Homeዜና42.7 ቢሊየን ብር ገቢ አትርፈናል - ኢምግሬሽን

42.7 ቢሊየን ብር ገቢ አትርፈናል – ኢምግሬሽን

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በበጀት አመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠት መቻሉንና የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች 23 ማድረሳቸውን ገልጸዋል።

አክለውም 1,046,286 ቪዛ፣ 32,952 ትውልደ ኢትዮጵያውያን መታወቂያ እንዲሁም 21,163 ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ከ42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ስኬታማ ስራ መሰራቱም የተገለፀ ሲሆን፥ በአየር እና በየብስ ድንበር አለማቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ለ7,225,691 ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው፤ 433 የውጭ ዜጎችና 4ሺህ 450 ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ 4ሺህ 883 ዜጎች በሐሰተኛ ሰነድ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጽሙ ተይዘው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በተጨማሪም 25ሺህ 407 ኢትዮጵያውያን እና 29ሺህ 606 የውጭ ሀገር ዜጎች በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ ተይዘው ተጠያቂ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሯ በበጀት አመቱ ስድስት ሚሊዮን የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን ይህን ሂደት ለመምራት የተለዩ የዲጂታል አማራጭ መተግበሪያ እና ስረአት መዘርጋቱን ዋና ተናግረዋል።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ኤክስ ፡ @zborkena 

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News