Homeአበይት ዜናኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

Advertisement
World Wide Travel Group
ከማህበራዊ ሚዲያ

ቦርከና ዜና

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)  ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠርቶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ገልጸዋል።

ሰልፉን ኢሕአፓ አባል በሆነበት በትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ደረጃ ለማሳደግ መወሰኑን ፓርቲው የገለጸ ሲሆን፣ ሰላማዊ ሰልፉ መቼ እንደሚደረግ በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ቸርችል አካባቢ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ውይይት አካሂዷል።

የቅንጅቱ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት “የዛሬዉ ውይይት ዓይን ገላጭ ነው፤ በቀጣይ በሌሎች ክፍለከተሞች በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ውይይቶች ይቀጥላሉ” ብለዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)  (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ከትብብሩ አባላት ጋር በመነጋገር ያደረገው ቢሆንም፣ አንድ አንድ አካላት ለመከፋፈያ ሲጠቀሙበት ነበር” ብለዋል።

“ትብብሩ በተናጥል እየሄደ ነው። ትብብሩ ፈርሷል፣ የፓርቲው ጤናማነት አደጋ ላይ ነው፣ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እና የአባላት መከፋፈል ለመፍጠር ተሞክሯል” ያሉት መጋቢ ብሉይ አብርሃም “ልምድ ባላቸው ፖለቲከኞች መፍትሄ አግኝቷል” በማለት ገልጸዋል።

አክለውም፣ “በመሆኑም አሁን ላይ የበለጠ እንዲጠናከር ስለፈለግን፣ የተጠናከረ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሰልፉን በቅንጅት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ወስነናል” ብለዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ በቅንጅቱ አማካኝነት መቼ እንደሚደረግ ይፋ ያላደረጉት መጋቢ አብርሃም፣ “በቅርቡ ቦታው ይፋ ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ቅንጅቱ ሰልፉን አንድ ጊዜ ብቻ የሚያደረግ ሳይሆን የቅስቅሳ ጊዜው እስከሚጠናቀቅበት ወቅት ድረስ በተደጋጋሚ በስታድየሞች እና በትልልቅ አደባባዮች ለማድረግ መወጠኑንም ጨምሮ ተናግሯል።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

- Advertisement -

Ethiopian News–Borkena English

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News