Homeመጽሐፍትመመለስን እንዳነበበኩት

መመለስን እንዳነበበኩት

Advertisement
World Wide Travel Group
መመለስ  ብርቱካን ሚዴቅሳ

የመፅኀፍ ርእስ   መመለስ
ደራሲ  : ብርቱካን ሚደቅሳ
አሳታሚ : ሮሆቦት አታሚዎች
የገፅ ብዛት : 292

በቶፊቅ ተማም

መግቢያ

የተወለዱት በአዲስ አበባ ፈረንሳይ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የመጀመርያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ሀለተኛ ድግሪያቸውን ከሃርቫርድ የኒቨርሲቲ በህዝብ አስተዳዳር ወስደዋል የአንዲት ሴት ልጅ እናት የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካ ሚደቅሳ በፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዳኛ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳትም ነበሩ በዳኝነትም ይሁን በፖለቲካው መስክ ትልቅ ስም ያላቸው ወ/ሪት ብርቱካ በኢትዮጲየ ህግ የበላይነት እንዲከበር በከፈሉት መስዋአትነት እና በጥንካሬአቸው  በአርአያነት ሲጠቀሱ በያዝነው ወርም መመለስ የሚል ርእስ የሰጡትን መጽሀፍ በታላቅ ድምቀት አስመርቀው ለገበያ አቅርበዋል  ‹‹ስራ ከጀመርኩበት ከ 1989 ጀምሮ የአደባባይ ሰው እንደመሆኔ መጠን የህይወት ታሪኬን የመፃፍ ጉዳይ በጉትጎታም በምክርም አስታኮ የመጣብኝ ጊዜያት በርካታ ናቸው ››  ገፅ 1 የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ  በመፅሀፍ ልፃፍ አልፃፍ በእውኑ ለመፅሀፍ የሚሆን ታሪክ አለኝ ወይ ምን ተሰራና ይፃፋል በሚል ሀሳብ  ይቸገሩ የነበሩ ሲሆን በዚህም መሀልም መፀሀፍ ለመፃፍ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አሳልፈዋል ፡፡

የከሸፈ ሙከራ

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

መፅሀፍ ለመጻፍ አስበው ባቀዱት መሰረት ለማፃፍ መንገድ ጀምረው የከሸፈባቸውን መንገዶችን አስፍረዋል ‹‹መጀመርያ በስደት በሄዱበት እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በተማሩበት ወቅት በተለይ እዛ ካለ አሜሪካዊ ፕሮፌሰር እና ባለደረቦቻቸው  ያካፈላቻቸውን የህይወት ታሪኳን መሰረት በማድረግ ወደ ዶክመንተሪ ከዛም ወደ መፅሀፍ እንዲመለስ ቢጠይቋትም አልፈቀደችም ለዚህም መልሷ ‹‹ በኢትዮጲያ የፖለቲካ ሰፈር ያደረኩት ሁሉ አገለግል ብየ አገልግየም በኢትዮጵያም የህዝብ አስተዳደር ለገዥ ሳይሆን ለዜጋ ያደላ ነገረ ስርአት አመጣ ያቅሜን አዋጣለሁ ብየ የወደድኩትን ህልሜን ወደ አውነታ ለማስጠጋት መጣሬ አልቀረ…ሆነው ግን ፍፁም ሌላ  ታዲያ ይሄ  ህይወት ምኑ ይፃፍለታል  የስቃይ እና የመከራ ታሪክ ቀርፆ እዩኝ ማለት ፅፎስ አንብቡኝ ይባላል ›› ገፅ 2-3 በማለት የፊልም ቀረፃ  እና የመፅሀፍ ስራ እንደማይሆን አሰረደኋቸው ይላሉ፡፡

ሁለተኛው ያልተሳካ ሙከራ በ 2008 የቢፒዲ አዋርድ አሸናፊ አሜሪካዊ ታሪኳን በበይነ መረብ ካነበበ በኋላ በታሪኳ በመሳብ ታሪክሽ የለየለት የመትረፍ እና ወደ ጥንካሬ የመመለስ ነው በማለት በመፅሀፍ ታሪኳን ለማዘጋጀት ቢከጅልም ፈቃደኛ መሆን አልቻለችም ፡፡ ከነዚህ ያልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ ወደ ሀገር ተመልሰው ምርጫ ቦርድን መርተው ሲሰናበቱ በተለይ ከባልደረቦቻቸው የቀረባለቸው ታሪክሽ በመፅሀፍ አስፍሪ ጥያቄ ተቀብለው ይህን መፅሀፍ ‹‹ ብዙ ፍቅር ለሰጠኝ እና ብርሀን ለሰጠኝ ማህበረሰብ (ቤቴ) ለበጎነት የፅሁፍ ሀውልት ላቆም ብድሯን ስለመመለስ ነች መልሼ የማልችለው ቢሆንም ›› ገጽ 12 በማለት መፅሀፍ ለመፃፍ መብቃታቸውን ይገልጻሉ 

ብርቱካን ሚደቅሳ በመፅሀፉ በተለይ ያሳለፈቸውን የፖለቲካ ጉዞ የበለጠ በመጽሀፉ ታሰፍረዋለች  ተብሎ ቢጠበቅም በመፅሀፉ የራሷን ትውስዎች የሰፈሯን እና ብሎም የሀገሯን ታሪክ ከትባ አስባስባ ስለአብዮቱ ስለ ፍትህ ፤ስለ ፍቅር ስለ ሰብአዊነት እና  ማህበራዊ ታሪካችን ሀዘንና ደስታችንን በሰዋዊ ቋንቃ የተረከችበትን መመለስ ስትል ርእስ የሠጠጭውን መፀሀፍ አበርክታለች ፡፡

የእንቢዎች ሰንሰለት

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በተለይ ወደ ፖለቲካው መግባት እንደ እርሾ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የቤተሰቧ አባል የሆነው አጓቷ ዛውገ ገ/መድህን መንገድ ይመስላል ለዚህም የኢህአፓ አባል የነበረው እነ ከኢህአፓ ጋር ይታገል የነበረው አቶ ዘውገ ገ/መድህን  መንድ መከተል ነው ከቀይ ሽብር በፊት ህይወቱ ያለፈው አቶ ዘውገ ገ/እግዜያብሄር ታሪክ ከቅርብ ቤተሰቧቸዋ የተነገራትን እንዲህ ታስቀምጠዋለች ‹‹ ሀዘኔ ጨርሶ እናቴ ያልተዋጠላት ስለነበርለእኔ የህልሜ አለም ሰው ስለሆንም አጎቷ በኅቷ እያወራችለን ነው ያደኩት ››ገጽ 51 በማለት እንዴት በአጎቷ እንደተሳበች ትገልጻለች ፡፡ከዚህ በተጨማሪም አጎቴ የሞተለት ኢህአፓ ይሉትን ድርጅት ምኑንም ከማወቄ በፊት ገና ልጅ እያለሁ ነው ይህን ስሜት በውሰጤ ያገኘሁት በቃ የአጎት ታሪክ ተደግሞ ተደግሞ ለቆመለት አለማ መስአትነትን መክፈል መፍቀዱ አጥብቆ ሳበኝ ›› እድሜየም እውቀትም ጨምሬ ዘውገ ህይወቱን ካጣ ከ 28 በኋላ እኔም እንደ ዘውገ ለአቅመ መሰዋአትነት ደረስኩ ታሰርኩ ቤት ለማስበርበር ልክ እንደ እንደ ዘውገ በፖሊስ ተንጠልጥየ መጣሁ ››ገፅ  52. በማለት በተለይ በእስር ወቅት ያሳለፉትን የተለያዩ ችግሮች እንደያልፉት የለ እንደሚባለው ነው ሲሉ ባመኑበት መንገድ መጓዝን እንቢ የማለትን መንገድ ከኢህአፓው ጭዳ  ዘውገ ገ/እግዚያብሄር መከቷሏን ትገልፃለች ፡፡

የብርቱካን ዳናዎች

የህይወት ታሪኳን ደጉሶ በያዘው መፅኅፍ ከማለዳ የህይወት ጅማሬ አንስቶ በህይወት ሀዲድዋ ውስጥ የምትመላለሰው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ‹‹የኔ የኔታ›› በሚል ርእስ ከልጅነት ሀሁ፤አቡጊዳ፤መልእክተ ወንጌል፤ካዛ ዳዊት ከደገመችበት የልጅነት ጊዜ በመነሳት ቀጥሎ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን  ስለተማረችበት የሚያዚያ 23 ት/ቤት ስለነበሯት የትምህርት ቤት እና የመምህራኖች ገጠመኞች በሚገርም ትውስታ አስቃኝታናለች ከዚህ ባለፈ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ላይ በተለይ ስድስተኛ እና ስምንተኛ ክፍል የነበራት ከፍተኛ ውጤት በመነን ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት / Special Class/ እንድትመደብ እንደረጓት በተለይ ከፈረንሳይ መነን እሩቅ ነው በማለት በተለይ ያላት ከፍተኛ ውጤት በመነሳት በመነን ት/ቤት ከከፍተኛ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች ጋር ለመማር መቻልዋን እዛ የነበረችበት የ 4 አመታት የትምሀርት ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብላ ለማሳየት ሞክራለች በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ለማምጣት የነበራት ትጋት በተለይ ስለ ማትሪክ ፈተና እንዲሁም በሀሳብ ብቻ/ MATHIMATICS /“C” በማምጣቷ ሳቢያ ወደ ህግ ት/ቤት መግባትዋን አውግታናለች ከዚህ ጎን ለጎን በአስራዎች አፍላ እድሜ ስለነበሩ የፍቅር ጥያቄዎች የአቻ ጓደኛ ግፊት ያንን ተቋቁሞ አላማን  ከግብ ማድረስን ለማሳየት ሞክራለች ከዚህ ባለፈ ሌሎች የሄደችባቸውን የህይወት መስመሮች በነቂስ  ለማሳየት በመፅሀፉ ተመላልሳለች ፡፡

ፈረንሳይ ለጋሲዮንን በመስታወት

- Advertisement -

ትውልዷ በፈረንሳይ ለጋሲዮን የሆነው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መፅሀፍ ከፖለቲካው ይልቅ ማህበራዊ ህይወቷን በተለይ ኢትዮጲያ ማህበራዊ ህይወት በተለይ ምን እንደሚመስል በፈረንሳይ ለጋሲዮን በኩል ለማሳየት ሞከራለች ከዚህም አንዱ በፈረንሳይ ስለሚገኙ እና በተለይ የሰፈሩ ታላላቅ አባቶች ስለሚዘወተሩበት ሰፈሩ ጠጅ ቤቶች፤ስለ ቀድሞ ሰፈሮችና በፈርሳይ ለጋሲን ስለሚገኙ ታረካዊ ስፍራዎች፤የፈረንሳይ ነዋሪ ስለሆኑት የቀድሞ ታዋቂ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ብዙም ያልተነገረ የቅድስና ተግባር ስለ ሰፈሩ ማህበራዊ መስተጋብር በፈረንሳይ ስለሚከበሩ የንግስ በአላት በተለይ  የግንቦት ልደታ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ማጠናቂያቀው የለም ባዳ በተሰኝ ንኡስ ርእስ ስር የቀረበውና በተለይ በ1990ዎቹ የሀገሪቱ ራስ ምታ ስለነበረው እና ብዙ ወጣቶች ስለቀጠፈው የኤድስ በሽታ በተለይ በቤታቸው ተከራይታ ትኖር ስለነበረው  ወለላ የተባለች እንስት ታሪክ ዋቢ በማድረግ  ወለላን ለማዳን ለማሳከም ማድረግ የሚገባቸውን ከቅርብ ጎረቤት ጋር በመሆን ያደረጉት ስዋዊ ተግባር ዳሩ የወለላን ህይወት ባያተርፍም ህይወቷ ካለፈ በኋላም ወለላ እድር ባይኖራትም የፈንሳይ ነዋሪዎች   የለም ባዳ ብሎው ማንም እድር ያለው ሰው የሚደረገውን አድርገው ግብአተ መሬት መፈፀሙን ከትባልናች በዚህ እንደ ሀገር ይዘነው የመጣነውን ልንለቅ የማይገባንን ሰብአዊ ተግባር ለማሳየት ያስቻላት ሲሆን አንባቢም በተለይ ቀድሞ ያለችውን የፈረንሳይ ለጋሲዮን ሰፈር በምናብ ልክ እንደመስታወት ገልፃ አሳይታናለች ፡፡

ያልፖተለኩ ፖለቲከኞች

በምርጫ ዘመን ዋዜማ በተለይ በሀገሪቱ የሚታተሙ ታዋቂ ጋዜጦች ሪፖርተርን ጨምሮ በሚዘግቡት የፓርላማ ክርክር ( በተለይ በአቶ በድሩ አደም እና ሌሎች በወቅቱ የነበሩ ጉምቱ ፖለተከኞ) በሚያርጉት ክርክሮች ሳቢያ በግል ለመወዳደር እንዲሳቡ እንዳደረጋቸውና እና በማግስቱም የምርጫ ህግጋትን ወደ ማበብ  መግበባታቸውን ሲገልፁ የመወዳደር ሀሳባቸውን ለወደጆች ቢያከፍሏቸውም በከፊል ድጋፍ ሲየገኙ በከፊል ነቃፌታንም አስተናግደዋል ፡፡ ቢሆንም በምርጫ 1992 የወረዳ 12/13 የግል ተወዳዳሪ በመሆን እና የምርጫ ምልክቷን ጭራ በማድረግ ተመዝግበው ተወዳድረዋል ፡፡በዚህ የመጀመርያ በሆነ የፖለቲካ ጉዟቸው በተለይ ከአንድ ጋዜጠኛ ተብየ የሚደርስባቸው ማስፈራርያ በተለይ ስም የማጥፋ ዘመቻ ሙከራ በጋዜጦች ላይ ስምሽን አጠፋለሁ  በየጋዜጣው ስምሽን ከማጥፋቴ በፊት መኝታ ተጋሪኝ የሚል ከፍተኛ የፆታዊ ጥቃት ሙከራ እንደረሰባቸው አስፍረዋል ያልፖተለኩ ፖሊከኞች እንደምትለን ብርቱካን በወቅቱ በፖለቲካው  የማይሳተፈው ደበበ ደፌራ የተባለ ወዳጃቸው ደፋር ጋዜጠኛ ተብየወን አደብ እንዲያሲዝላት ማድረግ ስትችል ከዚህ ባለፈ ለምርጫ ቅስቀሳ የግል ተወደዳሪ እንደመሆኗ መጠን የቅስቀሳ ዘዴዋ የመወዳደርያ ፖስተር በየአደባባዩ መለጠፍ ሲሆን በዚህ የካሰች ገ/ማርያም እገዛ የበረታ ነበር የሚሉት ወ/ሮ ብርቱካን የምርጫው ዘመንም በኢህአዴግ ወፈ ሰማይ ካድሬ ግጥሚያ በእኔ መሸነፍ ተጠናቀ የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ፖለቲከኛ ሳይሆኑ እሳቸው ለተሳተፉበት የፖለቲካ ተግባር የተባበሯቸውን ወዳጆች ያልፖተለኩ ፖለቲከኞች በማለት ተግባራቸውን በመፅሀፉ አካተውላቸዋል፡፡ 

ቡርቱካን የኢህአዴግ ፍሬ

ለቅንጅት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጣ ሁለ  ነገር ተካሮ ወህኒ በገባችበት ከማእከላዊ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በምትንገላታበት ወቅት በተለየዩ ሚዲያች በተለይ በአይጋ ፎረም የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ‹‹ ብርቱካን የኢህአዴግ ፍሬ ናት ›› እየተባለ ይፃፍ ነበር የሚለት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ  ‹‹ሊያስተላለፍ የፈለገው መልእክት ደግሞ በአጭሩ ብርቱካን ኢህአዴግ ባመጣው ስርአት ተጠቅማ ዳኛ ሆነች፤ምርጫ የተወዳደረች ብሎም የፓርቲ መሪ የሆነቸው ፍሬያችን ናት ›› ገፅ 245 ይህን መስማት ለእኔ ግርምት ነው የፈረጠረብኝ የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ‹‹ ያለ ሀጤአቴ ቀፍድደውኝ ሲየበቁ ፍሬአችን እያሉ ራሳቸውን ሲያሞግሱ ያፈራነውን የምንቀረጥፍ ነን ብለው እየተኩራሩም እንደሆነ እንዴት አይገባበቸውም ›› ገፅ 245 በማለት የነበረውን ተቃርኖ ይገልፃሉ ፡፡

በተለይ የጉርምስና እድሜዋን በዘመነ ደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት በርትቶ አብዝታ የምትሰማው ራድዮ ቁኑ ሙሉ ‹‹ ግፋ በለው› ሲል የበአሉ ግርማ ኦሮማይ ስርጭት ተክልክሎ በፎቶ ኮፒ ብቻ ስታነብ  በድብቅ  ቪ.ኦ.ኤ ታዳምጥ የነበረችው ብርቱካን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በተለይ በሚደረጉ ክርክሮች በኢህአዴግ የፖሊሲ ሀሳቦች መማረኳን የማትሽገው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከ1992 ምርጫ ላይ ለኢህአዴግ የነበራት አዎነታዊ አመለካከት ሙሉ ለሙአ አልተሸረሸረመ ፡፡‹‹በፍርድ ቤት ቆይታየ የመጀመርያ አመታት ራሱ በውሀ ቀጠነ ሰዎች እስር ቤት ሲታጎሩ እና ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲቀፈደዱ ሳይ ዋነኞች አለቆች ሳያውቁት ሊሆን ይችላል ወይም አልገባው ይሆናለ3 በሚል በአእምሮ ስንተ ምህረት ሊያርግላቸው ሞከረዋል ›› ገፅ 252 በማለት አሁንም ለኢህአዴግ የነበራቸው አዎንታዊ አመለካከት ያልከሰመ የነበረ ቢሆንም  በስተመጨረሻ የሆነው ሆኖ እድሜ ለስየ አብርሀ ጉዳይ የኢህአዴግ እይታየ ላይጠገን ተሰበረ በማለት ወደ ትግል እንድትገባ ሌላ መነሾ እንደሆናት ትገልፃለች ፡፡

ፈረንሳዊው ጎረቤቴ

የፈረንሳይ ለጋሲዮን ፍሬ የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በመፅሀፋቸው ከሳፈሩት ሌላኛው  እውነት በተለይ በወቅቱ የአትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሰደር ከነበሩት ስቴፋን ጎምፕርትዝ ጋር  የነበራቸውን ግንኙነት ነው ‹‹ ጥቅምት 1998 ቅንጅቶች ተጠራርገን ቃሊቲ ከመግባታችን በፊት ከአንድ ሁለት ቀን በላይ አላገኘሁትም ቃሊቲ ከወረድን በኋለ ሌሎች አምባሳደሮች እንደሚያርጉት እሱም እየመጣ ይጎበኛቸው እንደነበር እርቅም እንዲመጣ በመመላለስ ወትውቶናል የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ  ይህ የፈረንሳይ አምባሳደር ወ/ሪት ብርቱካን ቃሊቲ እስር ቤት ድረስ ዘልቆ ጠይቋል ለዚህም ምክንያቴ ጎረቤቴ ነሽ የሚል ነው ከዚህ ባለፈ የብርቱካን ቤተሰቦችንም ቤት ደረስ በመምጣት ይጠይቅ እንደነበር አልሸሸጉም ዳግም ከመጀመርያ እስር ከተፈቱ በኃላ  ታህሳስ 20 ቀን 2001 አ.ም ወደ ቃሊቲ የወረዱት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በወቅቱ የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው  ወደ ሀገራቸው ሊያቀኑ የነበሩትን አምባሳደር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒሰቴር መለስ ዜናዊ ያላቸውን መቀራረብ ተገን በማድረግ የብርቱካን ጉዳይ አወያይተዋል የውይይቱም ፍሬ ሀሳብ ‹‹ ይቅርታ ሳልጠይቅ ቀርቼ እስር ቤት ብገባ ድጋሚ የመውጣት እድል እጀግ ዘለግ ያለ ዘመንን እንደሚወሰድ የፈለጉትን  ይቅርታ መንግስታቸውን ካልጠየኩ በዚህኛው ዙር እስር አድሜ ልክ የፀና እንደሚሆን እና ምናልባት 25 አመታት የእርጅና ዘመን ሰደርስ የእስር ቤት አስተዳደር ካመነበት በአመክሮ ሊለቀኝ የሚችል መሆኑ ነው››  ገፅ 256 የሚል ሲሆን ከዚህ በኋላ ነው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አንገት አስደፊ  ያሉትን ይቅርታ ጠይቀው የእድሜ ልክ የተባለው እስር ቀርቶ ከ 18 ወር እስር በኋላ ነፃ መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ለዚህም ጎረቤታቸው የነበሩት የአምባሳደሩ ሚና ከፍተኛ ነበር ፡፡ 

አልፀፀትም

ከአፍላ ወጣትነት ጀምሮ በግል ተወዳደሪነት ለፓርለማ እስከመወዳደር ብሎም የተቃዋሚ ፓርቲ ከሌሎች ጉደኞች ጋር መስርቶ እስከመታገል ካዛም ባለፈ ከአንድም ሁለት ጊዜ ረዘም ላሉ ጊዜያት በእስር መማቀቅ ብሎም በመንግስት ግልበጣ እና ሙከራ ሞት እስከፈርዳባት ተጠየቅ የቀረበባት እና ሌሎች ክስተቶች ያሳለፈቸው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በእስር ጊዜ ፍርድ ቤት በምትቅርበብት ወቅት የነበረውን የወላጅ እኗታ ሁኔታም አልዘነጋችም ‹‹ በመሀል ወደ ቤተሰብ መቀመጫ ሰፍራ ሳይ እናቴ ፊቷ በላብ ተዘፍቆ መነሳት አቅቷት ወንበር ላይ ተቀምጣ ቀርታለች በምልከት ምንም አይሆንም አይዞን ለማለት ሞከርኩ አታየኝም ሰማይ ምድሩ ዞሮባትል ›› በማለት ከሷ ባለፈ የእናቷን ስቃይ አካፍላናለች ፡፡በመፅሀፏ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የማኅበራዊ  ህይወት እንዳሳየችን ሁሉ በተለይ በእስር በነበረችበት ወቅት የሰፈሯ እጅጉን መረበሸን አልሸሸገችም ፡፡

‹እኔ ከታሰርኩበት ጥቅምት 22 1998 ጀምሮ ለበርካታ ሳምንታት ፈረንሳይ ሰፈራችን የከረመቸው የጦርነት አውድማ መስላ ነው መጀመርያ ይህን ያየሁት ከማእካላዊ አስር ቤት ለብርበራ በሚ ጥቅምት 25 ወደ ቤቴ ይዘውኝ ሲመጡ ነው የሰፈሩ የሰፈሩ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በአድማ በታኝ ትጥቅ በታጠቁ በርካታ የፌደራል ፖሊስ ተወሯል ከመኖርያ ሌላ አንዳች ነገር የሌለበት መንደር ውስጥ ገብቶ ከሰው ደጃፍ ላይ ገፋ ሲልም ቤቱ ውስጥ ጦርነት የሚገጥም ፖሊስ ፈጣሪ ያሳያችሁ›› ገፅ 263  በማለት የነበረው ሁኔታ ትገልጻለች በሷ እስር ወቅት እንደዛ የታመሰ ሰፈር በተቃራኒው በሷ መፈታት  ከእስር መፈታት ተከትሎ ፌሸታ ሲሆን የብርቱካን መፈታት ተከት የምስጋና ፐሮግራም አዘጋጅቶ ለብርተካን መኪና  ሸልሟል  አዎ በዚህ መፅሀፍ የተጠቀሱና እና በተለይ በወህኒ ቤት ያጋጠማትን በሄድኩበት መንገድ ፈፅሞ አልፀጸትም የዋዛ ላልሆነው የነፃነት መንገድ እንኳንም ህይወቴን ሰጠሁ በየ አምናለሁ ምክንያቱም ከኢትዮጲያና ከህዝቦቿ የማይፈዝ ደማቅ ፍቀር ይዞኛልና ትለናለች ፡፡

እንደመውጫ

በተለይ በ1997 ምርጫን ተክትሎ ብቅ ካሉ ደፋር ፖለቲከኞች መካከል  የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የህይወት መስመሮቿን ያሰየችበትን መጥኀፍ ማበርከት ለሌሎችም አርአያ መሆን የሚችሉት  ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መመለስ በተሰኘ መፅሀፋቸው ውለታውን ቆጥሬ ለማልጨርሰው በደስታም በሀዘኔም ከጎኔ ለነበሩ የሰነ ፅሁፍ ሀውልት ይሆን ዘንድ ውለታ ለመመለስ የቆመ ሀውልት ነው የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካ ሚደቅሳ መፅሀፍ በሽፋኑ አይገመትም እንዲሉ በዋናነት ውስብስብ የሆነውና ያለፉትን የፖለቲካ ጉዞ ያሰፍራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ለየት ባለ መል ከልጅነት እስከ እውቀት ያለውን የሕወታቸውን ክፍል ገልጠው ማስነበብ ችለዋል በዘህ መጽሀፍ ውስጥ ያልተካተቱ እርሳቸው ዘንድ ያሉ ሌሎች ፖለቲካዊ ወጎችን ይዘው በሚቀጥለው መፅሀፍ ይመጡ ዘንድ እየጠየኩ በዚህ ላብቃ ፡፡

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena 

2 COMMENTS

  1. Well, it is good to share the information you read and understood.

    It is good for her to put her story the way she believes and wants.

    But , one undeniable fact remains as a bad memory of what and how she damaged by 1) signing

  2. Well, it is good to share the information you read and understood.

    It is good for her to put her story the way she believes and wants.

    But , one undeniable fact remains as a bad memory of what and how she damaged herself by 1) admitting and signing that she was guilty to be released from prison. 2) And most disturbingly by becoming the chairwoman of the so called Election Board that was/is the very simple instrument of the very criminal political system of Abyi Ahmed . She totally lost her multiplied her past credibility by zero when she played a huge role to make the election the very tragic one as far as the very critical interest of the people was concerned.

    I don’t know how people feel comfortable to read this story of her own ????

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News