
ቦርከና ዜና
በስዊድን ጎተንበርግ በተካሄደው የጎቲያ ኮፕ የእግር ኳስ ውድድር ላይ የተሳተፉ 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎችና የቡድን መሪዎች መጥፋታቸውን የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ የጠፉት ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ከእነሱ ጋር አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቡድን መሪዎች አብረው ጠፍተዋል ብሏል።
ይህ የታወቀው በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ሲሆን ያረፉበት ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ አባላቱ ያለ ምንም ማስታወቂያ ለቀው መሄዳቸውን ካረጋገጠ በኋላ ለፖሊስ ማሳወቁን ቦርከና ከዬተቦርግስ ፖስት ዘገባ መመልከት ችሏል።
የስዊድን የጠፉ ሰዎች የመርማሪ ክፍል ተወካይ ኤሊኖር ሃልዲን ግለሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ አለመመለሳቸውን አረጋግጫለሁ ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በስዊድን የሚገኘው ኤምባሲ ስለ ኢትዮጵያዊያኑ መጥፋት ያሉት ነገር የለም።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






