Homeዜናረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በዋስ ተለቆ ሲወጣ ዳግም በታጠቁ ሀይሎች ታፍኖ ተወሰደ

ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በዋስ ተለቆ ሲወጣ ዳግም በታጠቁ ሀይሎች ታፍኖ ተወሰደ

Advertisement
World Wide Travel Group
ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው

ቦርከና ዜና

ለአመታት በግፍ እስር ላይ የነበረው ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቅ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከተወሰነና በዛሬው ዕለት ከቀኑ 11 ሰኣት ገደማ ሂደቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ወድያውኑ በታጠቁና ጭምብል በለበሱ የመንግስት ኃይሎች መስታወቱ ጥቁር በሆነ መኪና ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ኢሕአፓ፤ ብልጽግና ሰላማዊ ዜጎች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽመው የግፍ እስር አልበቃ ብሎት በተደጋጋሚ አፈናዎችን ማድረጉን ተመልክቻለሁ ብሏል።

ፓርቲያችው መንግስት ያፈነውን ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በአስቸኳይ በሙሉ ደህንነት እንዲለቅ እና አሁንም በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ በጽኑ አሳስቧል።

የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ ግድ ይለናል የሚሉ ተቋማት እና ዜጎችም ይህንንና መሰል የብልጽግና መንግስት ወንጀሎችን በብርቱ እንዲያወግዙና ስለ ሰውነት ክብር በምናደርገው ትግል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ጥሪ አቅርቧል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

__

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News