
ቦርከና ዜና
ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕጽ በድብቅ ሲያስገቡ ተይዘዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን በሞት የተቀጡት ሰኞ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም. በአሲር ግዛት መሆኑን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሳዑዲ መንግስት የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር 17 ደርሷል።
ሰኔ 16 አምስት፣ ሰኔ 1 አራት፣ ሚያዚያ 13/2018 ዓ/ም ሦስት ኢትዮጵያውያን በሞት ተቀጥተዋል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው፣ የፀጥታ አካላት ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር አውለው ባደረጉት ምርመራ ጥፋቱን መፈጸማቸው በመረጋገጡ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል ብሏል።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ቢጠየቅም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ብይኑን በማጽናቱ እና በሸሪዓ ሕግ መሠረት የንጉሣዊ ትዕዛዙ ተፈጻሚ አንዲሆን መደረጉ ተገልጿል።
የሞት ቅጣቱ ዓላማ የዜጎችን ደኅንነት ለመከላከል እና ነዋሪዎችን ከአደንዛዥ ዕፅ አደጋ ለመጠበቅ እንዲሁም አደንዛዥ ዕፅን ለሚያዘዋውሩ እና ለሚያስፋፉ አካላት በሕግ የተደነገጉትን እጅግ ከባድ ቅጣቶች ተፈጸሚ ማድረግ መሆኑን ተጠቅሷል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena







ያሳዝናል ከፍተኛ የሃሽሽ ተጠቃሚዎች አረቦች ሁነው ሳለ አመጣችሁ ተብለው ተገደሉ ሃሽሽ አጫሹ አረብ ግ ን ቁጭ ብሎ ይስቃል፡፡ በንጉሱ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ካጠፋ ወደ ሃገሩ ተመልሶ ቅጣቱን እንሰጠዋለን እንጅ እዚህ አይታረድ ብለው ንጉሱ ውል አስረው ነበር ትግሬዎች ስልጣን ላይ ወጡ ገንዘብ ተቀብለው ስምምነቱን አፈረሱ ስራቸው ሁሉ ጥፋት የሆኑት የትግሬ ልጆች ዛሬም በየሶሻል ሚዲያው ከቤተሰቦቻቸው የወረሱትን ዘረፋ፤አንዱን ካንዱ ማበጣበጥ፤ህብረተሰቡን ዝቅጠት ውስጥ መክተት ዋና ስራቸው አድርገው ተያይዘውታል፡፡ የመንግስቱንም ደካማ ጎን በመገንዘባቸው የመቀሌው ህወአት ህጋዊ ተወካይ ሁነው አገሩን ምስቅልቅሉን አውጥተውታል አብይንም መቃብሩን እየቆፈሩለት ነው፡፡ ትላንት መንገድ በመምራት ዛሬ ላይ ደግሞ መሃል በመሆን በዘረፉት ብር አማካይነት የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡