Homeአበይት ዜናእስራኤል የፖሊስን ሥራ የሚያግዙ አነፍናፊ ውሾችን ለኢትዮጵያ ሰጠች

እስራኤል የፖሊስን ሥራ የሚያግዙ አነፍናፊ ውሾችን ለኢትዮጵያ ሰጠች

Advertisement
World Wide Travel Group
አነፍናፊ ውሾች
ከማህበራዊ ሚዲያ

ቦርከና ዜና

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  በአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር የፖሊስን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዙ አነፍናፊ ውሾችን (K9) ከእስራኤል ፖሊስ በድጋፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የሆኑት ም/ኮ ጀነራል መላኩ ፋንታ ድጋፉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት አነፍናፊ ውሾቹ በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት በኩል ከተለያዩ የውጪ ሀገራት ወደ አገሪቱ የሚገባውንና የሚወጣውን አደገኛ ዕፅ ለመከላከል እና ዝውውሩንም ባደገ ሁኔታ ለመቆጣጠር እንደሚያስችሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም በኬ ዘጠኝ በመታገዝ ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውንና የሚወጣውን አደገኛ ዕፅ በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  የፀረ-ፈንጂና የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር መምሪያ ባለሙያዎች በእስራኤል ሀገር ቴል አቪቭ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰው አነፍናፊ ውሾቹ ሰልጥነው ወደ አገሪቱ ሲገቡ ለ39ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከእስራኤል ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ዕፅ ዝውውር በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በርካታ  ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News