
ቦርከና ዜና
ስምረት ፓርቲ ዛሬ ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ሁሉን ዓቀፍ እና አሳታፊ በሆነ መልኩ እንደገና እንዲዋቀር ጠይቋል።
ፓርቲው በመግለጫው ሕወሃት ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የክልሉን ምክር ቤት ወደነበረበት ለመመለስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ “አደገኛ” እና “አውዳሚ” ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል።
ፓርቲው የፌዴራል መንግሥት፣ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ እና የትግራይ ተወላጆች በቀጣናው ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሁሉንም ወገኖች ድምፅ ያካተተ እንዲሆን አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ፓርቲው በአጽንኦት አሳስቧል።
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena






