Homeአበይት ዜናበቅርቡ ኤርትራ የነበሩት የሳዑዲአረቢያ ባለስልጣን በድጋሚ ወደ አዲስአበባ መጡ

በቅርቡ ኤርትራ የነበሩት የሳዑዲአረቢያ ባለስልጣን በድጋሚ ወደ አዲስአበባ መጡ

Advertisement
World Wide Travel Group
የሳዑዲአረቢያ ባለስልጣን

ቦርከና ዜና

የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ባለስልጣናት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኝተዋል።

ባለፈው ሳምንት ወደ አስመራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተወያዩት የሳውዲ አረብያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ዛሬ አዲስአበባ ገብተዋል።

ሚኒስተሩ ዛሬ ረፋድ ላይ ከዶክተር ጌድዮን ጢምትዮስ ጋር መምከራቸው ተገልጿል። አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአዲስአበባ እና በሪያድ መካከል ውይይት ሲደረግ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ከሶስት ሳምንት በፊት ዶክተር ጌድዮን ወደ ሳዑዲዓረቢያ ተጉዘው ከጂዳ ሚኒስትሮች ጋርም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በተመሳሳይ ከአንድ ሳምንት በፊት የሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስአበባ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተወያይተዋል። ዛሬ ደግሞ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋርሐን አዲስአበባ ገብተዋል ተብሏል።

የከፍተኛ ባለስልጣናቱ የዛሬው ውይይት ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረውን የሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ማተኮሩም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ነው የተባለው፡፡

ነገርግን የባለስልጣኑ ተደጋጋሚ ጉብኝት የቀጠናው ትኩሳት ከመቸውም ጊዜ በላይ መጨመሩን የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

__

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News