
ለትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራንና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች
ጉዳዩ፡- የአማራ እና የትግራይ ሕዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ሐገረ-መንግሥት አንድነት አደጋ የሆነውን የጥፋት ቡድን በጋራ መታገል ይመለከታል፡፡
ከጅምሩ የኢትዮጵያን የጋራ ማንነት ክዶ ለ‹‹ታላቋ ትግራይ›› የአገር ምስረታ የተነሳው ህወሓት፣ በዓለም የፖለቲካ ታሪክ የሚጠላውን ሀገርና ሕዝብ የመራ ብቸኛው ድርጅት ስለመሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የተሰወረ ሐቅ አይደለም፡፡ ይህንን እውነታ የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራንና የፖለቲካ መሪዎች በጊዜ ሂደት ተረድታችሁታል ብለን እናምናለን፡፡
በህወሓት የጥፋት ሴራ ደም ያልፈሰሰበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም፡፡ ‹‹ለብሔሮች እና ብሄረሰቦች መብት ታገልኩ›› ቢልም በገቢር የኢትዮጵያን ልጆች ለሥልጣኑ የበላይነት ሲል እርስ በርስ ሲያጋጭና በመካከላችን በሚፈጠረው ቅራኔ የፖለቲካ ትርፍ ሲሰራ የኖረ የጥፋት ቡድን ነው፡፡ ይህንኑ የጥፋት ዓላማውን ዛሬም ቢሆን የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነቱ እንዲፋታ እና እርስበርስ እንዲከፋፈል የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡
የህወሓት የፖለቲካ ግብ በአማራ ቁልቁለት እንዲሁም ሕብረትና አንድነቷን ባጣች የተዳከመች ኢትዮጵያ ስር የበላይነቱን ማረጋገጥ ስለመሆኑ ከፈጠራቸው የውሸት ትርክቶች፣ የጥላቻ ፖለቲካው እና ከግዛት ተስፋፊነቱ መረዳት ይቻላል፡፡
መላው የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች እንደሚያውቁት ህወሓት ለሠላሳ ዓመታት በወረራ ይዟቸው በነበሩ በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ነው፡፡ ለዚህ የወንጀል ድርጊት የሰውና የጅምላ መቃብር ምስክሮችን አስረጅ ምሳሌ አድርገን እናቀርባለን፡፡ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ‹‹አማራ ነኝ›› ማለት የጥቃት ምንጭ ነበር፡፡ 2008 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የህዝቡን ጥያቄ አንግቦ በመነሳት ሕጋዊ እና ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ጥያቄውን ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርብም፤ ህወሓት ጉዳዩን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከምድረ ገፅ አጠፋለሁ ብሎ በመነሳት ኮሚቴውን ለግድያ፣ እስር እና መሳደድ መዳረጉ እና በመጨረሻም ዜጎች አማራ በመሆናቸው ብቻ ማይካድራን በመሰሉ ቦታዎች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡
አሁን ላይ ያ ሁሉ መከራ አልፎ፣ እነዚህ አካባቢዎች ነጻ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቡ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ እየጠየቀ ያለው፣ ‹ማንነቴ አማራ ነው፤ ማንነቴና አስተዳደራዊ ፍላጎቴ ተከብሮልኝ በአማራ ክልል ስር ልተዳደር› የሚል ነው፡፡
ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ በተከለው የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተነሳ የአማራ ጥያቄ የሌሎችን መብት የሚጋፋና የሚጨፈልቅ እንዲመስል ለማድረግ ሞክሯል፡፡ እውነታው ግን አማራ የሚፈልጋት ኢትዮጵያ ከማንም በላይ አልያም ከማንም በታች መሆን ሳይሆን፡- ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ እና በህግ-ተገዥነት የተመሠረተ ዴሞክራሲ የሰፈነባት ጠንካራ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ያላት አገር ተገንብታ ማየት ነው፡፡
በዚህ መሻቱ ውስጥ በመሰረታዊነት የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ከታሪክ፣ ከሕግ፣ ከሞራል የሚቃረኑ አይደሉም፡፡ የወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ ጉዳይም በዚሁ አግባብ የሚታይ ነው፡፡
ስለሆነም የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች :-
1.ከምስረታው ጀምሮ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ፣ በትርክት፣ በተቋምና በሥርዓት አማራን ሲያጠቃ እና በሌሎች እንዲጠቃ ሲያደርግ፤
2.በግዛት ተስፋፊነቱ ተከዜን ተሻግሮ የስሜን በጌምድር አካል የሆኑትን ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት እንዲሁም የወሎ ክፍለ-ሀገር አካል የሆነውን ራያን በወረራ ወደ ትግራይ ሲያጠቃልል፤
3.በእነዚህ አካባቢዎች ባለርስት ሆነው ይኖሩ በነበሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም፣ በጅምላ ወደ እስራት ሲያግዛቸው፣ ከቀያቸው በገፍ ሲያፈናቀላቸው…ወዘተ እውነታውን እናንተ ታውቁ ነበር፡፡
ይህ አልበቃ ብሎ፣ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝን ከጀርባ በመውጋት፣ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ክህደት በመፈጸም ደም አፈሳሽ ጦርነት መቀስቀሱ፣ ይህንን ተከትሎ በማይካድራ፣ ጭና፣ ቆቦ፣ አጋምሳ ወልድያ፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸና፣ ኮምበልቻ፣ በተለያዩ የአማራና አፋር አካባቢዎች የፈሰሰው የንጹሃን ደም ጠባሳው ዛሬም አልሻረም፡፡
ህወሓት እነዚህን ወንጀሎች የፈጸመው በ ‘ትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭነት’ ስም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ አሁንም የጦርነት ዝግጅት እያደረገ ያለው በትግራይ ሕዝብ ስም ነው፡፡ ስለሆነም የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ከአማራ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጋር በጋራ በመቆም ‹‹በስሜ ይህ አይደረግም» («Not in My Name») በማለት፣ ከጋራ ጥፋተኝነት ራሳችሁን እንድታድኑ፤ የጋራ ትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የትግራይ ልሂቃን ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ በተለይም ደግሞ በወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ያደረሰውን ግፍና በደል እያዩ እየሰሙ ‹‹በስሜ ይህ አይደረግም» በማለት ፈንታ፤ አንዳንዶች የዘር ማጥፋቱን በሀሳብና በድርጊት ሲደግፉ ታይቷል፡፡ ይህ ታሪክ ከእንግዲህ እንዳይደገም፣ የጋራ ትግል እንድናደርግ ታሪካዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ዛሬም ቢሆን፣ በሕወሓት ፋሽስታዊ ጭካኔ ለአርባ ዓመታት በጅምላ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን አፅም ለቅመን በክብር አሳርፈን አልጨረስንም፡፡ ያረፈብን የታሪክ ጠባሳ ገና አልሻረም፤ አሁንም የወገኖቻችን በደል ፍትህ አልተሰጠም፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የሚመጣ ወንጀለኛ ካለ የሚመጣው ለፍርድ ብቻ ይሆናል!!
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃውሞ ፖለቲካ መሪዎች በትንሹ የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይጠበቃሉ፡፡
አንደኛ፡- ህወሓት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት የአማራ ተወላጆች ላይ ለፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እውቅና መስጠት፤
ሁለተኛ፡- ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በእነዚህ አካባቢዎች የዘር ማጥፋት ወንጀልን ጨምሮ ልዩ ልዩ ግፍና በደሎች ለተፈጸመበት የአማራ ሕዝብ የፍትሕና የካሳ ጥያቄው እንዲመለስለት አጋርነትን ማሳየት፤
ሦስተኛ፡- በትግራይ ሕዝብ ጉያ ውስጥ የተሸሽጉም ሆኑ በስደት ዓለም ያሉ የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በሃሳብ የደገፉ፣ በተግባር ያስፈጸሙ፣ አሁንም ለዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነት እየተዘጋጁ ያሉ የጥፋት ቡድኑ የህወሓት አመራሮች፣ አባላትና አጋሮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳልፎ መስጠት፤
አራተኛ፡- ወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ በታሪክ የአማራ ግዛት መሆናቸውን፣ ድኀረ-1983 በጉልበት ተነጥቀው ተወስደው እንደነበሩ አምኖ መቀበል፤ ናቸው፡፡
የወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ አማራ አስተዳደራዊ ፍላጎቱን በተመለከተ ትላንትም ሆነ ዛሬ ቃሉ አንድ ነው፡፡ ‹ማንነታችን አማራ ነው፤ አስተዳደራዊ ፍላጎታችን በአማራ ክልል ስር መተዳደር ነው› የሚለው ሕዝባዊ መሰረት ያለው ጥያቄ ሊከበርለት ይገባል፡፡ ‹ከትግራይ የሚመጣ ጥሩ ጎረቤት እንጅ፤ አስተዳደር ፈጽሞ አንቀበልም!› እያለ ያለው ሕዝቡ ‹ዛሬ ወደኋላ ላንመለስ ነጻ ወጥተናል› የሚል አቋሙን በአደባባይ ደጋግሞ አሰምቷል፡፡ ስለ ሕዝቡ ማንነት ከራሱ በላይ ምስክር ሊሰጥ የሚችል አንዳች አካል የለም፡፡ ከእንግዲህ ከሕወሓት ሊቃጣ የሚችል የትኛውም ዓይነት
የጦር ወረራ ከአሸባሪነት እና ከአገር አፍራሽነት ተግባር ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡
የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ፣ የራሳችንን አሳልፈን አንሰጥም አልን እንጂ የማይገባንን ለሁለታችንም ተፈጥሯዊ ወሰን የሆነውን ተከዜ ወንዝን አልፈን አልጠየቅንም፡፡ እኛ የናንተን ትግራዋይ ማንነት እና ወሰን እንደምናከብረው ሁሉ እናንተም የኛን አማራዊ ማንነት እና ወሰን ልታከብሩ ይገባል፡፡
የወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አማራ ሕዝብ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሚጋራቸው ሕዝቦች ቀርቶ ከጎረቤት ሀገራት ወንድም ሕዝቦች ጋርም በሰላም፣ በፍቅርና በመከባበር መኖር የሁልጊዜም ምርጫው፤ የጥንት ታሪኩም አካል ነው፡፡
በሌላ በኩል በአንዳንድ የትግራይ ልሂቃን ዘንድ ችግርን ወደ ውስጥ ከማየት ይልቅ ችግሩን ውጫዊ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ ይታያል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ወደ ውስጡ በማየት ግማሽ ክፍለ ዘመን በላዩ ላይ ተጣብቆ የቆየውን ሕወሓትን ኦዲት ሊያደርገው ይገባል! ተጠያቂነትን የማያውቀው የዚህ ድርጅት አሰራር የትግራይን ሕዝብ ዘመድ እያሳጣው፣ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል፡፡ እንደ ሰላም ወዳድ ጎረቤት ምክራችን የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የትግራይን ውስጣዊ ቀውስ ወደ ውስጥ በመመልከት እንጅ ውጫዊ በማድረግ የሚገኝ መፍትሔ፤ የሚቀየር ሁኔታ የለም፡፡
በመሆኑም በትግራይ ሕዝብ ስም የሚነግዱ የጥፋት ቡድኑ አመራሮች፣ እያደረጉት ያለው አውዳሚ የጦርነት ዝግጅት፣ በተግባር በመቃወም፤ አውዳሚ ጦርነቱን ለማስቀረት ከወገናችሁ የአማራ ሕዝብ እና ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ ታሪካዊና ሞራላዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኀበር
ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም.
ሁመራ-ጎንደር ኢትዮጵያ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena







የአማራ ህዝብ ጠላት በየጊዜው እንደ አሸን እየተራባ በሃገርና በውጭ ሳይቀር በፈጠራ ታሪክ ራሳቸውን አስከረውና ሌሎችን ግተው ዛሬ ላለንበት የአፓርታይድ የብሄር ክልል ደርሰናል። በቅርቡ አዲስ አበባ ራስ ገዝ ትሁን በኦሮሚያ ክልል ትጠቃለል የሚሉት የቁም ከብት ፓለቲከኞች የበቀሉት እንደዚህ ካለው ለእኔ ብቻ ከሚለው የቋንቋና የብሄር ስካር ነው። በታሪካችን ውስጥ አሁን ሃገሪቱ እንዳለችበት ያለ ዘመን ተፈጥሮ አያውቅም። ዞር ብለን የመሳፍንት ዘመን እየተባለ የሚጠራውን እንኳን ብንመለከት በምድሪቱ አንድ ወደ ሌላው ስፍራ ተዛውሮ ሰርቶ፤ ቤት መስርቶ የመኖር መብት ነበረው። አሁን እንሆ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተቀምጠን የዛሬ መቶ ዓመት ሚኒሊክ ይህን ሰራ ያን አረገ ብለን ሃዘን የምንቀመጥ ጉዶች ተፈጥረናል። የሚያሳዝነው እነዚህ የዘር ሰካራሞች ስለ አለፈው ነገር ክስና ኡኡታ ሲያሰሙ ራሳቸው ከበደል በደል እየፈጸሙ ሰውን ዘቅዝቀው ሰቅለዋል፤ ለስብሰባ ጠርተው በዘራቸው ተለይተው በጥይት ተደብድበዋል፤ ከሞትና ከጉዳት የተረፉት ተወልደው ካደጉበት ስፍራ መጤ ናችሁ በማለት ተባረዋል። ይህ ክርፋታም የብሄር ፓለቲካ ሁሉን እውር የሚያደርግ የሰውን ሰውነት የሚክድ በመሆኑ አክ እንትፍ ሊባል በተገባ ነበር። ግን ወያኔ በመቀሌ፤ አማራው በፋኖ በኩል፤ ኦሮሞው በኦላና በሌሎች የብልጽግና መንግስት ተለጣፊዎችና በራሱ በብልጽግና በኩል የሚወሸከተው ሁሉ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ አይነት በመሆኑ አወዳደቃችን የሮም እንደሚሆን ቀድሞ የታወቀ ጉዳይ ነው። ብሄርተኝነት የአፓርታይድ አንድ ገጽታ ነው። የደብረጽዪን ፉከራ፤ የወያኔ ከሻቢያና ከሌሎች ሃተፍ ተፍ ከሚሉ የቁም ሙት ድርጅቶች ጋር መጣመር ከሞትና ከረሃብ ከመከራና ከለቅሶ ሌላ የሚያመጣው አንድም ለውጥ አይኖርም። አበው “ሲኖሩ ልጥቅ ሲወጡ ምንጥቅ” ይላሉ። ይህ ሄደት መለስ የሆነው የወያኔ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት በሃገሪቱ ላለው የውጭና የውስጥ የፓለቲካ ውጥንቅጥ ዋናው መንስኤ ነው። ጠ/ሚ አብይ ለአማራ ህዝብና ከፋን ለሚሉት ታጣዊ ወገኖች ለወያኔ ያደረገውን ማጎብደድ በሶስት እጅ ብቻ ለአማራ ታጣቂዎች አድርጎ ቢሆን ኑሮ ዛሬ ጦርነት በአማራ ክልል አይኖርም፤ እስር ቤቱም በአዛውንት አማራዎችና እናቶች ባልተሞላም ነበር። ግን ጥላቻው ከአማራ ህዝብ ጋር የሆነው የኦሮሞ ስብስብ ከወያኔ ቢከፋ እንጂ አይሻልም። እስቲ ማን ይሙት የሰሜን ጦርን በተኛበት የመቱትና ያስመቱት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየተንፈላሰሱ አልፎ ተርፎም የመንግስት አካል ሆነው እያገለገሉ እንደ ታዲዎስ ታንቱ ያሉ አዛውንት፤ እንደ መስከረም አበራና ሌሎችንም እንበለ ፍርድ ባላጎረም ነበር።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሞኝ ነው። ስትሾም ያጨበጭባል፤ ስትሞት ያለቅስልሃል (አሁን ላይ በብሄር ተለይቶ ለቅሶ)፤ ስትታሰር ጸጥ ይላል። ከዘመናት በፊት ጄ/አማንን ገድሎ በስፍራው ጄ/ተፈሪ በንቲን ሲተካ ሰዎች ተሰብስበው እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወደ ጄኔራሉ ቤት ያመራሉ። የጄ/ባለቤት ነገር የገባቸው አይ እንኳን ደስ አለሽ አትበሉኝ። ፈጣሪ ያውጣሽ እንጂ ማለታቸው ዛሬ ፒ ኤች ዲና ሌላ ነገር በስማቸው ዙሪያ የለጠፉ ስመ ምሁራን ከሚረድት በላይ እኛ የሴት ወይዘሮ ጊዜውን መረዳታቸውን ያሳያል። መማር ፉርሽ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። እኝህ ወይዘሮ ባላቸውን ብቻ ሳይሆን ልጃቸውንም ጭምር አጡ። የሃበሻ ምድር የእንባ ምድር ናት። መግደልና መገዳደል የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። አንዲት የትግራይ እናት እንዲህ ትለናለች ” እኛ ማስለቀስ እንጂ ማልቀስ አናውቅም”። ልጆቹን ወደ ጦር ሜዳ መርቆ የሚሰድ ለዚያውም ለእርስ በእርስ እልቂት የስነ ልቦና ችግር እንዳለብን በግልጽ ያሳያል። ልጅ ምንም ቢከፋ ወደ እሳት አይገፋም ነበር። ግን ምርጫ የለም። እንግዲህ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ መግለጫም መታየት ያለበት ራስን ለመከላከልና ለማዳን የሚደረግ ጥሪ እንደሆነ ነው። ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸመው በደል ሰማይ የደረሰ ነው። በ 17 ዓመቱ የጫካ ዘመኑ፤ በ27 ዓመቱ የስልጣን ዘመን በጥናት በተደገፈ መልኩ የጀግና ዘሮች ናቸው፤ ሰው የማስተባበር አቅም አላቸው የተባሉትን ሁሉ እስከ ልጅ ልጆቻቸው እንዳጠፋቸው መረጃው አለ። ወያኔዎች ሰዎች ሳይሆኑ አራዊቶች ናቸው። ከነፍስ አባታቸው ከሻቢያ ቀድሞ የተጋቱትን የአማራ ጥላቻ አባዝተውና አሰራጭተው እንሆ ዛሬ ኦሮሞውም ሆነ ሌላው የችግሬ ምንጭ ሁሉ የአማራ ህዝብ ነው በማለት እያሳደደው ይገኛል። ግን ይህ ሁሉ ፉርሽ የሚሆንበትም ጊዜ ይመጣል። ለገባው አብሮ ተከባብሮ መኖር ምርጫ የማይገኝለት ብልሃት ነበር። ያ ግን አልሆነም እንዲያውም ከግብጽ/ሱዳን/ኤርትራ እና ከሌሎችም ጋር ሆነን ብልጽግናን ከስልጣን እናወርዳለን ይሉናል። ከዚያስ? ብልጽግናን ከስልጣን ለማውረድስ አቅሙ አለ ወይ? የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ ነውና ያም ይህም ልክ እንዳለፈው ፓለቲካችን ይንጣጣል። ውጤቱ ግን ባዶ እንደሚሆን ከአሁኑ የታወቀ ነው። ከግብጽ/ከሱዳን/ከኤርትራ ጋር ቂጥ የገጠመ ድርጅት የእነርሱ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ በራሱ አስቦ የሚንቀሳቀስ አለመሆኑን አንባቢ መረዳት ይገባዋል። ግራም ነፈሰ ቀኝ ለአማራ ህዝብ ራሱን ከወያኔና ከሌላም ጥቃት ለመከላከል ሴት ወንድ ሳይል ዝግጅት ማድረግ ያለበት አሁን ነው። ዋ በህዋላ እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት ሆኖ መውጫ እንዳይጠፋ ቀን ሳለ ማበሩና ማቀድ ወራሪና አጥፊ ሃይሎች ለመመከት መደራጀት/መዘጋጀት/የቅርብና የሩቅ ፕላን ማውጣት ተገቢ ነው ባይ ነኝ። እዚህ ላይ ጸለምት፤ ጸገዴ፤ ወልቃይት የተባሉት ስፍራዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊ መኖሪያ እንጂ ለአማራ ብቻ የተሰጠ ምድር አለመሆኑን ነው። ሃገርን ሃገር የሚያሰኘው አንድ መሆኑ ነውና። ግን በእነዚህ ስፍራዎች ያሉትን ኗዋሪዎች አባሮ ሌላ ማስፈር ግን አይቻልም፤ እንዳይሆንም አስፈላጊውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ራስን ማዘጋጀት ነው። ማይካድራ አይደገምም። እንደ ገና በግ ተጎትቶ የሚታረድ አማራ ዛሬም ወደፊትም መኖር የለበትም። የዘረኞችና የብሄርተኞች ብልሃትና ተንኮል ሊገባን ይገባል። ተግባራቸው ለእኔ ብቻ ነው። ከአሁን በህዋላ የሚሞኝላቸው አንድም የአማራ ህዝብ አይኖርም!