
ቦርከና ዜና
የአለም ጤና ድርጅት በበኩሉ አሜሪካ ያለባትን 260 ሚሊዮን ዶላር የአባልነት መዋጮ አለመክፈሏን አስታውቆ እንድትከፍል አሳስቧል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ አመት በፊት አሜሪካ ከድርጅቱ እንድትወጣ መፈረማቸውን ተከትሎ ነው መውጣቷ የተገለጸው።
ነገርግን ሀገሪቱ ከ2024 ጀምሮ መክፈል የነበረባትን 260 ሚሊየን ዩሮ አለመክፈሏን የአለም ጤና ድርጅት (WHO) አስታውቋል።
የድርጅቱ አባል ሀገራት በአሜሪካ መውጣት ዙሪያ ከቦርድ አመራሮች ጋር ለመምከር በቀጣይ ወር ቀጠሮ መያዛቸውን ፋርማ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) እንደምትወጣ የተናገሩት በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ቢሆንም፣ በ2020 በምርጫ መሸነፋቸውን ተከትሎ የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ውሳኔያቸው ተሽሯል።
ነገርግን ትራምፕ ዳግም ወደስልጣን ከተመለሱ በኋላ አሜሪካ ከዓመት በፊት በሰጠችው ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሠረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል ከሆነው የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) አባልነት በይፋ ለቅቃ ወጥታለች።
ፕሬዝዳንቱ ሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸውን በጀመሩበት ዕለት ካስተላላፏቸው የአመራር ውሳኔዎች መካከል አንዱ የሆነው ከዓለም ጤና ድርጅት መውጣት ተግባራዊ ሆኗል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከሚገኘው የዓለም የጤና ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት እንዲነሳ ተደርጓል።
ከዚህ በኋላ አገሪቱ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ውስን እና ከተቋሙ መውጣቷን ለማጠናቀቅ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት የጤና ባለሥልጣን በድርጅቱ ውስጥ በታዛቢነት የመሳተፍም ሆነ መልሶ አባል የመሆን ዕቅድ የለንም ሲሉ ተናግረዋል።
ነገርግን ከአሜሪካ ጤና እና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቶች በጋራ በወጣው መግለጫ መሠረት ከዚህ በኋላ አገሪቱ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ውስን እና ከተቋሙ መውጣቷን ለማጠናቀቅ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን ተጠቅሷል።
ሀገሪቱ በበሽታዎች ቁጥጥር እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው በሌሎች የኅብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ላይ በዓለም አቀፍ ድርጅት በኩል ሳይሆን በቀጥታ ከአገራት ጋር ለመሥራት አቅዳለች።
በኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የሚመራው እና ከ190 በላይ አገራትን በአባልነት ከያዘው ተቋም አሜሪካ ለመውጣት መወሰኗ በአሜሪካ እንዲሁም በቀሪው የዓለም ክፍል የሚከናወኑ የጤና ሥራዎችን እንደሚጎዳ ተገልጿል።
ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ከዚህ ቀደም ለትራምፕ ውሳኔ በሰጡት ምላሽ እርምጃውን ኮንነው መልሰው እንዲያጤኑበት አሳስበው ነበር።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግን በ2019 በተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ዶክተር ቴዎድሮስ የሚመሩት የአለም ጤና ድርጅት በሽታው በተከሰተበት የቻይና ውሃን ከተማ ምርመራ ባለማድረጉ ተጠያቂ አድርገውታል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ የሚጠበቅበትን አላከናወነም በሚል ከድርጅቱ ለመውጣት ወስነው የነበረ ቢሆንም በጆ ባይደን በመሸነፋቸው ተግበራዊ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል።
አሜሪካ እራሷን ያገለለችው ከዓለም ጤና ድርጅት ብቻ ሳይሆን ትራምፕ በቅርቡ 70 ከሚደርሱ የመንግሥታቱ ድርጅት አካላት ከሆኑ ተቋማት ለመውጣት ውሳኔ አሳልፈዋል።
በተጨማሪም የሰላም ቦርድ በማለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያስተዋወቁት ስብስብ የተባበሩት መንግሥታትን ሚና የሚያዳክም ነው በሚል ትችት እያስተናገደ ይገኛል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






