
ቦርከና ዜና
በአዲስ አበባ ከተማ፣ ኮተቤ 02 አካባቢ በተለምዶ ከአንቆርጫ ገብርኤል ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 ሰዎች በላይ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
የአደጋውን መንስኤ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስአበባ ፖሊስ አስታውቋል።
አንድ ተሽከርካሪ የመንገዱን አካፋይ ጥሶ በመውረድ በተከሰከሰበት በዚህ ዘግናኝ አደጋ፤ ህይወታቸውን ካጡት መንገደኞች መካከል በማይታመን ሁኔታ አንዲት ትንሽ ታዳጊ ህፃን በተዓምር በህይወት መትረፍ ችላለች።
በአካባቢው እና በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ከእንዲህ አይነቱ ልብ ሰባሪ አደጋ ትምህርት በመውሰድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና እርጋታ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






