
ቦርከና ዜና
በፌደራል ደረጃ ከተመዘገቡ 470 ሺህ የንግድና የአገልግሎት ሰጭ የግል ድርጅቶች ውስጥ 370 ሺህ የሚሆኑት፣ በገጠማቸው ተግዳሮት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ምክንያት ከፌደራል መዝገብ ተሰርዘዋል ተብሏል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በባለሙያዎች ያካሄደው ጥናት በ2024 የፈረንጆች አመት ውስጥ ከ370 ሺህ በላይ ድርጅቶች ከፌደራል መዝገብ መሰረዛቸውን ይፋ አድርጓል።
በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የንግድና አገልግሎት ሰጭድርጅቶች ቁጥር ከ100 ሺህ እንደማይበልጡ የሪፖርተር ዘገባ ያመላክታል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሙሼ ሰሙ ጥናቱ ቁጥርን ከመዘገብ ባለፈ ድርጅቶቹ የገጠሟቸውን ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች አጥንቶ ያመላከተ መሆን ይገባው እንደነበር ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ ያስጠናው ጥናት የእነዚህ ድርጅቶች ስራ ማቆም የስራ ዕድል መጥፋት፤ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የመንግስት ገቢ እንደሚቀንስና ከአገልግሎት አሰጣጥና አቅርቦት አኳያም የምርት አቅርቦትና ስርጭት ሚዛንን እንደሚያዛባ ተመላክቷል።
ሙሼ የድርጅቶች በዚህ ደረጃ መዘጋት የመንግስት ገቢን በመቀነሱ ምክንያት በቀሩት ጥቂት ድርጅቶች ላይ የሚያሳድረው የግብር ጫና በሒደት ቀሪዎቹንም ከገበያ ሊያስወጣ የሚችል ክስተት መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚገባ ነው ብለዋል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ባለሙያዎች ተጠንቶ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በፌደራል ደረጃ ተመዝግበው ከሚገኙና በተለያየ ሙያና ዘርፍ ከተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች መካከል 80% የሚሆኑት እንደተዘጉ በጥናቱ ተረጋግጧል።
ለረጅም ዓመታት ፈጣን እድገት በማሳየት 470 ሺህ ደርሰው ከነበሩት በፌደራል ደረጃ የተመዘገቡ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች መካከል 370 ሺዎቹ በ2024 መዘጋታቸውን በዘገባው ላይ አክሏል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አክለውም በፌደራል ደረጃ በስራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች መካካል የተዘጉት 80% መሆናቸው አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ : ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






