Homeአበይት ዜናራስን በራስ የማስተዳደር መብታችንን እናረጋግጣለን - ደብረጽዮን

ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችንን እናረጋግጣለን – ደብረጽዮን

Advertisement
World Wide Travel Group
ደብረጽዮን

ቦርከና ዜና

በፌዴራል መንግሥቱ የተቋቋመውን ጊዚያዊ አስተዳደር በሀይል አፍርሶ ስልጣን የያዘው የህወሓት ቡድን አሁንም ከፌደራል መንግሥት ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብቷል።

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በትናንትናው እለት ምክር ቤታቸውን ሰብስበው አወያይተዋል።

ደብረፅዮን የፌደራል መንግስቱ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ የትግራይ ህዝብን ዳግም ለመውረር እየሰራ ይገኛል ሲሉ ወንጅለዋል።

የትግራይ ህዝብ አሁን ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመታደግና ያሉትን መሰረታዊ እና ወሳኝ የህዝብ ጥያቄዎች በመመለስ የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማረጋገጥ ለነገ የማይባል ስራ መሆኑን ተገንዝበን እነዚህን የህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት ለመስራት እቅድ ይዟል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

አሁን ላይ ያጋጠመንን የህልውና አደጋ በመመከት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በማረጋገጥ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች ትግራይን እንፈጥጢብለዋል።

ህወሃት የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲፋጠን በትኩረት እንደሚሰራም ለምክርቤቱ አስረድተዋል።

በደብረፅዮን የሚመራው ህወሀት በጄነራል ታደሰ ወረደ የሚመራውን ጊዚያዊ አስተዳደር አፍርሶ ስልጣን በሀይል ከተቆጣጠረ በኋላ ከፌደራል መንግስት ጋር ግልጽ የሆነ አለመግባባት ውስጥ ገብቷል።

የፌደራል መንግስት ለጄኔራል ታደሰ ከለላ ባለመስጠቱ ታደሰ በህወሓት የቁም እስር ሰለባ ሁኗል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

መንግስት በህገወጥ መንገድ ስልጣን በያዘው የህወሓት ቡድን ላይ የወሰደው እርምጃም ይሁን ያወጣው መግለጫ የለም።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena 

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News