Homeአበይት ዜናጋዜጣዊ መግለጫየአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት ወቅታዊ መግለጫ---

የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት ወቅታዊ መግለጫ—

Advertisement
World Wide Travel Group
የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ተብዬው ባለመሳተፍ ወይም የድምፅ መስጫ ወረቀቱን በማበላሸት መቃወም አለበት !!!

እውነተኛ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ከምርጫ ተብዬው ማግለል ይገባቸዋል!!!

ሰኞ፣ ግንቦት 17፣ 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባን ሕዝብ ጨምሮ አብዛኛው የኢትዮጲያ ሕዝብ ከተፈጥሮ የተጎናጸፈውን እና በአገዛዞች የተነጠቀውን ሉዓላዊ ስልጣኑን መልሶ በእጁ ለመጨበጥ በተለያየ መንገድ ትግል እያደረገ ባለበት በአሁኑ ግዜ፣ “7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ” የሚባል የተለመደ እና አሰልቺ ድራማ እየተተወነ ይገኛል። የዘንድሮውን “2018 ምርጫ” ተብዬ ከባላፉት ስድስት ምርጫዎች የተለየ የሚያደርገው በትግራይ ክልል 100%፣ በአማራ ክልል በግምት 80%፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሱማሌ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች በርካታ የገጠር ቀጠናዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ45 % በላይ ኢትዮጲያዊያን በጦርነት ምክንያት ሊሳተፉ የማይችሉበት መሆኑ ነው። ከዚህ እውነታ በተቃራኒ፣ አገዛዙ “በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ምርጫ ለማካሄድ 97 በመቶ አስቻይ ሁኔታ አለ” በማለት ሰሞኑን በይፋ እየቀጠፈ መገኘቱ ለህዝባችን የማንቀያ ደውል ሊሆንለት ይገባል።

 በተጨማሪም፣ ባለፉት ስድስት ምርጫ ተብዬዎች እንኳን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ፣ በአንፃራዊነት አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ጠንካራ ተቃዋሚዎች የሌሉ መሆናቸውም መላው ዓለም የሚያውቀው ሐቅ ነው።ይህም፣ ስድስተኛው “ምርጫ 2013” ተብዬውን ነፃ ለማስመሰል ብልፅግናን እንዲያሸንፉ ከተፈቀደላቸው ከአምስት የማይበልጡ ተቃዋሚዎች መካከል፣ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ለእስር ተዳርገው እየተሰቃዩ ያሉበት ሁኔታ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት እውነተኛ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ ይገባል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

 የአዲስ አበባ ህዝብ ሆይ !!!

ባለፉት አምስት ዓመታት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ነዋሪዎች ጥረው ግረው በመሃል ከተማ ያፈሩትን ወይም በውርስ ያገኙትን አንጡራ ሀብታቸውን በኮሪደር ልማት ስም ያለበቂ ካሳ ተነጥቀው ከተማ ዳርቻ ላይ ተጥለዋል። 

ይህ በማር የተለወሰ መርዝ፣ ከተማዋን ለማዘመን እንደሚደረግ ተደርጎ የሚቀርብ ቢሆንም፣ አገዛዙ “መጤ እና ወራሪ” ብሎ በፈረጀው ላይ የወጠነው የዘር–ማፅዳት ዘመቻ (ethnic cleansing campaign) አካል መሆኑ መላ ኢትዮጰያዊያን የሚያውቁት የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ ሂደት፣  “በህጋዊ ማፈናቀል” ከነዋሪው የተቀማው የመሃል ከተማ አንደኛ ደረጃ መሬት ብዙ ቢሊዮን ብሮች የሚያወጣ በመሆኑ፣ የኦህዴድ ባለሥልጣናት እና ሎሌዎቻቸው ያለምንም ሀፍረት እየተከፋፈሉ በወላጃቸው ሕወሓት ዘመን የተጀመረውን የፖለቲካ እና ንግድን ጋብቻ አስቀጥለዋል። 

ስለዚህም፣ የተከበርኸው የአዲስ አበባ ህዝብ ከምርጫ 97 ታሪካዊ ምርጫ በስተቀር ከአብራክህ የወጡ እውነተኛ አማራጭ ተወካዮችህ የተስተፉበት ምርጫ እንዳልተካሄደ ግምት ውስጥ አስገብተህ እና በዘንድሮው “7ኛው ምርጫ” ተብዬ ደግሞ ወይ ተፈናቅለህ ወይ ለመፈናቀል ተራህ እስኪደርስ እየጠበቅህ በመሆኑ፣ አፈናቃይህ የሆነው አገዛዙ ባቀነባበረው ድራማ ላይ ታድሚ እና ተሳታፊ በመሆን በራስህ ጥፋት ላይ አሻራህን ማኖር የለብህም። ከምርጫ እለት ዋዜማ ጀምሮ በርህን ዘግተህ ቤትህ በመቀመጥ ወይም በግዳጅ የምትሳተፍ ከሆነም የድምፅ መስጫ ወረቀቱን በማበላሸት ተቃውሞህን  እንድትገልፅ ጥሪ አቅርበንልሃል። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ይህ ጥሪያችን ተሳካም አልተሳካም፣  የአዲስ አበባ ትግል ዳግም እንዲቀጣጠል የምናደርገውን ትግል ይበልጥ እንደምናጠናክር በዚህ አጋጣሚ ልንገልፅልህ እንወዳለን። አዲስ አበቤዎች እየተሰባሰብን ነው።

 የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!!

አገዛዙ ሀገርን እንደሀገር፣ ሕዝብን እንደሕዝብ የሚያስቀጥል ሳይሆን፣ በተቃራኒው፣ በከፋፍለህ ግዛ ስልት ሕዝብን ከሕዝብ ጋር እያጋጫ የሥልጣን ዘመኑን እስከተቻለው ድረስ ለመለጠጥ እየሰራ የሚገኝ እና የሥልጣን ዘመኑ ሲያበቃም እንደ ወላጅ አባቱ ሕወሓት ሀገር በትኖ እና ጄኖሳይድ ፈፅሞ ለመሄድ የቋመጠ የከንቱዎች ስብስብ ነው።

የአማራን ሕዝብ በማንነቱ እየለየ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንፁሃንን አፈናቅሏል፣ ጨፍጭፏል። በአማራ ሕዝብ ላይ መደበኛ የጄኖሳይድ ጦርነት ከአወጀ ድፍን ሶስት ዓመታት የሞላው ሲሆን፣ ኦሮሚያ ክልልንም የጦር ወንጀል የሚፈፅምበት የጦርነት አውድማ አድርጎታል። በትግራይም ሌላ ዙር አውዳሚ ጦርነት ለማድረግ ከፍተኛ መዋዓለ–ንዋይ እየፈሰሰበት የሚገኝ ዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህ ሁሉ አገዛዙ ሥልጣን ላይ ከወጣበት ግዜ አንስቶ የጠፋው ከአንድ ሚሊዮን በላይ የህዝብ ህይወት አለበቃ ብሎት ነው።

- Advertisement -

በአገዛዙ ድፍን የአማራ ክልል ሕዝብ በመደበኛ ጄኖሳይድ ጦርነት አበሳ እየተለበለበ ባለበት፣ በኦሮሚያ እና መሰል ክልሎች ጦርነት እና በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ሆኖ ዜጎች በየዕለቱ እየታፈኑ በሚዘረፉበት፣ በሚገደሉበት እና ስርዓተ አልበኝነት የሀገሪቱ ዓይነተኛ መገለጫ ሆኖ እያለ፣ ትግራይ ክልል ከሞላ ጎደል እንደ ሌላ ሀገር ሆኖ ከኢትዮጰያዊያን ወገኖቹ በተለየበት ሁኔታ፣ በአገዛዙ የምርጫ ድራማ ላይ ያለምንም ተቃውሞ መሳተፍ ማለት ጦርነቱ፣አፈናው፣ ግድያው፣ ማፈናቀሉ፣ መለያየቱ እና በኑሮ ውድነት እሳት መገረፉ ተባብሶ እንዲቀጥል ወይ መፍቀድ ወይ አይቶ አንዳላየ መሆን ነው ብሎ ታሪክ በእኛ ዘመን ላይ እንደሚፈርድ ሊታወቅ ይገባል።

ስለሆነም፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝባችንም ከቻልህ በምርጫው ላይ ባለመሳተፍ፣ አገዛዙ እንድትሳተፍ የሚያስገድድህም ከሆነ የድምፅ መስጫ ወረቀቱን በማበላሸት የአገዛዙን ገመና እርቃን እንድታወጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ስንተባበር እንጠነክራን፣እናሸንፋለን !!!
የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት፣
ግንቦት 17፣ 2018 ዓ.ም።

በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

_

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News