
የመጽሀፍ ግምገማ -አጼ ዘርአ ያእቆብና ሥራዎቹ
ገምጋሚ ኤዲ/አደፍርስ ሀብቴ መካሻ
ቄስ ቻፕሊያን / የእርቅና የማህበረሰብ ጉዳዮች አማካሪ
ይህን ታሪካዊና ሀገራዊ መጽሀፍ ለማንበብና ለመገምገም ያነሳሳኝ በትውልድ ሃገሬ ኢትዮጵያና በአሜሪካ ከሃያ አመታት በላይ ቆይታዬ ለሰላም ለፍትህና ዲሞክራሲ በግልና በየማህበራቱ ካጋጠሙኝ እውነታዎችና ያለፍኩባቸው የትምህርትና የህይወት ልምድ በመነሳት ታሪኮቻችን በማንኛውም መልኩ በውጭ ጸሮቻችንና በራሳችን የዋህ ወይም ምንደኛ ሰዎች እንዳይጎዱ በማሰብ ነው::
ዝርዝር ጉዳዮች
የመጽሀፉ ርእስ- አጼ ዘርአ ያእቆብና ስራዎቹ
ደራሲ – ቴዎድሮስ ደመቀና ዶ/ር አንዷለም
አባተ የአጸደ ልጅ
የገጾች ብዛት 543 በማንኩሳ ማተሚያ አዲስ አበባ በ2017 የታተመ
መግቢያ
ይህ መጽሃፍ ርእስ የሰጠውና ያተኮረበት ንጉስ ዘረያእቆብ በመጀመሪያዎቹ የመካከለኛ ዘመናት በ14ኛው ክፍለዘመን(1385) የተወለደ በዚያ ዘመን ገናናትዋ ከፍ ብሎ ታዋቂ ትልልቅ ድንቅ ከተሞች እነበረራን በመሃል ኢትዮጵያ የገነባችበት በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ እጅግ ገናና ሃያል የሆነችበት ዘመን መገባደጃ ላይ ነበር::ያች ገናና ኢትዮጵያ የአሁኑ አትላንቲክ ውቅያኖስ በስሟ ይጠራ የነበረች ለውጭ ወረራና ከገናናት ከፍታ የወረደችበት የውስጥ የስልጣን ፉክክር መሳፍንቱ ሳይቀር እንዳይገዳደሉ በከፍተኛ ተራራ ላይ ይጠበቁበት የነበረውን ታሪካችንን ራሴላስ የመሳፍንት ታሪክ ከሳሙኤል ጆንሰን ማንበብ ይቻላል::ያ ስንፍናችን እየቀጠለ ምን ያህል እንደጎዳን ከታሪክ ተምረን ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እንድንበቃ በመመኘት ይህን ግምገማ በአክብሮት አቀርባለሁ::
የመጽሃፉ ሚዛናዊነት
ደራሲዎቹ ስለዘረያእቆብ መልካም ገድሎች ሲዘግቡ ዘረያእቆብ መንግስቱ ይጸና ዘንድ ሃገራችንን ሊከፋፍሉ እንደሚችሉ በመስጋት ያስወገዳቸው መነኮሳት የነአባ ባህርይ ወይም ደቅ እስጢፋኖስ ደጋፊዎች የሚያቀርቡትን የተቃውሞ ሃሳብ በመጽሃፉ አቀርበዋል እውቁ የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ በዚሁ መልክ ያቀረቡት በህግ አምላክም ይስተዋል::
ሆኖም ግን የደቅ እስጢፎን ተሃድሶ በመደገፍ በዘረያእቆብ ላይ የከፋ ነቀፌታ በወንጌላዊያን አማኞች ዘንድ የተስፋፋው የአፍሪካና ጥቁር ህዝቦች ጽኑ መሪዎች ስም ትግል እንዲጎድፍ ለነጻነታችን የተዋደቁ አጼ ቴዎድሮስን የወራሪ እንግሊዞች ጸሃፊዎች እብዱ ንጉስ ያሉትንና የአፍሪካ የነጻነት ድል ተምሳሌት የአድዋን ታሪክ መሪ አጼ ምኒሊክን በሚያጥላሉበትና የሃገራችን መሰሎቻቸው ለትውልድ በሚያስተላልፉበት መልኩየዘረያእቆብንም እንዳጎደፉ በዘረያእቆብ ስራዎች ጥናታዊ ጽሁፍ ካቀረበ የወሎ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ገምጋሚው ተረድቻለሁ::እኒህ በሚሲዮን ስም የዘረያእቆብን ጉድለት ብቻ የጋቱን የራሳቸው አውሮፓ ጸንታ እንድትቆም የጀርመኑ ቢስማርክ ያደረገውን ጨካኝ እርምጃ ሊዘክሩ አይፈልጉም::የራሳችን የወንጌልና የታሪክ ታላቆች የአጼ ቴዎድሮስ አማካሪ አለቃ ዘነብ በአጼ ምኒሊክናአጼ ሃይለስላሴ ዘመን የታሪክ ሊቆቹና የወንጌል ምሁራን አለቃ ታዬና የዶ/ር አዲስ አለማየሁ አስተማሪና አርታኢ ቄስ ባድማ ያለው ስለዘረያእቆብ የከፋ ትርክት ሳይዘግቡ በክፉ ሚሲዮናዊያን የተበረዘው ትውልድ ይህን ክፉ ጥላቻ ማቆምና ሃገራዊ ቅርስ መጠበቅ እንዳለበት መጽሃፉ ያስተምራል::
የመጽሃፉ ዝግጅት ተባባሪዎች የነጆቴ ልጆች እነ ነጻነትና ሌሎችም ከሁሉም የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች መካተት የመጽሃፉ ሚዛናዊነት ብቃት አንዱ መልኩ ነው::
የሴቶች እኩልነት በዘረያእቆብ አገዛዝ መከበር
የሃገራችን ኢትዮጵያ አንዱ ክፉ የቆየ ልማድ የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ ሴቶችን የይሁዲ ባህል እንደሰው የማይቆጥረውን በሚመስል መልኩ ሴቶችን ያገለለውን የመንግስት ከፍተኛ አስተዳደር በሴቶች ለመሙላት ያደረገው ትልቅ እመርታ ነበር::በዚህ ከተመደቡት ውስጥ የራሱ ሴትልጅ በጥፋት ስትገኝ ተገቢ እርምጃ መውሰዱም ልእልትችን በተራበ ከመሳለቅ ኬክ ይብሉ ከሚሉ የፈረንሳይ ልእልቶችና በአምቻ ጋብቻ ስልጣን ከተቆናጠጠና በፍቺ ከታወቀው የእንግሊዝ ሞናርኪ የተሻለውን ንጉስ ዘረያእቆብ አዋቅሮ ነበር::
የሃገር መከላከያ አደረጃጀትና መስተዳድሮች
የሃገራችን ኢትዮጵያ ሰራዊት ሃገሩን በሚገባ የሚጠብቅ ፍትህ የሚያስከብር የሌሎችንም ፍትህ ለማስከበር የመን ድረስ የዘመተውን በሚያስተማን መዋቅር ዘረያእቆብ ማደራጀቱን መጽሃፉ በዝርዝር ያትታል::
የየአካባቢው መስተዳድሮችን ዘረያእቆብ በሃገርኛ ጤናማ ፌደራላዊ ስልት ያካሄደ ሲሆን የነበሩትም መጠሪያዎች በትክክል አካባቢያዊና ተቀባይነት የነበራቸው ነበሩ::
ንግድና አለምአቀፍ ግንኙነቶች
ዘረያእቆብ በዚያን ወቅት የገናናዋ ኢትዮጵያን አንድነት ከሰሜን ከተማረበት ደብረቢዘን ባህረ ነጋሽ/ ኤርትራ እስከ ደቡብ ሸካ ባሌከምስራቅ ሞቃዲሾ እስከ እናርያ ምእራብ ድረስ በጥበብ በእኩልነትያስተዳረናየኢትዮጵያ ምርቶችን ከውጭ ምርቶች ጋር በተገቢው ያስፈጸመ ነበር::ቆይቶ ባርያ ፍንገላው ሲጀመር ሁሉም እንደተሳተፈበት የእናርያ አባገዳዎች አስቴር ገኖና ሌሎቹን ባርያአድርገው ሸጠው በስዊዲን ሚሲይኖች ነጻ የወጡበት ሌሎችም ኦነሲሞስ ነሲብ /ሂካን ጭምር እንዳይከሰት ዘረያእቆብ አስቀድሞ የሰው ዘር እኩልነትን በይፋያስተማረና የተገበረ መሪ ነበር::
ማጠቃለያ
ሃገራችን ኢትዮጵያ የራስዋን ድንቅ ታሪክና መሪዎች እንድታከብር ሊደረጉ የሚገባቸው ለውጦችም በሃይማኖትና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነትና የራስ ማስተዳደር ሙሉ መብትተጠብቆ እንዲቀጥል ኢትዮጵያችንም የቀደመ ከፍታዋ እንዲመለስ ይህ መጽሃፍ እንደሚመክረን ልንተገብር ሃገራችን ኢትዮጵያን ለማንሳት ሁላችንም እንድንረባረብ ያሳስበናልና እናንብበው እናጋራው::
__
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






