Homeመጣጥፍይድረስ ለቴዲ አፍሮ፤ ለጀግናችን

ይድረስ ለቴዲ አፍሮ፤ ለጀግናችን

Advertisement
World Wide Travel Group

ይድረስ ለቴዲ አፍሮ፤ ለጀግናችን

በእጹብ ድንቅ ስንኞችህ
ስሜት ነኪ ዜማዎችህ
ቁጭት ቀስቃሽ ስራዎችህ
ለድምጻችን ድምጽ ሆነህ
ከፊታችን የቆምክልን፤
በውስጥ አገር፤ በውጭ አገር
ስቃያችን መከራችን
እ ህ ህ አችን ጭንቀታችን
በብርሃን አሳይተህ
በቅላጼህ ያዜምክልን
ቴዲ አፍሮ፤ ነህ ጀግናችን
ለድምጻችን ድምጽ ሆነህ
እንባችንን ያበስክልን።

በዘመነ ውርደት፤ 
በዘመነ ዕብሪት
ዕውቀት ወደ ሁዋላ
ድንቁርና ወደፊት
ሃሰት ቅጥፈት 
ማደር ለከርስ በነገሱ
ንዋይ ስልጣን 
ሰውነትን ባረክሱ፤
ፍትህ ርትዕ
ሰላም ፍቅር በኮሰሱ
በነጻነት፤ በዕኩል መኖር
በፖሊሲ በተጣሱ
እንደ አንድ ህዝብ 
እንደ አንድ አገር
አብሮ መኖር በተረሱ።

አንድነትን ለኢትዮጵያችን
በፍቅር መኖር ለህዝባችን
የምትሰብክ ሃዋርያ
ቴዲ አፍሮ ነህ አርአያ።

ፋና ወጊ ያሳብ መሪ
የተኛ አንቂ፤ ቀስቃሽ ነሺ
ድል ኮርኩዋሪ ድል መካሪ
በምነት ተስፋ ድል አብሳሪ።

ቴዲ አፍሮ፤ ነህ ጀግናችን
የጦቢያ አምላክ፤ አላህ ከቢር
ረጅም ዘመን ያኑርልን
ጤና ሰላም ያድልልን።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቴዲ አፍሮ፤ ውድ ጀግናችን
ኑር በብዙ ኑር ለቤትህ
ለልጆችህ ቤተሰብህ
ህዝበ ኢትዮጵያ አፍቃሪዎችህ
ለጦቢያ ውድ አገርህ
ወግ ማእረግ ታሪክ ክብርህ፤
ስንኝ ቁዋጥረህ ዜማ አዚመህ
ታሪክ ገድልዋን የሰበክሃት
በሙሉ ልብ በጀግንነት
ባደባባይ የጮህክላት
አረንግዋዴ ቢጫና ቀይ
ክብር ሰንደቅዋን “አንሳ! ወደ ላይ!”
ከውስጠ ነፍስህ የጮህክላት ።

ቴዲ አፍሮ፤ ነህ ጀግናችን
ኑር በብዙ ለኢትዮጵያችን
ኑር በብዙ ለህዝባችን።

አስፋው ረጋሳ
ሚያዝያ 2018
ከምድረ አሜሪካ

__

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በመጣጥፍ  መድረክ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡

ቦርከናን ይደግፉ :-እዚህ ገጽ ላይ 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News