደረጃጀት የተከተለ ባለመሆኑ በአደረጃጀት ላይ ብዙ ክፍተቶች አስከትሏል፡፡ በጥቂት ጀግናዎች የተጀመረው ትግል የበለጠ መልክ እና ቅርፅ የያዘው የክልሉ ልዩ ኃይል በፈረሰ ወቅት ነበር ፡፡ የክልሉ ልዩ ኃይል መፈረስ ፋኖን በመሳሪያ እና በሰው ኃይል ቢያበልፅገውም በአደረጃጀት እና በፖለቲካ መርሆ የራሱን ችግር ይዞ ነበር የመጣው ፡፡ ከልዩ ኃይል የወጣው ታጣቂ በቅዬው ከሚገኘው የፋኖ አደረጃጀት ጋራ ትግሉን ተቀላቀለ፡፡ ይህ ልዩ ኃይሉ ከመፍረሱ በፊት ለመንግስት ቀኝ እጅ ለሆነው በተለምዶ ብአዴን ብለን የምጠራው የፖለቲካ ክንፍ ወታደር የነበረ ነው ፡፡ ይህ ከወያኔ ስራት የተወረሰው ልዩ ኃይል የየፖለቲካ ንቃተ ሕሊናው የታነፀ በአብዩታዊ ዴሞክራሲ እና በብሄር ፖለቲካ ነው ፡፡ ስለሆነም ይህ ኃይል ወደ ፋኖ ሲቀላቀል ወይም ፋኖ ሲሆን በፖለቲካው አስተሳስቡ ብአድናዊ ነበር፡፡ በተለያየም መንገድ አኩራፊ ብአዲናዊያን ጋር ግኝኙነት የነበርው እና መመሪያም የሚቀበል ነበር፡፡ ፋኖ ከአደረጃጀቱ የራሱ የፖለቲካ መርሆ ፍልስፋና ስላነበርው ይህን ኃይል በአዲስ አሰተሳብ ሊቀርፀው አልቻለም ፡፡ ይህ የፖለቲካን ክፍተት አምጥቷል ፡፡

አርበኛ አስማረ ዳኜ ሲታወስ
የፋኖ የትግል እፀፆች :
የተበታተነ ኢሳይሳዊ ትግል
ከላይ እንዳልኩት ይህ ሁሉ ሲሆን ፋኖ እንዴት ዘመናዊ እና ሕዝባዊ ትግል ማከናወን እንዳለበት የተሰራ ሥራ አልነበረም ፡፡ ለእዚህ ዋና መሰናክሉ አኩራፊው የብአዴን ክንፍ እና በአገር በውስጥም በውጭም ያለው ተስፈኛው ቴክኖክራት ነው ፡፡ ይህም በመሆኑ ከብአዴን በጠራ መልኩ ድርጅት እንዴት ይመሰረት ፡ እንዴት ይመራ ፡ አባሎች እንዴት ይመልመሉ ፡ እንዴት ይመሩ ፡ የድርጅቱ ሕገ ደምብ እንዴት ይሁን፡ ከሕዝብ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ባለ መርሆ ይከናወን የሚለው ሰነድ አልተሰራም ፡፡ ከእዚህ ቀደም ከነበሩ ከተሳኩ ካልተሳኩ የትጥቅ ትግሎች የመማር ሂደት አልነበረም አሁም በቅጡ ያለ አይመስልም፡፡ ከብአዴን በጠራ መልኩ አዲስ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ( ትምህርት) አልተሰራበትም አልተዋቀረም ፡፡ ለትግል የወጣው ፋኖ ፡ ትግሉን የሚያግዘውን ማሕበረሰቡን የሚያስተምሩ የሚያነቁ ሰነዶች አንቂዎች ወይም ደቀመዛሙርት አልተዘጋጁም አላዘጋጀም፡፡ የሁሉም እሩጫ በደመ ነፍስ ነበር ፡፡ ፋኖ ለትግሉ የሚጠቀምበትን የፖለቲካ ሰነድ አልነበርውም ፡፡ ፍኖተ ካርታ ( እኔም የተሳተፍኩበት) በውጭ ባሉ የአማራ ምሁራኖች ለማዘጋጀት ተሞክሮ ነበር ፡፡ በዝግጅቱ ውስጥ እንደነበረ ሰው ልናገር የምችለው በዝግጁ ውስጥ የነበረው ስብስብ ( ከይቅርታ ጋር) ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ የሌለው ፡ የራሱ አጀንዳ ያለው ፡ ፈራ ተባ የሚል፡ ትግሉን በራሱ ጎጥ መነፅር የሚመለከት ፡ ቁርጠኝነት የጎደለው ትችት ወይም ሂስ የማይቀበል አኩራፊ፡ በፖለቲካ ቋንቋ የመደባዊ ባህሪያቶች እስረኞች ናቸው፡፡ በሌላም ስብስብ የታዘብኩት ለአማራ ሕልውና እንታገላለን የአማራን ወይም የፋኖን ትግል እናግዛለን ብለው የተሰባሰበው ስብስብ አንድም ትግል ትግል የማይሸቱ ለወደፊቱ ፋኖ በለስ ቀንቶት መንግስት ቢመሰርት እራሳቸው በድርጅት ስም ለልስጣን አዘጋጅተው የተቀመጡ ሆነው አግቻቸዋለሁ ፡፡ አንድ ማሳያ ላንሳ ፡ አንዱ የአማራ ነፃ አውጪ ድርጅት መስርቻለሁ አብይን አንኮታኩቼ ነው የምጥለው ያለ ግለስብ የመጀመሪያ የትግል ስልቱ ስንደቁንን መቀየሩ ላይ ነበር ፡፡ እንግዲህ ለእዚህ አማራ ነፃ አውጪ ነኝ ባይ አማራን ነፃ የሚያወጣ ሰንደቁን በመቀየር ነው ማለት ነው ፡ ይህ ሰው በመእረጉ ዶክተር ነው፡፡ በሌላም ስብስብ ለአማራ እንሞግታለን (advocacy) ያሉ ስብስቦች ውስጥ በድርጅቱ አርማ ላይ የአማራ ታሪካዊ ባሕላዊ ሰንደቁን ጨምሮ ይኑር አይኑር የሚል ሙግት መግጠሜ፡ ማየቴ እና መስማቴ እውን ያለሁበት ስብስብ ለአማራ የሚታገል ነው ወይ የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገድዶኛል ፡፡ በአማራ ስም ተደራጅቶ በአደባባይ የአማራን ባሕል ታሪክ እና እራእይ የሚያፀባርቅ አርማ አልሰራም ፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አልጠቀምም የሚልህ ስብስብ በፖለቲካል ትርጓሜው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ይህም ትርጓሜ ይህ ስብስብ በፖለቲካ በስነልቦና የተሸነፈ የተመታ አማራ ነው ወይ የጠላት መልእክተኛ ነው ፡፡ እንዲህ አይነቶች ብዙ ምሳሌዎች ማንሳት ይቻላል፡፡ እንዲህም በመሆኑ ፤ ለትግሉ የሚሆን ሚዛኑን የጠበቀ ሳይሳዊ የሆነ ያለፈውን ያየ፡ የአሁንን የዳሰሰ የወደፊቱን የተነበየ ሰነድ ለአማራው የኅልውና ትግል ለማዘጋጀት አልተቻለም ቢዘጋጅም የትግል ሰነድ ሳይሆን የመንግስትነት ሰንድ ቅርፅ የያዘ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንዱ የፋኖ ክፍል ማኒፌስቶ አውጥቶ ነበር ያ መልካም ጅምር ሆኖ ሳለ እንደ ማታገያ ሰነድ ሆኖ የቀረበ ሳይሆን ወደፊት መንበር ስልጣኑን ሲይዙ የሚከተሉትን ማህበራዊ ፡ ፖለትካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ እና ዓለም አቀፍ ፖሊሲን የሚያሳይ ነበር ፡፡ ይህ በባሕሪው ስህተት ባይሆንም የማታገያ ሰንድ ግን ሊሆን አይችል፡፡ ለምሳሌ በትግል እና በመንግስትነት ወቅት ሴቶችን ከጥቃት መከላከል ሁለቱ የተለያዩ ጉዳዮች ሲሆኑ ሁለቱም የተለያየ ስልቶች ፖሊሲዎች እና አደረጃጃቶች የሚጠይቁ ናቸው ፡፡ የመጀመሪያው ማንቃትን ማደራጀትን ማስታጠቅን የሚጠይቅ ሲሆን ፡፡ ሁለተኛው ሕግን በነጋሪት ጋዜጣ ማውጣት የወጣውን ሕግና በተቋም ማስፈፀምን የሚጠይቅ ነው ፡፡ ተግባብተናል??
የወዳጅ እና የጠላትን አሰላለፍን በግልፅ ያለየ ትግል
በተጨማሪም የጠላት አሰላለፍ አመዳደብ እና አያያዝ በዘመናዊ ጥናት የታገዘ አልነበረም አሁንም አይደለም ትክክለኛ ትንታኔም አልተሰጠበትም፡፡ ዘግይቶ የበቀለው የአማራ ብሄረኝነት ውስጥ የአማራው የጠላት መስፈርቱ አንድ እና አንድ ነው፡፡ ፈረጆች እንደሚሉት Binary classification ነው እነሱ እና እኛ፡፡ እርዩተ ዓለም የሚባል ነገር በመዘገበ ቃላቱም የለም ፡፡ እንዲያውን አንዱ የአማራ ትግል አግዛለሁ የሚል አንጋፋ ፖለቲከኛ የአማራ ትግል እርዮተ አለም ሊኖረው አይችልም ብሎ ሲናገር የሰማሁት መሰለኝ፡፡ ለምሳሌ አሁን አማራ ክልል ተብሎ ከተከለው ውጭ ያለው አማራ አዲስ አበባን ጨምሮ ወይ ጠላት ነው ወይ የተገለለ ነው፡፡ ሐረር ውስጥ ስለሚበደሉት አማሮች የሚጮኽው ሐረር የተወለደው አማራ እንጂ አሁን ካለው ክልል አይደለም፡፡ አማራዊነት ወይም አማራኒዝም ወይም ኢትዮጵያዊነት በመርሆም ሆነ በፍልስፍና ደረጃ አልዳበረም አልተጠናም ፡፡ መነሻችን ሃመሩ ሃ መደረሻችን ሃሌቷ ሃ የተባለትም መርሆ የሚመስል ግን በሳይሳዊ መንገድ ያልተተነተነ የብሽሽቅ መስመር ነበር ፡፡ ሕዝባዊም መሰረት ስላነበረው አሁን ብዙም ሲባል አይሰማም፡፡ አማራነትም በትክክለኛው መንግድ አልተብራራም ፡፡ አማራነት በእናቱም በአባቱም እስከ ሰባት ቤቱ ድረስ የደም ጥራት ያለው ነው የሚለው የተሳሳተ ምልከታ ዘመኑን ያላዋጀ ፖለቲካ መስመር ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ እሳቤ ቅይጥ ማንነት ያለው አማራ ከፖለቲካው ትግል እንዲገለል ፡ ወይ በጥርጣሪ አይን እንዲታይ ከከፋም በጠላትነት እንዲፈረጅ አድርጎታል ነው ፡፡ የፋኖ ወዳጅ እና ጠላት አሰላለፍ በተመለከተ ፡ በስልታዊ ( Tactical) እና በእቅዳዊ ( Strategic) ጥናት አድርጊያለሁ ( ለግዜው አልተሰራጨም) በጥናቴ ካገኘሁት ቁም ነገር ሁለቱን ላካፍላችሁ ፡አንዱ የዘር ጥራትን የሚመለከተው ነው እንዲህም ይላል፡፡ The Extremist Amhara Racialist Position (“Seven Generations”) This faction is a liability, not a vanguard. No successful political movement in a plural society survives this ideology. It is suicidal and it helps Amhara’s enemies more than Amhara: በሌላ በኩል ሁለተኛው አክራሪ ብሄርተኞችን በተመለከተ ነው ፡፡ የአማራ የሕልውና ችግር ምንጭ የብሔር ፖለቲካ ከሆነ ብለን ካመንን የብሔር ፖለቲከኖች ድርድር የማይደረግባቸው መዋቅራዊ ጠላቶች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ Structural Enemies (Non-Negotiable) ፡ These are actors whose political survival depends on Amhara weakness. A. Hardline Ethnic Federalist Elites (Across Groups) ፡ Not entire ethnic groups—elite factions. Why enemies? Their legitimacy narrative is built on “historic Amhara oppression” Amhara empowerment undermines their moral foundation፡ They benefit materially from Amhara displacement and fragmentation፡ These actors do not need Amhara dead—but they do need them politically weak. እንግዲህ የፋኖ ትግል ሲጀመር እና ሲከናወን እነዚህን ውስጣዊ እና ወጫዊ ጠላቶቹን በትክክል ሳይተነተኑ እየተከናወነ ያለ ነው ማለት ይቻላል ፡፡ ይህ የጠላትን አሰላለፍ እና አመዳደብ በቅጡ ካለመረደት የተነሳ ወዳጅ መሆን የማይገባቸ ወዳጅ ሲደረጉ ጠላት መሆን የማይገባቸው ወዳጅ ሲደረጉ ይስተዋላል፡፡ በልደቱ ጎራ ያለውን አሰላለፍ እንደ ምሳሌ ብንመለከት ለእዚህ ጥሩ ግብአት ነው ፡ ልደቱ ከአፈራው አማራ ይልቅ ለገደለው ጁዋር ወይም ወያኔ ቅርበት አለኝ ሲል እና ሲተባበር ይታያለ ፡፡ ተመሳሳይ አሰራርም በፋኖ ውስጥም ተከስቷል የሚል ክስ አለ፡፡ ወደድነውም ጠላነውም ማስራሻ ሰጤ ትግሉን ለቅቄ የወጣሁት ትግሎ ወይም የትግሎ አጋሮቼ ከቆሙኩበት አላማ በተቃራኒ ስለሄደብኝ ነው ብሏል ፡፡ ሌሎችም የአማራ ፖለቲካኛ ነን የሚሉና በሚዲያ የማይጠፍ ግለሰቦችም አማራ በሕገ መንግስቱ ይድናል ሲሉ ተደምጠዋል ያ ማለት በጠላትነት የተሰለፈው እና አማራን ግደለው እረደው የሚለው አካል ወዳጅህ ነው ማለት ነው ፡፡ በፋኖ ትግል ውስጥ አንዱ ችግሩ ወዳጅ እና ጠላትን በቅጡ ላይቶ አለማወቅ ነው ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር ማስተዋል ያለብን አንዳንድ የፋኖ አደረጃጀት እና ትግል ከዘር ጥራት አልፎ የመንደር /የጎጥ ውስጥ የተደበቀ ነው ፡፡ ይህ ማለት አንዱ ጎጥ ለሌላው ጎጥ ስልታዊ ጠላት ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህ በጣም አደገኛ እና ትግሉን እየገደለው ያለ ክስተት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ፡፡
ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መልስ ያልሰጠ አደረጃጀት
ከፋኖ ትግል አንፃር አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያለው ታሪካዊ ዝምድና እና ትስሥር በቅጡ አልተብራራም ፡፡ አንዳንዱ በኢትዮጵያ መአቀፍ ስለኖርን ይህ ማእቀፍ ነው እንድንጎዳ ያደረገን ስለሆን የኢትዮጵያን ካባ ጥለን በአማራነታችን ብቻ መሰባሰብ እና በአማራነት መታገል የሚለ ሲሆን ሁለተኛው ኢትዮጵያን ከስር መሰረቷ የገንባናት የሞትንላት አገራችን ነች ዛሬ አገራችን ብለው የሚጠሯት ኦሮሞዎች ሳይቀሩ ባይተዋሮች እና ከ450 አመታት በፊት የተከሰቱ ናቸው ፡፡ እና አገራችንን ለማንም አስረክበን አንሄድም አማራ በኢትዮጵያዊነት መአቀፍ የሚድን ነው የሚሉ ናቸው ፡፡ በግሌ በሁለተኞቹ መስመር እስማማለሁ፡፡ ይህን ተከትሎ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ አንዱ ያለተዘጋጀው እና ያልተጠናው ጉዳይ ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ እንዴት አብሮ መሰራት አብሮ መኖር ይቻላል ፡ ኢትዮጵያን እንዴት ለሕዝቦቿ ምቹ አደርጎ መገንባት ይቻላል በሚሉ ጉዳዩች ላይ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ፋኖ በመርሆ ደረጃ የተቀበላቸው እና በሰራ ላይ ያዋላቸው ሰነዶች የሉም ፡፡ ለምሳሌ ድህረ አብይ ምን አይነት መንግስት ምን አይነት ሕብረት ያስፈልጋል በሚለው ጉዳይ ላይ ምንም ሥራ አልተሰራም፡፡ በሌላም በኩል ብሶት ካለበት የኦሮሞ ሕዝብ ጋራ ፡ ብሶት ካለበት የትግራይ ሕዝብ ጋራ ወዘተ እንዴት ለጋራ አላማ በጋራ መስራት ይቻላል በሚል በቅጡ የተሰራበት ሰነድ የለም ፡፡ ለምሳሌ በሰሜን ሸዋ የሚኖሩ ኦሮሞች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ በብዙ መልኩ ከአማራው ማሕበረስብ ጋራ የተጋመዱ ናቸው በእዚህም ምክንያት በአክራሪ ኦሮሞች በጠላትነት የሚታዩ እና የሚታደኑ ናቸው፡፡ ይህን ማሕበረሰብ እንዴት አጋር አድረገን እና ትግሉን ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል የሚለው ጥያቄ ገና አልተመለሰም ፡፡ በጅምላ ብቻ ከኑግ ጋር የተገኝሽ ስሊጥ አብረሽ ተወቅጭ አይነት ፖለቲካ ለድል አያበቃም ወዳጅ ሊሆኑ የሚችሉ ኃይሎችንም ጠላት ያደረጋል ፡፡ ከእዚህ ጋር በተያያዘ የጠላት አሰላለፍ እና አመዳደብን በተመለከተ ከሠራሁት ሥራ ውስጥ አንዱን ላካፍላችሁ ፡፡ Potential Long-Term Allies፡ . Civic Federalists and Post-Ethnic Reformists (Across Groups) ፡ Oromo, Amhara, Gurage, Sidama, mixed-identity Ethiopians፡ Oppose ethnic cleansing፡ Support equal citizenship and territorial integrity፡ Why crucial፡ They offer legitimacy beyond ethnicity፡ They reduce Fano’s isolation፡ They counter the “Amhara = reactionary” narrative፡ ይህንን ከአሁኑ ግንዛቤ ውስጥ ያልከተተ የፋኖ ትግል ወደፊት ለመራመድ አዳጋች ይሆንበታል፡፡
በፋኖዎች መካከል ሕብረትን ያልፈጠረ ትግል
በሌላም በኩል በተመሳሳይ ትግል ላይ ካሉ አነሰተኛ፤ መካከለኛ፤ በከፍተኛ አደረጃጃት ካላቸው ፋኖዎች ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋራ እንዴት አብሮ መሰራት ይቻላል ፡ እንዴት መጣመር ይቻላል፡ ቅራኔን እንዴት መፍታት ይቻላል ወዘተ በሚሉ ጉዳዩች ላይ ጥናትም ትንታኔም አልተሰራም ፡፡ ስለሆነም አንዱ ፋኖ ሌላውን ፋኖ ሲኮንን ሲያሳድደው ይታያል፡፡ ይህ መሰርቱ የዓላማ ልዩነት ሳይሆን አንዱ አንዱን በቅድሚያ አጥፍቶ አራት ኪሎ የመግባት እሳቤ ስላለው ነው ፡፡ የፋኖ መሪነት እና የኢትዮጵያ መሪ መሆን የተላያዩ ነገሮች መሆን አለባቸው ፡፡ የፋኖ መሪ የሚታገለው ከፋኖ መሪነት ወደ የአገር መሪነት እራሱን ለመቀየር ሳይሆን አገሪቱ በሕዝብ የተመረጠ አስተዳዳር እንዲኖራት ነው ፡፡ አሁን ያለው የፋኖ አደረጃጀት እና አመራር ይህን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው ፡፡ ለእዚህም ነው በፋኖዋች መካከል ሕብረት አንድነት ለመፍጠር ያለተቻለው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትርነት እሩጫ፡፡
በሌላም በኩል በአማራ የሕልውና ትግል ውስጥ የአማራ ሙሁራን ዲያስፖራን ጨምሮ በምን መንገድ እና ይዘት መሳተፍ እንዳለባቸው ፡ በምን መንገድ መደራጀት እንዳለባቸው የሚያሳይ አንዳችም ሥራ አልተሰራም ፡፡ ያው የተለመደው ገንዝብ አምጡ ፡ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ እና ሚዲያ ላይ ተናገሩ ከሚለው በቀር ፡፡ ይህም በመሆኑ የአብዛኛው የዲያስፖራ እንቅስቃሴ ወይ ግብታዊነት ላይ የተመሰረተ ነው ፡ ወይ ከመንፈሳዊ አላማ ወይ ከቁሳዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ ነው ፡፡ ይህን የሚያክል የሕይወት መስዋትነት የሚጠይቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የፖለቲካ አደረጃጀት ባለመመስረቱ ዲያስፖራውም ባሻው መንግድ እንዲቀሳቀስ እና አንዴ ሞቅ አንዴ ቀዝቀዝ፡ እንዲል ተደርጓል ፡፡ በግፍ የተገደሉ ወገኖችን ፎቶ ይዞ መወጣቱ ብቻ ትግል አይደለም ፡ ከአንድ ሺ የዲያስፖራ ጩኸት አንድ የቢቢሲ ወይም የጋርዲያን ዘገባ ምን ውጤት እንዳመጣ አይተናል፡፡ አንድ ቢቢሲ እና አንድ ጋርዲያን የኖረበት ምክንያት የዲያስፖራው እንቅስቃሴ የፈረ ተባ፤ የይስሙላ፡ የስሜት ፡ በጥቅም ላይ ይተመሰረት በመሆኑ ነው ይህም በአማር የሕልውና ትግል ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅእኖ ፈጥሯል ፡፡ አብዛኛው ዲያስፖራ የትርፍ ሰአት ተጋይ ወይ አጋዥ ነው ፡፡ ትግል ደግሞ በትርፍ ሰአት የሚሰራ ሥራ አይደለም፡፡
ባሕር እና አሳ
የአማራ ሕዝብ ለፋኖ ባህሩ ሲሆን ፋኖ ደግሞ በባህር ውስጥ ያለ አሳ ነው ፡ አሳ ባህሩን እንደሚያቀው ሁሉ ፋኖም የአማራን ሕዝብ ጠንቅቆ ማወቅ አለበት ፡፡ ይህን ስል ምን ማለቴ ነው? አማራ ፋኖ እንዴት አማራን እወቀው ይባላል ትሉ ይሆናል ፡፡ አግባብ ያለው ጥያቄ ነው ፡፡ ነገር ግን ይህን ሕዝብ በትክክለኛው መንገድ ማወቅ እና መተንተን የአማራ ፋኖ ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ፡፡ ለምሳሌ የአማራ ሕዝብ በደልን የሚፀየፍ ሕዝብ ነው ፡፡ በደሉ ከማንም ይምጣ በምንም ምክንያት ይምጣ በደለን ይፀየፋል ፡፡ የአማራ ሕዝብ ስለ በደል ሲናገር በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያልፍርድ የሄድች ጭብጦዬ የሚል ብሄል አለው ፡፡ ይህም አቋሙ ነው ወደ ትጥቅ ትግልም ያስገባው ፡፡ ነገር ግን በፋኖ የተወሰዱ አንዳንድ እርምጃዎች ፋኖን ከባህሩ የሚያሶጣው ሆኖ ታይቷል ይህንንም ጠላት በሰፊው እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ በቀርብ በተሰጠ ምስክርነት የልጆቼን አባት ያስተማራቸው ልጆቹ አምበርክከው በልጆቹ ፊት ገደሉት የሚለው ክስ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም ፡፡ ከዛም በላይ ከእዚህ ቀደም በማሕበራዊ ሚዲያ አንድ ፋኖ አንድን አባት በአደባባይ ሲረሽን ታይቷል፡፡ ይህ ክስተት ብዙ ሰዎችን ያስደነገጠ ነበር እኔም ሌሎችም በወቅቱ አውግዘነዋል፡፡ ይህ እንግዲህ አባይ በጭልፋ እንዳይሆን እፈራልሁ፡፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች በትግል ውስጥ የሚከሰት ስህተት ነው ተብሎም አይታለፈም ፡፡ ይህም የሚከሰተው የአማር ሕዝብ ጠቅቆ ካለመረዳት ነው፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች እንዲከሰቱ አመቺ ሁኔታ የፈጠረው ፋኖ በዘመናዊ በሰለጠነ እና ሕዝባዊ ትጥቅ ትግል መርሆ ባለመመራቱ ነው ፡፡ ያም ቢሆንም አርበኛ መንግስቱ አማረ ከአንከር ሚዲያ ጋር ባደረግው ቃለ መጠየቅ የተከሰተውን ክስተት ማስተባበሉ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ከእዚህ ቀደም ብአዴን ቅርጫፍ ነው መቁርጥ ግንዱን ነው የሚል መጣጥፍ አጋርቼ ነበር የፅሁፉ አበይት መልእክት አማራ ለአማራ ደም እንዳይቀባባ እና የትግል ትኩረቱ በአገዛዙ ላይ እንዲሆን ለማመልከት ነው ፡፡ በእርግጥ የውስጥ ጠላት በተለይ ወገን ሆኖ ወገንን የሚከዳ ጠላት ከዋናው ጠላት የከፋ ነው ፡፡ በብሄላችንም ጠላት እማ ጠላት ነው አስቀድሞ መምታት አሾክሻኪውን ነው ይባላል፡፡ ያም ቢሆንም የአማራን ስነ ልቦና ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሞት ፍርድ ከመሄድ በፊት በእስር ማቆየት ማስተማር ብሎም ወደ ትግሎ በመቀላቀል አጋር በማድረግ ሊደስ የሚችለውን አደጋ መቃቃር ደም መቀባባት መቀነስ ይቻላል የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ምህረትም አንዱ የትግል ስልት ነው ፡ በትንሹም በትልቁም ያስከፋንን እንግደል ካልን ጠላታችን ከሩቅ ሳይሆን ከጎናቸን ነው የሚፈለፈለው ፡፡ አማራ የዘመን በደሉን አይረሳም ፡፡ በኪነጥበቡ ( በግጥም፡ በዘፈን ፡ በእጉርጉሮ፡ በድርሳናት ) ታሪኩን ከትውልድ ወደ ትውልድ ያስተላልፋል፡፡ ለምሳሌ መላኩ ተፈራ የአምላክ ታናሽ ወንድም ፡ ይህንን ማርልኝ ደግሜ አልወልድም፡፡ ይህ ስንኝ የመላኩን ማንነት ብቻ ሳይሆን የነበረውን ግፈኛ ስርአት በሕዝብ ልጆች ላይ የደረሰውን በደል እና ሰቆቃ የሚያስታውስ ነው ፡፡ አንድ ልጨምርላችሁ : ጠጅም እንዳያምረኝ ድሮ ጠጥቻለሁ ፡ ሥጋም እንዲያምረኝ ቋንጣ ስቅያለሁ ፡ ቢሻን ከወንድሜ ካባቴ እበላለሁ ፡፡ በአፄ ቴድሮስ ዘመን የተገጠመ ነው አሁን ይታወሳል፡፡ ስለሆነም ፋኖ የሕዝብ ልጅ ነኝ ብሎ ከወጣ ድረስ የራሱን ሕዝብ ስነ ልቦና ጠንቅቆ ማወቅ አለብት ፡፡ የአቤ ጉበኛ አልወለደም የብሶት ድርሳን ነው፡፡
አሁን በቅርቡ በመንግስት ድሮውን ጥቃት ተስውተዋል የተባሉት አባት አርበኛ ፋኖ ተስፋዬ መካሻ በተመለከተ ዘመንድኩን በቀለ ( ብንወደውም ብንጠላውም ፡ ብንስማማም ባንስማማም) ያወጣው መረጃ እጅግ የሚረብሽ እና ማብራሪ የሚያስፈልገው ነው ፡፡ ይህን የሰሞኑን ጉዳይ ስናነሳ ከእዚህ ቀዳም ለአገዛዙ ተላልፎ የተሰጠውን አርበኛ ፋኖ አስገድ መኮንን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ተደጋግመው በተለዩ መንገድ ፡ የሚገለፁ የፋኖ ድክመቶች ( በመረሸን፡ በሞት፡ አሳልፎ በመስጠት፡ በመካድ ወዘተ) መልስ ሊሰጥባቸው እና ሊታረሙ የሚገባቸው ድርጊቶች ናቸው ፡፡ እነዚህ ነገሮች ተደጋግመው ከተከሰቱ የሚመለከተው አመራር ተጠያቂ መሆን መቻል አለበት፡፡ ይህን በተመለከት በእዚህ በኩል ስማቸው የተጠቀሱት የፋኖ አመራሮች የፋኖ ደጋፊዎች ጉዳዩን በዝምታ ሊያዩት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ይህንን የመሰለ መረጃ ነው መንግስት በአዳባባይ የአማራን የሕልውና ትግል የሚያሳንሰው ፡ የሚያዋርደው ፡፡ አሳውን ከባሕሩ ለማውጣት የሚጠቀምበት፡፡ አንዴ አሳ ከባሕሩ ከወጣ የሚከተለውን ሁላችንም እናውቃለን፡

ዛሬ በትግል ስም የምናደርጋቸው እያንዳዱ እርምጃ በታሪክ የምትመዘገብ ግን ቀን ቆጥራ ዋጋ የምታስከፍል ወይም ክብር የምታስጥ ትሆናለች ፡፡ በክልሉ ከሰሞኑ የተደረገው ውይይት በከፊል ያሳየው ይህንን እውነታ ነው ፡፡ የቀድሞ ወዳጅህን በምን ቀበርከው ቢሉት በሻሽ የኋልኛው አዳይሽሽ አለ አማራ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ማንም አካል ጠማንጃ ማንሳት ይችላል፡፡ ቃታም፣ መሳብ ይቻል ይሆናል ፡፡ የመጨረሻ እውቀት ጥረት እና ጥበብ የማያስፈልገው ሥራ ቢኖር ቃታ መሳብ ነው፡፡ እውቀት ፤ጥበብ፤ ትግስት እና ማስተዋልን የሚሻ ሥራ ቃታን መመራት ነው፡፡ በተጨማሪም እና በዋናነት ጠመጃ ማንሳቱ እና ቃታ መሳቡ ውጤቱ የሚለካው ካለው ሕዝባዊነት ነው፡፡ ለሕዝብ መብት እና ደህንነት ያልቆመ ጠመንጃ ከጠላት ጠመንጃ ተልይቶ አይታይም ፡፡ ለመልካም ምግባር እና በመልካም ስም ተነሰተው ሕዝባቸውን የጨረሱ ያስመረሩ ትግላቸውን የቀለበሱ ትግሎች በዓለማችን ተከስተዋል ከእዚህም ውስጥ አንዱ በፖል ፖት የተመራው የካቦዲያው የማርክሲስት አብዮት ነው፡ ለሕዝብ በሕዝብ ስም የመጣው የካምቦዲያ አብዮት ከ1.5 ሚሊዮን ሕዝቦችን ነፍስ አጥፍቷል፡፡ ወደ አገራችን ስንመለስ የደርግ የአለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ብሎ ኢትዮጵያን ደም በደም አድርጎ አልፏል፡፡ ወያኔ በትግል ስም ብዙ ሰዎችን ቆርጥሞ በልቷል ፡፡ በትጥቅ ትግል ውስጥ ከሕዝባዊነት ወደ ፀረ ሕዝባዊነት ለመሽጋገር መስመሩ በጣም ቀጭን ነው ፡፡ ለእዚህ የሻቢያን ታሪክ መጠቀሱ በቂ ነው ፡፡ ኤርትራን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ሕዝብን ለባርነት የዳረገው የ30 አመት ትጥቅ ትግል የተከናወነው በሕዝብ ስም መሆን መዘንጋት የለብንም፡፡ ዛሬ የኤርትራ ሕዝብ ያለበትን ሁኔታ እራሱ ሕዝቡ ያወቀዋል ፡፡ ዛሬ ትላንትና በባርነት አንቃ ይዛናለች ባሏት ኢትዮጵያ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በስደተኝነት በስላም እንዲኖሩ ተገዳዋል ፡፡
ይህን ፅሁፍ አጠናቀሪ ከጨረስኩኝ በኋላ በቢቢሲ አማርኛው ክፍል የወጣው ዜና አስደጋጭ ብቻ ሳይሆን አነጋጋሪም ስለሆነ ዘገባውን ለማካተት ተገድጃለሁ፡፡ ዜናው እንዲህ ይላል “በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ በሚገኘው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ሦስት ወጣት ሴቶች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ተገድለው ተገኙ። ድርጊቱ መፈጸሙን ለቢቢሲ ያረጋገጡት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አስረስ ማረ ዳምጤ፤ ሦስቱ ሴቶች “ለጠላት ሲሰልሉ በመገኘታቸው እርምጃ መወሰዱን” በመጥቀስ እርምጃውን ተከላክለዋል።” ይህ ሊብራራ የሚገባው ጉዳይ
ፋኖ በትጥቅ ትግል ያሳካውን ድል ያህል በፖለቲካው ትግል ግማሹን ያክል አላሳካም ፡፡ ይህ የፋኖ ከፍተኛ ስብራቱ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ፡፡ ለእዚህ ስብራት ዋንኛ ተጠያቂው አኩራፊው ብአዴን ሲሆ ሁለተኛው ተጠያቂወ ተስፈኛው የአማራ ቴክኖክራት (Technocrat) ነው ፡፡ አኩራፊውን ብአዴንን በተመለከተ በአንድ ምሳሌ ላስረዳ በአንድ የፖለቲካ ስብስብ ላይ አንድ የአኩራፊው ብአዴን ደቀ መዝሙር የሆነ ሰው እንዲህ አለ እናተ ( አብዛኛው ዲያስፖራ ነው) በፖለቲካ መስክ የእገሌን ጥፍር ቁሻሻ አታክሉም ብሎን አረፈው (እገሌ የተባለው ሰው የብአዴን መአከላዊ ኮሚቲ አባል ነበረ) ፡፡ ያ እግሌ የተባለው ሰው ዛሬ በአብይ እስርቤት ይማቅቃል፡፡ ከብአዴን የፀዳ አዲስ የፖለቲካ መስመር እና አደረጃጀት እንዳይኖር ያደረገው ይህ አብይ ለመተካት ያሰበው ኃይልና ስብስብ ነበር ፡፡ በእነሱ ግምት ትንሽ ጥይት በማስጮህ ስልጣንን ከአብይ እንቀማለን የሚል እምነት ነበራቸው፡፡ የአብይም መልስ እኛ (ብልፅግና/እኔ) ወደ ስልጣን የመጣንበትን/በመጣሁበት መንግድ ስልጣኔን አትቀሙኝም ነው ፡፡ በእዚህም ስሌት የሚገድለውን ገድሎ፤ የሚያስረው አስሮ፤ የሚያባርረውን አባሮ ፡ የሚያስገድለው አስገድሎ ፡ የሚያስድደውን አሰድዶ አሁንም በስልጣን ላይ አለ፡፡ አኩራፊው ብአዴን ይህን ስህተቱን አያምንም አሁንም በስደት ያሉ የተረፉ ብአዲናዊያን ከእዚህ ቀደም የሰሩትን ስህተት ለመስራት ሲዳክሩ ይታያሉ ፡፡
በውጭ እና በውስጥ ባሉ የአማራ ቴክኖክራት (Technocrat) እና ተሰፈኞች የአብይን መንግስት ከአኩራፊው ብአዴን እና ትጥቅ ባነሱ ፋኖዎች በትንሽ ግርግር ማስወገድ ይቻላል ብሎ ያመነና አብይ አፍንጫ ስር ተቀምጦ አብይ በሚያዘው በሚቆጣተረው ኢትዮ ቴሊኮም ስለ ትግሉ መረጃ ሲለዋወጥ የሚውል፡ በሚዲያ እየቀረበ የሚናገር አብይን የሚያወግዝ ነበር፡ በፖለቲካው እይታ ይህ ስብስብ የትግል ዲስፕሊን ያልነበረው ነበር፡፡ በሕቡ መደረግ የነበረበት ትግል የንግድ ተቋም በማቋቋም ፡ የመረዳጃ ማህበራት በማቋቋም ነገሩ የገባውም ያለገባውንም በማጃበል የተከናወነ ነበር ፡፡ ይህ የአምባ ገነኖችን ባህሪ በቅጡ ካለማወቅ ፡ ካለመረዳት ፡ ከታሪክ ካለመማር ፡ በግብዝነት እና ከማን አላብኝነት የሚመጣ ችግር ነው ፡፡ ኢሕአፓ ፡ መኢሶን አፈር ከድሜ የገቡት የመንግስቱ ኃለማሪያምን መንግስት ወይም ወታደራዊ መንግስትን ባሕሪ ባለመረዳታቸው የመነጨ ነው ፡፡ በሌላ አንጋገር የተኩላን ግልገል ውሻ ነው ብሎ እንደ ማሳደግ አይነት ነው ፡፡ የአማራው ቴክኖክራት እውቅት ንባብ አንሷቸው አይደለም ግን የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የትም አይደርስም ብሎ በመናቅ ያመጡት ሽንፈት ነው፡፡ በመንግስቱም ዘመን ወታደሩ ምን ያውቃል ከሚል አጉል የሙህራን ግብዝነት የመነጭ ብዙ ሙሁራኖች ተበለተዋል ፡፡ እንዳልኩት የጠመጃ ቃታ ለመሳብ ዶክትሪት አያስፈልገውም ወይም ፕሮፎሰር መሆን አይጠቅም ፡፡ ብዙ የኢትዮጵያ ፖለቲካኞች ያለተረዱት የማይረዱት ይህንን እውነታ ነው ፡፡ በነገራችን ላይ የቅንጅትም ውድቀትም ምንጩ ተመሳሳይ ነው ፡፡ ከጫካ የመጣችው ወያኔ የመሃይም ጥርቅም ነች ምን ታመጣለች እኛ ዶክተር ፕሮፌሰር ኢንጂነር ተመራጮች አሉን ብለው ገቡበት ፡ ግን ያ ከጫካ የመጣው የጨነቀው እለት ቃታ እንደሚስብ አልተረዱትም ፡፡ የትግል ውድቀት መጀመሪያ ጠላትህን አሳንሶ ማየት ነው ፡፡
የአገዛዙ የአድኑኝ ጥያቄ እና የሕዝብ መልስ
እንግዲህ ከላይ የጠቀስኳቸው እፀፆች ናቸው ዛሬ ፋኖ ለደረሰበት አንዳድ ስብራቶች ያደረሱት ፡፡ ሰሞኑን አገዛዙ ካድሬዎቹን በየ ወረዳው በየ ቀበሌው በመላክ ሕዝባዊ ስብሰባ በማደርግ ፋኖን በፅንፈኝነት ማወገዝ ብቻ ሳይሆን በወጀለኛነት፡ በዘራፊነት ፡ በሴት ደፋሪነት ፡ በንብረት ዘራፊነት ፡ በካዳተኝነት ፡ በባዳነት ፡ ወዘት ሲከስ ሲወግዝ እን ሲያሶግዝ ተደምጧል ፡፡ እዚህ ላይ ሕዝብ ተስብስቦ የተናገረው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ማለት አይቻልም ፡፡ ነገር ግን ከሶስት ሚሊዮን በላይ የአማራ ካድሬ ያለው ብልፅገና በሕዝብ ውስጥ ገብቶ ሕዝብ መስሎ አይናገረም ማለት አይቻልም ፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በቅጡ ለመረዳት ፓሪቶ ኤፊሽንሲ (Pareto efficiency) ወይም 20/80 ትንተናን እንጠቀማለን ፡ ወይም ትንሽ ቆሎ ይዘህ ከአሻሮ ተጠጋ የሚለውን ብሄል እንጠቀም፡፡
ሲጀመር ፡
- ፋኖ የመልአክት ስብስብ አይደለም በትግል ውስጥ ስህተት ሊፈፅም ይችላል
- መንግስት ተብዬው እና አገልጋዮቹ አማሮችም ቢሆኑ ፋኖን ለማስገደል ላማስወገድ ተግተው ይሰራሉ፡
- የትጥቅ ትግል ውስጥ መንግስት ፋኖ አስመስሎ የራሱን ሰዎች ያስገባል ወንጀልም ያሰራል
- የመንግስት የፅጥታ ኃይሎች ወንጀል ሰርትው ፋኖ ነው ሊሉ ይችላሉ (A “false flag mission” (or operation) is a covert action designed to look like it was carried out by another group, shifting blame and creating pretext for conflict
- ከፋኖ ውስጥም አቀመ ደካማ ወይም እልኸኛ ይኖራል
- በፋኖ ትግል ውስጥም ወንጀለኛ ሊኖር ይችላል
- በፋኖ ስም ወንጀል ሊሰሩ የሚችሉ አካላት ይኖራሉ
የእነዚሁ ሁሉ ድምር ውጤት በፋኖ ትግል ውስጥ ትቁር ነጥብ ሊጥሉ የሚችሉ ድርጊቶች ሊከሰቱ ይችላሉ ተከስተዋልም ፡፡ ከእዚህም በተጨማሪ የአገዛዙ ካድሬዎች በሕዝብ መሃል ቆመው ያለተደረገው ተደረገ ብለው ፋኖን እንዲያወግዙ አቅጣቻም ተቀምጦላቸዋል፡፡ ይህ የአካድሬ አሰራር ከ66 አብዮት በኋላ በኢሕአፓ እና በመኢሶን አማካኝነት ከውጩ ዓለም ከማርኪሲዝም እርዮተ አለም ጋራ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው ፡፡ ወያኔ፡ ግንቦት 7 ሁሉ በሰፊው ተጠቅመውበታል ፡፡ አሁን 20/80 የሚለውን ስሌት ስናመጣ በፋኖ ትግል ውስጥ ተፈፀሙ የተባሉት ስህተቶች 20% ቢሆን መንግስት ይህን 80% አድርጎ ፋኖን ከሕዝብ ለመነጠል የፕሮፓጋንዳ ወይም የአውጫጪኝ አይነት ስራ በመሳራት ላይ ይገኛል ፡፡ የሰሞኑ የቢቢሲ ዘገባም ይህን ያጠናክራል፡፡ ይህን በተመለከት ከተደረጉ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ውስጥ አንድ ወዳጄ እንድመለከተው እና መልስ እንድሰጥበት ከላከልኝ ቪዲዎች ውስጥ በሰሜን ሜጫ መራዊ ከተማ ፡ በደቡብ ሜጫ መሐል ገነት ከተማ፡ የኪንፋዝ በገላ ወረዳ የሕዝብ ውይይት እና የሕዝብ ውይይት በሐይቅ ከተማ በጥሞና ተመልክቸዋለሁ አድምጬዋለሁ፡፡
ውይይቱ ሁለት ይዘት ያለው ሲሆን አንዱም ልመና ሌላውም በስም ማጥፋት የታጀበ ማስፈራራት ነው ፡፡ ይህ የመንግስት ድርጊት ሁለት ነገሮችን ሊያሳየን ይችላል ፡
- አገዛዙ በፋኖ ትግል ውጥረት ውስጥ መግባቱን የሚያሳይ ነው ፡ ምክኛቱም ያልተመታ አይጮህም እና
- ሁለት የፋኖ ትግል ሕዝባዊ መሆኑን የሚያሳይ ነው ፡ ፋኖ የሕዝብ አካል ባይሆን ሕዝብን አያወያይም
መንግስት በጦር ሜዳ አሸናፊ ቢሆን ኖሮ ቀበሌን ሰብስቦ ልጆቻችሁን አንድ በሉልን መልሱልን አይልም ነበር ፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ፋኖ አሳ ቢሆን ባሕሩ ሕዝቡ ነው ፡፡ በመንግስት የተሞከረው ሙከራ አሳውን ከባሕሩ አውጡት የሚለው ነው ፡፡ በእርግጥ አገዛዙ አንዳንድ ክስተቶችን በማንሳት የፋኖን ቅቡልነት ለመቀነስ ፡ ብሎም ለማጥፋት ጥረት አድርጓል ነገር ግን ከሕዝቡ የተሰጠው ምላሽ አገዛዙን ከማበሳጨቱም በላይ ውይይቱን ፍሬ አልባ አድርጎታል ፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ፡ የክልሉ መስተዳደር ባለበት የመሐል ገነት ከተማ ውይይት ፡ የክልሉ መስተዳዳር እንዲህ ብለዋል “አንዳዶች ፈርታችሁ እጃችሁን ካወጣችሁ በኋላ ልማት ልማት ልማት ልማት ብላችሁ ደሞ በልማት ዙሪያ አውርታችሁ ዋናወን ችግራችሁን ሳትነኩት መሄድ የምትፈልጉ ሰዎች አላችሁ” ከእዚህ ንግግር እንደምንረዳው በሕዝቡና በመንግስት ተወካዮች መካክል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ ነው ፡ እንዲያውም ከእድምተኞቹ የመጀመሪያ ተናጋሪ የሆኑት አባት ንግግራቸው የከፈቱት በመንግስት እና በሕዝብ መካከል መቀራራርብ እንደሌለ በማሳየት እንዲህ ተናገሩ ፡ “ምናልባት በሩቅ የምናያችሁ በቅርብ ማናገኛችሁ የክልላችን አስተዳዳር እና የዞናችን አስተዳዳር” ይህ ቀላል መልእክት ይደለም፡ እሳቸው በግልፅ ያሳዩት አንተዋውቅም ዛሬ ከየት መጣችሁ ነው ያሉት ፡፡ እኝሁ ሰው ናቸው ስለ ልማት ያነሱት በተለይ ከወተት አባይ አሲናት ስትመጡ ያያችሁት መንገድ ብለው ስለ መንገዱ መበላሸት እና ከአገልግሎት ውጭ ስለመሆኑ አስረዱ ፡፡ ፋኖዎችን በተመለክተም እነሱም ልጆቻችን ናቸው በጉዳዩ ላይ ቀርበን መወያየት አለብን ብለው ተናግረዋል ፡፡ እዚህ ላይ ሁሉን ውይይት መተንተን አልችልም ግን ወደ ሐይቅ ጎራ ብዩ አንድ ሁለት ልበል ፡ የሐይቅ ሕዝብ በእዚህም በዛም ሰላም ይምጣ የሚል መልእክት ነው ያስተላለፈው ፡፡ በግጥም በታጀበው አነጋገራቸው ብሶታቸውን ያስሙ እናት በተለይ በእናት ላይ ያለውን ድርብ ድርብርብ ሰቆቃ እንዲ ብለው ገልፀውታል፡ እኔው ተሳስቼ እኔው ዘንጋ ብዬ ወንድሙ ወንድሙን አይገልውም ብዬ ብላ እናት በሐዝን ላይ ነች ብለዋል ፡፡ ይህ ለአገዛዙም ቢሆን ለፋኖ ትልቅ ትምህርት ነው፡ ፋኖ በምንም አይነት መልኩ በወንድሙ አማራ ላይ ብአዴንም ወይም ወሬ አቀባይም ቢሆን የመጀመሪያው እርምጃ ቃታ መሆን የለበትም የሚል መልእክት ነው ያለው ፡፡ እኝሁ እናት በሌላ ስንኛቸው ባዝላት እምቢ አለችኝ ባሽሞነሙናት ፡፡ አስባለች መስል በሆዷ ክዳት ብለዋል ፡፡ ይህ አባባላቸው ሁለት ስላት ያለው ቢላዋ ነው ፡፡ የአማራ ሕዝብ አብይን አዝሎታል አሽሞንሙኖታል፡ ነገር ግን እዛው ወሎ ላይ የክህደቱን ቃል እንደተናገረ አስታውሳለሁ ፡፡ ለሥራ የምሰጣቸውን ባጀት ለልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ተጠቀሙበት ባለ በማግስቱ ነው እነ ዶር አምባቸው የተገደሉት፡፡ በሌላም በኩል በሕዝባዊ ስብሰባውም ሆነ በተለይ በሐይቅ በተደረገው ውይይት ያየሁት ፋኖ በበቂ ሁኔታ ድርጅታዊ እና ፖለቲካዊ ሥራ አለመስራቱን ነው ፡፡ የወሎ ፋኖዎች ብዙ የቤት ሥራ ይጠብቃቹሃል ፡፡ ይህ ቢሰራ ኖሮ የአገዛዙን ካድሬዎች ፍትሃዊ በሆኑ ጥያቄዎች ብቻ አፍር ከደሜ በማስገባት መድረኩን መቆጣጠር ይቻል ነበር ፡፡ ባየኋቸው ውይይት ውስጥ በአማራ ላይ ስለሚደርሰው ግፍ እና በደል አንድም ጥያቄ ውይይት አልተነሳም ፡ በክርስቲኖች ላይ ስለሚደረስው ግፍና በደል ምንም አልተባለም ፡፡ እርግጥ ይህ ውይይት 80% የአገዛዙ ካድሬ የሞላበት ዙሪያውን በጠመጃ የተከበበ የአፈና ውይይት ነው አላማውም ፋኖን ከሕዝብ ለመነጠል ነው ፡፡ የጭንቀት አስታርቁን መልሱልን ውይይት ነው ፡፡
ፋኖ ከእዚህ ምን ይማራል
በጀመሪያ ደረጃ ማወቅ ያለብን ቃታ መሳብን እውቀትን ጥበብን ማስተዋልን የማይፈልግ ቀላል ጉዳይ ነው ፡ አንዴ ቃታ ከተሳበ የወጣውን ጥይት ማስቆም አይቻልም፡፡ አንዱ ቀላሉ ነገር አሁንም ጥበብ እውቀት እና ማስተዋልን የማይጠቅ ነገር ሰው መግደል ነው፡፡ ስውን መግደል ጀግና አያደርግም ጀግናም አያሰኝም ፡፡ ሰውን ለማጥፋት ጠማጃም አያስፈልግም ፡፡ ቃኤል ወንድሙን አቤልን የገደለው በድንጋይ ነው ፡፡ ትልቅ እውቀት ጥበብ ማስተዋል እና ትእግስት የሚሻው ከላይ የጠቀስኩትን በተቃራኒው ማድረግ ነው ፡፡ እውቀት፡ ጥበብ፡ ማስተዋል እና ታጋሽነት ቃታውን ማዘዝ አለበት ፡፡ ይህን ለማድረግ ግልፅ የሆን አላማ፡ ግብ፡ እራዕይ ፡ ሕዝባዊነትን ያነገበ የፋኖ አደረጃጀት ያስፈልጋል፡ ትግሉም ሆነ ጠመጃው መመራት ያለበት መርሆ ባለው ፖለቲካዊ ድርጀት ነው ፡፡ ይህ መርሆ ያለው ፖለቲካዊ ድርጀት ከውጭ ተሰርቶ ለፋኖ መቀርብ የለበትም ቢቀርብም አይከፋም ፡፡ ግን እዛው መሬት ባሉ ፋኖዎች መሰራት ይቻላል፡፡ ፋኖ እራሱን እዚህ ሃላፊነት ብቆ ማድረግ መቻል አለበት ፡፡ ገጥመናል ገጥማናል ብቻ ሳይሆን የገጠምነው በጠመጃ ብቻ ሳይሆን በእውቀት ፡ በአደረጃጀት፤ ንቃተ ሕሊና፤ በፍትሃዊነት ፡ ከጠላቶቻችን በልጠን ወይም ተሽለን ስንገኝ ነው፡፡ ጠላቴን በእሳት አቃጥለዋለሁ በሚል ንግግር አይደለም ፡፡ መፅሃፍ ቅድሱ አንድ የሚያስተምረን ነገር አለ ( በተለይ አንገታቸው ላይ መሃትም ደረታቸው ላይ መስቀል አድርገው ለሚታገሉ ወንድሞች ) እንዲህም ይላላ የማቲዎስ ወንጌል 12፡ 33 ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ። 34 በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።35 መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
እንግዲህ ወንድሞቼ ትግል አስከፊ የሞት እና የድል ጉዞ ነው ፡ ትግሉ ያለው በሕይወት እና በሞት መካካል ነው፡ ከትግሉ አጀማመር አንፃር የፋኖ አሁናዊ አቋም በአወንታዊነት የሚታይ ነው ፡፡ ነገር ግን ብዙ ሥራ መስራት ይጠይቃል ፡፡ መታረም የሚገባቸው ድርጊቶች በግዜ መታረም አለባቸው ፡፡ መዘመን የሚገባው ትግል መዘመን ይገባውል ፡፡ ወቅቱን ያዋጀ የውስጥ እና የውጩን ፖለቲካ የተነተነ ትግል ያስፈልጋል፡፡ የገጠመን ጠላት አንድ አይደለም፡ የአማራ ሕዝብ እንደ ገና ዳቦ ነው ከላይም ከታችም እሳት እየነደደበት ነው ፡፡ ከውጥም ከውጭም ነው ጠላቶች ያሉት፡፡ ይህ ሁሉ ባለበት ሁኔታ ትግሉ ከግቡ ለማድረስ ትእግስት ፡ እውቀት፡ ጥበብ፡ ብልሃት ፡ ፍትሃዊ እና ቆራጥ አመራር ያስፈልገዋል፡፡ ይህን እንዲረዳ የራሴን እሳቤ በሰንጠረዥ አቅርቢያለሁ ፡፡ ይህ ሰጠረዥ ሙሉ ነው ማለት አይደለም ፡፡ ሌሎች ወገኖች ጨምሩበት ፡ አዳብሩት ፡ ፋኖውችም እስካሁን የሰራችሁት ሥራ እንዳለ የሚታወቅ ቢሆንም በሰጠረዡ መሰርት ያለውን አጠናክሩ የጎደልውን ሙሉ ፡፡

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






