
ቦርከና ዜና
በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የክልሉ መንግሥት የትርፍ ሰዓት ክፍያዎችን በቅርቡ በተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ መሠረት እንዲያሰላ ጠይቀዋል።
ባለሙያዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት የፌዴራል መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የክፍያ ሥርዓት እንዲኖር ካወጣው መመሪያ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲተገበር መሆኑ ተገልጿል።
በባሌ ሮቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች፣ ጥያቄያቸው የተሻሻለውን የደመወዝ መዋቅር መሠረት በማድረግ የሚከናወኑ የሥራ ክፍያዎችን የሚገዛውን ብሔራዊ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
“ለአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ የሚሆን በጀት የለም ተብለናል። ለሁለት ወራት በአዲሱ ደመወዝ መሠረት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አግኝተን ነበር፣ ከዚያ በኋላ ግን ክፍያው ተቋርጧል ሲሉ” ተናግረዋል።
በጉደር ሆስፒታል የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ የመስከረም እና ጥቅምት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች በአዲሱ ደመወዝ መሠረት መሰጠታቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ሆኖም የሆስፒታሉ አመራሮች በኋላ ላይ ተጠርተው ክፍያውን በ“በአዲሱ ደመወዝ” መሠረት እንዳይፈፀም መመሪያ እንደተሰጣቸው ሐኪሙ ገልጿል።
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕሮፌሰር ነፃነት ወርቅነህ በሰጡት ምላሽ፣ ውሳኔው በክልል ደረጃ የተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገርግን የተቋረጠባትን ምክንያት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል ተብሏል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






