
ቦርከና
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ከሰጠች በኋላ የመጀመሪያውን የከፍተኛ ባለስልጣናት ጉዞ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ ጧት የሶማሊላንድ መዲና ሀርጌሳ መግባታቸውን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አይ 24 የሶማሊላንድ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ፣ ጌዲዮን በቆይታቸው ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዱላሂ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘግቧል።
ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉት ውይይቶች እና ስምምነቶች በመግለጫው እንደሚነሱ ዘገባው ጠቁሟል።
ጉብኝቱ በእስራኤል እና በሶማሊላንድ መካከል ያለውን ፖለቲካዊ እና ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነው እንደሆነ ተመላክቷል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ የነጻ ሀገርነት እውቅና ከሰጠች በኋላ በከፍተኛ የእስራኤል ልዑክ ወደ ሀርጌሳ ሲያመራ የመጀመሪያ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረግ ጥረት አካል ነው ተብሏል።
በተያያዘ መረጃ ሶማሊላንድ ለጅቡቲ አየርመንገድ የሰጠችውን ፍቃድ መሰረዟን አስታውቃለች።
ሀርጌሳ የኤር ጅቡቲን ፍቃድ የተነጠቀችው እስራኤል የሰጠችውን እውቅና ውድቅ በማድረጓና ለሶማሊያ በመወገኗ ነው ተብሏል።
ኤር ጅቡቲ በሳምንት አራት ቀን ወደሶማሊላንድ በረራ ያደርግ እንደነበር ተገልጿል። ስማቸው ያልተገለፀ አንድ የሶማሊላንድ ባለስልጣን “የአቪየሺን አገልግሎት በሁለትዮሽ መከባበርና ትብብር ላይ የተመሰረተ ነው” ብለዋል።
ባለስልጣኑ “ያ መርህ ካሁን በኋላ አይቀጥልም” ሲሉ ገልፀዋል። ሁለቱ ሀገራት ባሳለፍነው ሳምንት አምባሳደሮቻቸውን ወደሀገራቸው በመመለስ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል ተብሏል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ : ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






