Homeአበይት ዜናበሰሜን ወሎ ዞን ሲሪንቃ ከተማ በተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት የአባትና ልጅ ህይወት...

በሰሜን ወሎ ዞን ሲሪንቃ ከተማ በተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት የአባትና ልጅ ህይወት አለፈ

Advertisement
World Wide Travel Group
ፋይል

ቦርከና ዜና

የመንግስት ጦር በአካባቢው በፈፀመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት አንድ የ65 አመት አባት እና የ23 አመት ልጃቸው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቦርከና ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ለቦርከና በሰጡት አስተያየት የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ በመኖሪያ ቤት ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈው በቤት ውስጥ ስለነበሩ እንደሆነ ገልፀው፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ከቤት ውጭ በመሆናቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን አስረድተዋል።

ከአባትና ልጁ በተጨማሪ በቤት ውስጥ የነበሩ እንስሳቶቻቸው ተገድለዋል ተብሏል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በአካባቢው የነበረው ተኩስ ከባድ እንደነበር የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ ከአዲስአበባ እና ከደሴ የመጡ ተጓዦች መንገዱ በግጭቱ ምክንያት በመዘጋቱ ህይወታቸውን ለማትረፍ ከተሽከርካሪ ወርደው በመኖሪያ መንደሮች ለመግባት መገደዳቸውን አብራርተዋል።

የአይን እማኞቹ የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ የደረሰው ሰሞኑን የፋኖ ሀይሎች በወልዲያ ዙሪያ ሰፍሮ በሚገኘው የመከላከያ ሀይል ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ ጦርነት ከታጣቂዎቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የመንግስት ጦር በወሰደው የአፀፋ እርምጃ ነው ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል።

__

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News