Homeነፃ አስተያየትያያ ታዴ እንቶ ፈንቶ (ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ) 

ያያ ታዴ እንቶ ፈንቶ (ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ) 

Advertisement
World Wide Travel Group

ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

ታደሰ ወረደ ብልህ ፖለቲከኛ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ቧልተኛ የጦር መኮንን ይመስሉኛል፡፡

ህ.ወ.ሀ.ት ከጥር 17 ቀን 2018 ዓ/ም አንስቶ በአማራ ክልል ይዞታዎች ላይ ከሰነዘረው አራተኛ ዙር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ለትግራይ ክልል ቴሌቪዢን በሰጡት ቃለ-ምልልስ ላይ የትግረኛ ልሳን በተጣባው የተበላሸ አማርኛ እየተንተባተቡ ያስተላለፉት መልእክት አስደማሚ ብቻ ሳይሆን የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ተብሎ ሊወሰድላቸው እንደሚችል አልጠራጠርም፡፡

“እኔ እኮ ታጣቂዎቼን ወደምስራቅና ምእራብ ጠለምት ወረዳዎች ያዘመትኩት ወደቀድሞው የትግራይ ሉኣላዊ ግዛት እንደገና ለመመለስ ያለኝን ፍላጎት ለፌደራሉ የሀገር መከላከያ ኀይል ከወዲሁ ለማስታወስ እንጂ የምራቸውን እንዲዋጉ አልነበረም” ሲሉ ግብዙ ጀኔራል አንዳች ሀፍረት ሳይሰማቸውና ሳይሸማቀቁ በአደባባይ ሲያላግጡ ሰማናቸው፡፡

እነሆ በአሁኑ ወቅት ግን “ጥቃት የከፈተውና አንዳንድ ስፍራዎችን ለጊዜውም ቢሆን ተቆጣጥሮ የነበረው ወራሪ ሰራዊታቸው ወደኋላ እንዲመለስ ተለዋጭ ትእዛዝ መስጠታቸውን ሳይቀር ድፍረት በተመላበት አነጋገር ገልጸው ለወደፊቱም ቢሆን በሠላም እንጂ በጦርነት የሚፈታ ችግር የለም ሲሉ የመግለጫቸውን ተደራስያን ማንነት እንኳ በቅጡ ያላገናዘበ ተጨማሪ ማብራሪያ አይሉት ማደናገሪያ አክለዋል፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ለመሆኑ በወቅቱ የትግራይ ፖለቲካዊና መንግሥታዊ አደረጃጀት ውስጥ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪ የህ.ወ.ሀ.ትን ታጣቂ ኀይል የማሰማራት መብትና ሥልጣን አላቸው እንዴ?

እስከምናውቀው ድረስ ጀኔራሉ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጉንቱ ተሿሚ ቢሆኑም በተዘበራረቀና ቅጥ አምባሩ በጠፋበት የፖለቲካ ማእበል ውስጥ እየተናጠች ባለችው በዛሬዋ ትግራይ ውስጥ ከህ.ወ.ሀ.ት ታማኝ አሽከርነት የዘለለ አንዳች ረብ ያለው ኃላፊነት የላቸውም፡፡

ታዲያ እኝህ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት የትግራይ መከላከያ ኀይል (T.D.F) እየተባለ የሚንቆለጳጰሰውንና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተደራጅቶ ከፌደራሉ መንግሥት ክትትልና እይታ ብቻ ሳይሆን ከፕሪቶርያው የተኩስ ማቆምና የዘላቂ ሠላም ስምምነት ባፈነገጠ መንገድ በነደብረ-ጽዮን ገብረ-ሚካኤል ስር የሚታዘዘውን አማጺ ኀይል በምን ሂሳብ ሊመሩና ለእንዲህ ያለው ግዳጅ ሊያሰማሩ ይቻላቸዋል?

ሰውየው እንዳጫወቱን ከሆነ ታዲያ ጉድ አንድ ሰሞን ነው እንዲሉ ወራሪው የህ.ወ.ሀ.ት ኀይል በቅርቡ በከፈተው ድንገተኛ ወረራ ንጹሃንን ጨፍጭፎና ሀብት-ንብረታቸውን አውድሞ ሳይሆን ለጠለምት ህዝብ የወዳጅነት ሠላምታ አድርሶና በአማራ ክልል የተያዘው ግዛት ለወደፊቱ ወደትግራይ ሉኣላዊ መሬት ሊመለስ ይችል ወይም አይችል እንደሆነ ከወዲሁ መጠነኛ ፍተሻ አድርጎ ነው ወደኋላ እንዲያፈገፍግ የተደረገው፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቀድሞ ነገር በአለም-አቀፋዊው የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት ውስጥ የትግራይ ሉኣላዊ መሬት የሚባል ነገር የለም፣ አይታወቅምም፡፡

እንደየትኛውም የፌደሬሽኑ ኣባል ሁሉ ትግራይ የሉኣላዊት ኢትዮጵያ ክፍልና አካል የሆነች አንዲት የአስተዳደር ክልል እንጂ ራሷ ነጻና ሉኣላዊት የሆነች አገር አይደለችም፡፡ ህ.ወ.ሀ.ት ራሱ ያስረቀቀውና ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የምትተዳደርበት ፌደራላዊ ሕገመንግሥትም ቢሆን ከውስጣዊ የአስተዳደር አውቶኖሚ ባለፈ የአንድን ነጠላ ክልል ሉኣላዊነት የሚገልጽ ድንጋጌ አካቶ አናገኘውም፡፡

በርግጥ ይህ አይነቱ የተራመደና በእውቀት ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብ እብሪትና ማን-አህሎኝነት ከአቅማቸው በላይ ለሚያንጠራራቸውና ጥቁር የመሀይምነት መንጦላእተ-ደመና  ዓይነ-ህሊናቸውን ለጋረደባቸው አንዳንድ የትግራይ ፖለቲከኞችና የጦር ሹማምንት ፈጽሞ ሊዋጥላቸው አይችልም፡፡

አሁን አሁንስ ብልጣብልጥነቱ ሳይቀር ከጊዜ ወደጊዜ እየነጠፈባቸው መምጣቱን ነው የምንታዘበው፡፡

- Advertisement -

አንዳች እንጥፍጣፊ ሳይተው አቅመ-ፖለቲካውን ሁሉ ለገሰ ዜናዊ ይዞባቸው ወደመቃብር የወረደ ነው የሚመስለው፡፡

በርግጥ ሁላችንም በሚገባ እንደምናስታውሰው አፈሩ ይቅለለውና የዜናዊ ልጅ እኮ በጊዜው ተንኮለኛና ጸረ-ኢትዮጵያ ሆኖ ከመገኘቱና በየትኛውም የአለም ክፍል በመንግሥታት መሪዎች ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ በቁንጮነት ከሚመራት አገሩ ይልቅ በተጋነነ የአፍቃሬ-ተገንጣዩዋ ኤርትራ አቋም አብዝቶ ሲንቀሳቀስ ከመታየቱ በስተቀር ጥሬ እውቀቱንም ይሁን ፖለቲካዊ አቅሙን በተመለከተ ያን ያህል የሚታማ ሰው አልነበረም፡፡

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News