Homeአበይት ዜናአከራዮች ኪራይ ከጨመሩ በሕግ ይጠየቃሉ ተባለ

አከራዮች ኪራይ ከጨመሩ በሕግ ይጠየቃሉ ተባለ

Advertise Here
Advertise here
መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ
መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ

ቦርከና ዜና

የቤት ኪራይ መጨመር የሚችለው አከራይ ሳይሆን መንግስት ብቻ ነው ተብሏል።

አዲስ አበባ ውስጥ ሰኔ 30 የሚያበቃውን የቤት ክራይ ውል ተንተርሶ አከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለተከራዮች እያሳወቁ ነው። አንዳንዶቹ አከራዮሽ ቤቱን እፈልገዋለሁ ውጡ / ቤቱ ተሽጧል ውጡ በማለት ቤት ተከራዮች እንዲለቁ ግፊት እያሳደሩ ይገኛሉ።

ከቤት ኪራይ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ “ተከራዮች በህግ የተሰጣቸው መብታቸውን በደምብ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል። አከራዮችም መብትና ግዴታቸውን በአግባቡ መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።

አንድ ሰው ግዴታ ያለበት 2 ዓመት አንድን ሰው ሊያከራይ ነው። ግዴታው ሁለት አመት ነው ከዛ በላይ መጨመር ይችላል (ጊዜውን)። ስለዚህ አከራዩ ‘ ዋጋ ጨምር ‘ ማለት አይችልም። ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው። በአመት አንድ ጊዜ ሰኔ 30 ላይ በመጣው የዋጋ ጥናት መሰረት ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው።

2017-2018 በጀት አመት ላይ አምና ዋጋ ተጠና የጨመረ ዋጋ ስላልነበረ በነበረው ነው የሚቀጥለው ብለን አሳውቀን በነበረው ነው የቀጠለው። ዘንድሮም ዋጋ እያጠናን ነው። ስለዚህ የዋጋ ጥናቱ በሚመልሰው መልስ መሰረት ወይ በነበረት ይቀጥላል አሁንም አልያም የጨመረ ዋጋ ካለ በይፋ መንግሥት ያሳውቃል። እስከዛ ድረስ አከራዮች ዋጋ ጨምሩ የማለት መብት የላቸውም ፤ አሰራሩም አይፈቅድላቸውም።

ተከራዮችም መብታቸውን መጠቀም አለባቸው። አከራይ ‘ ዋጋ ጨምር ‘ ስላለው ብቻ ዋጋ መጨመር የለበትም። ውላቸው እኛ ጋር አለ። ውላቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ ነው። ውላቸው ውስጥ ሆነው ዋጋ መጨመር ስለማይጠበቅባቸው እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም በቅርባቸው ወረዳ አለ ስራ አስፈጻሚ የሚመራው ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አለ ፣ ክፍለ ከተማም አለ ወረዳው ካልፈታ ክፍለ ከተማ ይፈታል፣ ቢሮ እኛም ጋር አለ። እነዚህ ቦታዎች ላይ እየመጣ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።

አከራይ ዋጋ ጨምር ስላለው ብቻ የሚጨምር ተከራይ ካለ መብቱን እየተጠቀመበት አይደለም።

_

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News