Homeዜናኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ሆነች

ኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ሆነች

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና

መንግስት የኑሮ ውድነት የተረጋጋ ነው ቢልም ሀገሪቱ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት በማሳየት የመጀመሪያውን ደረጃ መያዟ ተገልጿል።

በ2026 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ከ10 ዋና ዋና የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የዋጋ ንረት ያስመዘገበች ሀገር መሆኗን የቢዝነስ ዴይ ዘገባ አመላክቷል።

ከኢትዮጵያ በመቀጠል ግብፅ እና ኬንያ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ተብሏል።

ከመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ጋር ተያይዞ የጨመረው የነዳጅ ወጪ ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ታይቶ የነበረውን የዋጋ መረጋጋት ወደኋላ መመለሱ ዘገባው ጠቁሟል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ከ2025 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4.1 በመቶ ነጥብ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፤ ይህም ከግብፅ 2.4 በመቶ ነጥብ፣ ከኬንያ 2.0 በመቶ ነጥብ እና ከጋና 1.5 በመቶ ነጥብ ብልጫ አለው ተብሏል።

በጥናቱ ከተካተቱት ሁሉም 10 ሀገራት በዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ካለፈው ዓመት የበለጠ ከፍተኛ የዋጋ ንረት አስመዝገበዋል።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News