Homeአበይት ዜናጋዜጣዊ መግለጫየጨረባው ምርጫ ዴሞክራሲን አያዋልድ፣ መፍትሔ አይፈይድ

የጨረባው ምርጫ ዴሞክራሲን አያዋልድ፣ መፍትሔ አይፈይድ

Advertisement
World Wide Travel Group

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ) 

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ከቅድመኹኔታዎችአለመሟላትናከነጉድለቱ፣ መሠረታዊ የኾኑ የሀገር ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በንግግር፣ በድርድርናበጥልቅውይይት መኾን አለበት በሚል ሩቅና አዋጭ እሳቤ፣ የውስብስብ ችግሮችመፍቻየሀሳብየበላይነት መኾኑን አስልተን፣ በዚኽ ከደረጃ በታች በኾነ ምርጫቀርቶ በእውነተኛምርጫምቢኾን የገዘፈውና የተወሳሰበው ሥርዓት ወለድና መጠነ ሰፊ ችግር ማስወገጃመንገድንግግርናድርድር ነው በሚል እና ከውጭ ኾኖ ተባለ ከማለት በተጨባጭነውሩን ለማጋለጥእጅግበተቀዛቀዘ ስሜት በተወሰኑ አስቻይነት አላቸው ባልንባቸው አካባቢዎችተወስነን ወደምርጫውገብተናል። በሂደቱ ላይ እንደአቅም የአገዛዙን የነውር ገመና በማጋለጥና መሰልየፖለቲካየበላይነትን የተጎናጸፍንበት ነው። 

ውጤቱ እና በኹሉም አካባቢዎች የተፈጸሙ ችግሮች ገና ተጠቃለውያልመጡቢኾንምበሂደቱከቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ዕለትና የምርጫ ማግስት ኾነን ስናየውከነግዙፍእንከኑ፣ ከአሳሳቹ97% የአስቻይነት ሪፖርትና ትንተና፣ ከኢሕአዴጋዊ የጥርነፋ ውርስ ባህርይ/co-opted/እና99.9% የጥቅለላ አባዜና ጉምዥታ ያልተላቀቀ፣ በዓይነቱም ኾነ በድርጊቱ በታሪክከሚታወቁትየጨረባ ምርጫዎች ያልተለየ መኾኑ ገሃድ የወጣ ነው። በቅርብ ታሪካችን እንዳየነውይኽልማድበእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ እጅግ የተወሳሰበውንም የሀገራችንን ችግር ከድጡወደማጡከመውሰድ የዘለለ ዴሞክራሲን አያዋልድም፣ መፍትሔም አይፈይድም! ውጤቱምምንምቢኾንየትኛውም ዕጩ በትብብሩ ስም ምክርቤት እንዳይገባና ቢገባምፍጹምተቀባይነትየሌለውነው።በዚኹ አጋጣሚ ከነበዛ እንከኑም ቢኾን በጠባቧ ቀዳዳ የቦርዱኃላፊዎችንና ውስን ድርጅቶችላደረጉትና እያደረጉ ላለው ጥረት እውቅና አለን። 

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አገዛዙ ለዘመኑ በማይመጥንና ከባህርይ አባቱ በወረሰውየጨረባምርጫ ራሱን ለንግሥና ከማጨት ወጥቶ የስልጣን ምንጭና ባለቤት ሕዝብብቻመኾኑንተረድቶ የሕዝብን ድምጽ እስከሚያከብር ትግሉን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲኾን በቅርቡሕዝብንያሳተፈ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ የተሟላ መግለጫየሚሰጥይኾናል።

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እንዲኹምዓለምአቀፉ ሚዲያ ከሰሞኑላደረገው የላቀ አስተዋጽዖ እውቅና እየሰጠን አኹንም እንደጀመረውየኢትዮጵያን ጉዳይበቅርበትእንዲከታተል፣ ግፎችን እንዲያጋልጥ፣ አገዛዙ ሸብረክ ብሎ ከፖለቲካ ኃይሎችጋር እስከሚደራደር ምንም ዓይነት እውቅና የመስጠት የሚመስል መልዕክት ከማስተላለፍእንዲቆጠብ እንጠይቃለን። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ያ ባይኾን በኢትዮጵያውያን ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ፣ ለንጹሓን እልቂትቦምብእንደማቀበል፣ የግፉ አጋፋሪ እና ከኢትዮጵያውያን ጥቅም በተቃራኒ የቆሙእንደኾነ አድርገንእንቆጥረዋለን። 

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! 
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት – ለኢትዮጵያ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም 
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News