የምክክር ኮሚሽኑ ችግር እንደገጠመው አረጋገጠ

ቦርከና ዜና
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከቀናት መዘግየት በኋላ በመጪው ሰኞ ሙሉ በሙሉ ወደ ምክክር እንደሚገባ አስታውቋል።
ኮሚሽነር መስፍን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አርዕያ ከምክክሩ ራሳቸውን አግልለው የቆዩ ግለሰቦች እና ፓርቲዎች እየተቀላቀሉ መሆኑን ተናግረዋል።
ነገርግን ኮሚሽኑ ስለገጠመው ችግርና የምክክር ሂደቱ መዘግየት በተመለከተ ጋዜጠኞች ጥያቄ ቢያቀርቡም ለመመለስ ፍቃደኝነት አላሳዩም።
ይሁን እንጂ ከባጅ ማደል እና ከተመካካሪዎች አቀማመጥ ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግሮች እንደገጠመው ተናግረዋል።
መስፍን ጉባኤው ያጋጠሙትን መጠነኛ ችግሮች በመቅረፍ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ዋናው ስራው እንደሚገባም ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ በአጠቃላይ በሂደቱ ከአስተባባሪዎች ጋር ሰባት ሺህ መሆናቸውን ገልጿል።
4000 ተሳታፊዎች እና 3000 አስተባባሪዎች በድምሩ 7000 ሰዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ በሂደቱ ላይ ሰፊ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል ከመሳተፉ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ቀላል ያሏቸው ችግሮች ማጋጠማቸውን አብራርተዋል።
የተሳታፊዎች አቀማመጥ መደበላለቅ መኖሩንና ኮሚሽኑ በተቋማት ምደባ ላይ አንዳንድ ክፍተቶች ታይተዋል ያሉ ሲሆን እንደ የሃይማኖት አባቶች ከተገቢው ቦታ ውጭ የተመደቡበት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ቦታ ላይ የተሰባሰቡበት ሁኔታ ተከስቷል ብለዋል።
ኮሚሽኑ እነዚህን የአቀማመጥ እና የስራ ክፍተቶች በዚህ በሁለቱ ቀናት ሙሉ በሙሉ እንደሚያስተካክል አስታውቋል።
በምክክር ሂደቱ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት ፕሮፌሰር መስፍ፣ ከሰኞ ጠዋት እስከ ማታ በየቦታው ተከፋፍለው ስራዎቻቸውን በሰፊው ማከናወን እንደሚጀምሩም አረጋግጠዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena







Well, the very ugly/ disgraceful damage has been made when the Professor accepted to be the leading figure of the body that was born as a good baby of a ruling party in order to fool and manipulate the people who have been victims of being fooled for so many years!!!
It is really sad to see well educated individuals like the professor who totally damaged not only their educational status but also their personalities 😭!