Homeአበይት ዜና" እራሴ ፈተና አውጥቼ እፈትናለሁ" ህወሃት

” እራሴ ፈተና አውጥቼ እፈትናለሁ” ህወሃት

Advertisement
World Wide Travel Group

“ማንኛውም ክልል የሀገር አቀፍ ፈተና የማውጣት እና የመፈተን ስልጣን የለውም” የፌዴራል መንግስት

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ

ቦርከና ዜና

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በራሱ ፈተና አውጥቶ ተማሪዎችን እንደሚፈትን የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ገለጹ።

ኃላፊው ” ሰኔ 29 ቀን ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ በወረቀት ሊፈተኑ የነበሩ 15,349 ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ምክንያት ፈተናው ስለቀረባቸው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዳይጓዙ ተነግሯቸዋል ” ብለዋል። “ፈተናው በአውሮፕላን የሚመጣና በፌዴራል ፖሊስ የሚጠበቅ በመሆኑ፣ ወደ ትግራይ እንዳይላክ የሚያደርግ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ” ያሉት ኃላፊው ” የሚኒስቴሩ ውሳኔ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“የክልል ካቢኔ የፈተና ወረቀቱ በወቅቱ እንዲላክ ለፌዴራል መንግሥት ደብዳቤ አስተላልፏል። እስካሁን አውንታዊ ምላሽ አላገኘም ” ብለዋል። በዚህም ትምህርት ቢሮው የራሱን ፈተና አዘጋጅቶ ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ኃላፊው፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የራሱን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ወስኖ ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስገባ ገልጸው ” የፈተናው ጊዜም ወደፊት ይፋ ይደረጋል ” ብለዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮን ” እራሴ ፈተና አውጥቼ እፈትናለሁ ” የሚለውን ውሳኔ በክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች፣ ውሳኔው በተማሪዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በመጥቀስ ከፍተኛ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ “በራሴ ፈተና አዘጋጅቼ እፈትናለሁ ” ማለቱን ተከትሎ፣ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴራል መንግሥት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ታማኝ የመረጃ ምንጭ ” ይህን ፈተና የማዘጋጀት ስልጣን የፌዴራል መንግሥት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ ነው ” ያሉ ሲሆን፤ ማንኛውም ክልል የሀገር አቀፍ ፈተና የማውጣት እና የመፈተን ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው አስታውቀዋል።

የክልሉ ” እራሴ ፈተና አውጥቼ እፈትናለሁ ” የሚለው አካሄድ ፍጹም ቅቡልነት የሌለው መሆኑን የገለጹት አመራሩ፣ ” እንፈትናለን ብለው ከወሰኑና ፈተናውን ከሰጡ የፈተናው ውጤት ምንም አይነት ተቀባይነት ስለማይኖረው የምስኪን ተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ጉዞ ነው የሚያበላሹት ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ቀደም ብሎ በትግራይ ክልል በተካሄደው የኦንላይን ፈተና ወቅት የነበረውን ሁኔታ ያነሱት አመራሩ ፤ የፌዴራል ፀጥታ አካላትና ፈታኞች በአግባቡ ስራቸውን እንዳይወጡ ጫና ተደርጎባቸው እንደነበር ገልጸዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ለአብነትም ለጸጥታ ማስከበር ስራ የተሰማሩ አካላት እንኳን መሳሪያ እንዳይዙ የማድረግ ጫና እንደነበረባቸው ጠቅሰው፣ በወቅቱ የተማሪዎች ቀጣይ ህይወት ጉዞ እንዳይበላሽ ሲባል ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው በጫና ውስጥም ቢሆን ታግሶ እንዲሰጥ ማድረጉን አስታውሰዋል።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena 

- Advertisement -

1 COMMENT

  1. አይ ወያኔ ሃገርና ህዝብን መቀለጃ እንዳደረገ ሊያልፍ ነው? በድንገት ለራሱ ወታደራዊ ምልመላ እንዲያመቸው ግንቦትን የትምህርት ዘመን ማብቂያ ያደረገው ወያኔ አሁን ደግሞ ራሴው በራሴ እፈተናለሁ እያለን ነው። ይህ የሚያሳየው ከትግራይ ወደ ተለያዪ የዓለም ሃገራት የተዘረጋው ትግራይን ሃገር የማድረግ ጥማት አንድ ገጽታ ነው። ከጥንስሱ ከመገንጠልና ከመገንጠል ውጭ ሌላ ዓላማ የሌለው ይህ ድርቡሽ ድርጅት ዛሬም በ 11ኛው ሰአት ላይ ባህሪውን አልቀየረም። ከትግራዪ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ስም ጋር አብሮ የተለጠፈውን የፈረደበት ድክትርና አሽቀንጥረህ ጥለህ የሰውየውን ቃላት ስትመዝን በራሱ አስቦ በራሱ ተንፍሶ የማይኖር የወያኔ አሽከርና ተላላኪ መሆኑ ለመረዳት አያዳግትም። ለዚህ ነው ትግራይ ተገነጠለችም አብራም ከቀሪው የሃገሪቱ ክፍል ጋር ቀጠለች የሃበሻ ህዝብ የመከራ ዝናብ ምንጭ ሁና ትቀጥላለች የምንለው። ሲጀመር በህዝቡ ስም የነገድትና የሚነግድት የሩቅና የቅርብ የወያኔ ካድሬዎችና መሪዎች ልብ አውላቂዎች ዛሬ የተናገሩትን ሳይነጋ የሚንድ ከእውነት ዓለም በእጅጉ የራቁ እጃቸው በሰዎች ደም የተነከረ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ የእብድ ጥርቅሞች ናቸው።
    አሜሪካ ቢጮህ አውሮፓ ቢንጫጫ ብልጽግና ተው ቢል ሽማግሌ ቢላክ ለሰላም እጃቸውን አንሰጥም ብለው ዛሬም የጦርነት ዝግጅት ላይ የሚገኙት። የክልሉ ትምህርት ተጠሪ ተበደልን ለምን ይህ ይሆናል የሚለው እሳቱ የበለጠ እንዲቀጣጠል እና የትግራይ ህዝብን ለክፋት ለማነሳሳት የሚጠቀሙበት የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ እንጂ ለትግራይ ተማሪዎች አንድም ቀን አስበው አያውቁም። ከእንደ እነዚህ አይነት በዘርና በቋንቋቸው ጢቢራቸው ከዞረ የክልል ጎጠኞች ጋር ምንም አይነት የፓለቲካ ህብረት ቢፈጠር ወንዝ አያሻግርም የምንለው ለዚህ ነው። የፋኖ ከወያኔና ከሻቢያ ጋር ጥምረት መፍጠር አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች እንዲሉ እንጂ እነዚህ ሁለት የብሄር ድርጅቶች ለኢትዮጵያ መፈራረስና አሁን ለገባንበት የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ዋና ተጠያቂዎች ናቸው። ሰበባቸው ብዙ፤ መፈከራቸው ፉርሽ፤ አላማቸው ግብ አልባ የሆኑት እነዚህ የዝንተ ዓለም የብሄር ሰካራሞች ለህዝባቸውም ሆነ ለሌላው መከራ ከማዝነብ የተሻለ ነገር አልፈጠሩለትም። ይህ የትግራዪ የራስ ፈተና አውጥቶ በራስ የመፈተን ወሬም ከዚሁ በብሄሩ ከሰከረው የእብዶች ስብስብ የሚመነጭ መራራ ፈሳሽ ነው። ወያኔና ሻቢያ እያሉ፤ በሃገሪቱ የክልል ፓለቲካና የመገንጠል ህገመንግስቱ እያለ ገና ብዙ ገመና እናያለን። ለመኖር ወንድምና እህትህን የምትገልበት ምድር ላይ ሰላም ይመጣል ብሎ መገመት ራስን ማታለል ነው። ለዚህ ነው የጀብደኞችና የዘረኞች አወዳደቅ የሮም አወዳደቅ የሚሆነው። ለዚህ ነው አማሟታቸው ሳያምር እንደ ቆሻሻ ጊዜ አሽቀንጥሮ የሚደፋቸው። እድሜ ልክ ክፋትን እየተጋቱና እያስጋቱ በተንኮል ብቻ ብልጣ ብልጥ ሆኖ መኖር አይቻልም። ለወያኔም ለሻቢያም ለብልጽግናም በየብሄሩ ትጥቅ አንስተው በህዝባቸው ስም ለሚነግድት ታጣቂዎች ሁሉ ሊያውቁ የሚገባቸው ሃገርን በማተራመስ፤ በማሰር በመግደል፤ በማፈናቀልና በአፈሙዝ ሃይል ህዝብን ጸጥ ማሰኘት አይቻልምና ሌላ መላ ምቱ። የዘር ፓለቲካውን አክ እንትፍ በሉት። ሰውን በሰውነቱ ብቻ መዝኑት። የሃገርና የዓለም መሳለቂያ ህዝባችን አታድርጉት። መገዳደሉን ግርግሩን፤ ማሰር መፍታቱን፤ ማሳደድን በዘመናት ሁሉ አድርገነዋል። በዚህ ምክንያት መጣ የተባለ ለውጥም ካለ ትሻልን ትቼ ትብስን ነው የሆነው። ስለሆነም ለሰላም በሰላም ለመኖር የጦርነት አስተሳሰባችን እንቀይር። በመገንጠልና በማስገንጠል የሚገኝ አንድም ፍሬ የለም። የትግራይ የትምህርት አመራርም የሃገሪቱ የትም/ሚኒስቴር የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ ፈተናው እንደሆነው ሆኖ እንዲያልፍ ቢያደርግ መልካም ነው። ያለበለዚያ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ስለሚሆን ማንም ቢሆን የወያኔን የፈተና ውጤት የሚቀበል የለምና የተማሪዎችን ጊዜ አታቃጥሉ እናንተ ሽንኮች!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News