Homeነፃ አስተያየትየአማራውን የህልውና ትግልና የቀጠናውን የኃይል አሰላለፍ በሚመለከት (አክሎግ ቢራራ ዶ/ር)

የአማራውን የህልውና ትግልና የቀጠናውን የኃይል አሰላለፍ በሚመለከት (አክሎግ ቢራራ ዶ/ር)

Advertisement
World Wide Travel Group

ለሚዲያ የተዘጋጀ የምክረ ሐሳብ

  አክሎግ ቢራራ (ዶር)

የአማራ ሕዝብ ደህንነትና መብት ምንድን ነው?

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የጥላቻ ጦርነት እና የሥልጣን ተትኪነት ሳይሆን የዜግነት፣ የፍትሕና የሰላም፤ የእውነተኛ ዲሞክራሲ ትግል ነው። ይህ ሰነድ ለሬዲዮ፣ ለቴሌቪዥን፣ ለዩቲዩብ ወይም ለጽሑፍ ሚዲያ የሚሰራጭና ሊስተካከል የሚችል ረቂቅ ነው።

መግቢያ

የአማራ ሕዝብ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያጋጠሙትን ግድያ፣ መፈናቀል፣ እስራት፣ ንብረት ውድመት፣ የፖለቲካ መገለልና የደህንነት ሥጋት በቀላሉ ማየት አይገባም። የሕዝቡን ሕይወት፣ ክብር፣ መሬት፣ ባህል፣ ፖለቲካዊ ውክልናና ኢኮኖሚያዊ ዕድል ማስከበር ሕጋዊና ተገቢ ጥያቄ ነው። ችግሩን የተባባሰ ያደረገው የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ነው። ይህ ገዢ ክፍል ዋና የህልውና ጠላት መሆኑ አያከራክርም። 

የጠላትነቱን ዘግናኝነትና አረመኔነት ለመገንዘብ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር የሚያካሂደውን ግድያና ጭካኔ ማየት በቂ አይደለም። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በገዳማት የሚኖሩትን አዛውንት፤ መነኩሴዎች፤ ቀሳውስት በድሮን የሚጨፈጭፍ አረመኔ ነው። ለማዘናጋት ሲል፤ በአንድ በኩል እርቅና ሰላም እያለ ይሰብካል (ብሄራዊ ምክክር ኮሚሺን በሚል የዳቦ ስም) በሌላ በኩል ግን ቀን ከሌሊት ንጹሃንን በከባድ መሳያ ይጨፈጭፋል። ረሃብን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመ ዜጎችን ያደኸያል፤ ያስርባል፤ በገፍ እንዲሞቱ ያደርጋል። የምክክር ኮሚሽኑ ዋናው ተቆጣጣሪ ዐብይ አህመድ ነው። ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ለዐብይ አህመድ ነው። ቅቡልነት የሚፈልገው ውይይቱ ሕዝባዊ ነው በሚል ብልህነት፤ ፕሬዝደንት ሆኖ እንዲያገለፍግል ነው። ሌላው ሁሉ ሪፎርም ሽፋን መሆኑን እንድተገነዘቡት እፈልጋለሁ። በሪፎርም ስም እኮ የኢትዮጵያን ሕዝብ በድህነት እየቀጣው ነው።

ዐብይ አህመድ ከግራኝ አህመድ የባሰ ጨካኝና ከፋፋይ ሰው ነው። ዋና ጠላት አድርጎ ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የሚያካሂደው በአማራና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች ላይ መሆኑን መላው የዓለም ሕዝብ ያውቀዋል፤ ድምጽ ግን አያሰማም። 

ስልቱ ከፋፋይነት ነው። አማራውን ከአማራው፤ ከትግራዩ እና ከኦሪሞው ጋር ያናክሳል፤ ትግራዩን ከአማራው ጋር፤ ኦሮሞውን ከሲዳዳማውና ከሌላው ጋር ያናክሳል። ኦሮሞውን ከሶማሌው ጋር ያጋጫል። ይህ መለያው ሆኗል። 

ዐብይ አህመድ አሊ እስካልተወገደ ድረስ፤ አንኳን የኢትዮጵጵያ ህዝብ ቀጠማውም ሰላምና እርጋታ አይኖረውም። ይህ ሰው  ገድድላል፤ ያፍናል፤ ያስርባል፤ ይቀማል። ይህ ሰው ጦረኛ ነው። ሰው እንደ ቅጠል ማርገፉን የተለመደ አድርገን መቀበላችን ሊገባኝ አልቻለም።

- Advertisement -

በጥቅሉ ስገመግመው ይህ ሰው በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተጠላ ነው፤ ኦሮሞውንም፤ ትግራዩንም፤ ጋሞውንም ወዘተ ጨምሮ። 

ሆኖም አማራውን በሚመለከት “ህልውናን ማስከበር” ማለት ሌላን ሕዝብ ጠላት ማድረግ፣ ሲቪሎችን ማጥቃት፣ የብሔር ጥላቻን ማስፋፋት ወይም በቀልን የፖለቲካ መሣሪያ ማድረግ አይደለም። በአንድ ወቅት፤ የደርግ መንግሥት ሲገዛ ኢትዮጵያ እሰራ ስለ ነበረ፤ የኔ ዘመዶችና ወዳጆች “ይህ ባሪያ አይገዛንም” ብለው ሲናገሩ እጣላ ነበር። “መንግሥቱ ኃይለማሪያም ጨካኝ ነው ብትሉ እስማማለሁ። ኦሮሞ በመሆኑ ግን ስትስደቡት የምትስድቡት እና የምታስቆጡቱ መላውን የኦሮሞን ሕዝብ ነው፤ ራሳችሁንም ጭምር ነው” እል ነበር። ጨምሬም፤ አማራውን “አህያ” የሚሉትንስ ምን ስም ልታወጡላቸው ነው?” እየልኩ እተች ነበር። 

ዛሬም፤ ትክክለኛው ትግል የሕይወት ጥበቃ፣ የእኩል ዜግነት፣ የፍትሕ፣ የፖለቲካ ተሳትፎና የሕግ የበላይነት ትግል መሆን አለበት። ይህንን የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ይተገብረዋል የሚል እምነት የለኝም፤ እልቂቱን፣፤ የእርስ በርስ የቀጠና ጦርነቱን ይፈልገዋል።

በአማራ ክልል የመንግሥት ኃይሎችና የፋኖ ቡድኖች ግጭት በ2025 መቀጠሉን፣ በተፋላሚ ወገኖች የተፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች፣ በሲቪሎችና በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ የደረሱ ጉዳቶች መኖራቸውን የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶች ያመለክታሉ። የተጎዳው ተራው ሕዝብ ነው።

መደምደሚያ

በአሁኑ ወቅት በብዛት የሚወራው ፖለቲካ “የጽምዶን” የአገር ውስጥና ውጭ የኃይል አሰላለፍ ጉዳይ ይመለከታል። እኔ የዚህን ኃይል አሰላለፍ የምገመግመው መንግሥት መር ከሆነው የአማራው የህልውና ትግል ጋር በማያያዝ ነው። የአገር ውስጥና የውጭ የኃይል አሰላለፍ የአማራውን ክልል የጦር አውድማ ካደረገው የአማራውን የህልውና ትግል ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለኝ። መላውን አማራ በያለበት ለባሰ እልቂት ሊያመቻችበት የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋትም አለኝ። የኃይል አሰላለፉ ቡድን የአማራውን ፍትሃዊ ትግል አስቀድሞ እውቅና ከሰጠው፤ የአማራ መሬቶችን (ወልቃይት፤ ጠገዴ ወዘተ) ቀይ መስመር መሆናቸውን በይፋ ካስታወቀ እና በዘላቂነት ትግሉ ለጋራ አገር የጋራ ያጋራ ትግል ያስፈልጋል በሚል ከተንቀሳቀሰ አማራጭነቱ አግባብ አለው።

ለማንኛውም፤ የአማራው ክልል ሳይለይ የጦር አውድማ እንዳይሆን ሁላችንም ድምጽ የምናሰማበት ወቅት አሁን ነው።

የችግሩ እምብርት

1. የዜጎችን ሕይወት በእኩልነት የማይጠብቅ የመንግሥት አሠራር መኖሩ።

በማንነት ምክንያት የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ መፈናቀሎችና ጥቃቶች በፍጥነት የማይከላከሉ፣ ከተፈጸሙም በኋላ ተጠያቂዎችን የማይይዙ ተቋማት የዜጎችን እምነት አፍርሰዋል። የአማራው ሕዝብ የሚፈልገው ልዩ መብት ሳይሆን በሀገሪቱ የትም ቢኖር በእኩልነት እንዲጠበቅ ነው።

2. የተጠያቂነትና የፍትሕ እጥረት መኖሩ።

ያለፉ ግፎች ተጣርተው ፍትሕ ሳያገኙ አዳዲስ ጥሰቶች ሲደጋገሙ በቀልና ትጥቅ እንደ መፍትሔ እንዲታዩ ያደርጋል። በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለክስና ያለፍርድ ተይዘው እንደቆዩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አድርጓል። በሰሜኑ ጦርነት የብዙ ሽህዎች ህይወት እረግፎ እስካሁን በሃላፊነት የተጠየቀ አካል ወይንም ግለሰብ የለም።

የሃላፊነትና የተጠያቄነት መርሁ ግልጽ መሆን አለበት። ጥፋት የፈጸመ ማንኛውም የመንግሥት ኃይል፣ ታጣቂ ቡድን ወይም ግለሰብያልተፈቱ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የወሰን ጥያቄዎች መኖራቸው። በግል ይጠየቅ። የአንድን ወንጀል በሌላ ወንጀል ማስተባበያ ማድረግ አይገባም።

3. ያልተፈቱ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የወሰን ጥያቄዎች መኖራቸው።

የአካባቢ ወሰን፣ የተፈናቃዮች መመለስ፣ የአስተዳደር ውክልና፣ የክልልና የፌዴራል ሥልጣን ግንኙነት በጦር መሣሪያ ሊፈቱ አይችሉም። በሕግ፣ በሕዝብ ፈቃድ፣ በገለልተኛ ምርመራና በድርድር መፈታት አለባቸው።

4. የፖለቲካ ውክልና መበታተን ሁኔታውን አባብሶታል።

የአማራን ሕዝብ ማን ይወክላል የሚለው ጥያቄ በአንድ ፓርቲ፣ በአንድ ታጣቂ ቡድን፣ በአንድ የዲያስፖራ ድምፅ ወይም በአንድ ክልላዊ መንግሥት ብቻ ሊመለስ አይችልም። አሳታፊ መሆን አለበት፤ ግልጽነት ያለው መሆን አለበት። 

ወኪልነት ከገበሬዎች፣ ከሴቶች፣ ከወጣቶች፣ ከተፈናቃዮች፣ ከምሁራን፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከነጋዴዎች፣ ከሲቪል ማኅበራትና ከተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶች የተዋቀረ መሆን አለበት።

5. የሲቪክና የሚዲያ ምህዳር መጥበብ እና ያሉትም መበታተን ብዢታዎች ፈጥሯል።

ገለልተኛ ሚዲያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና የሲቪል ማኅበራት በፍርሃት ውስጥ ሲሠሩ፣ ሕዝቡ ታማኝ መረጃና ሰላማዊ የተቃውሞ መድረክ ያጣል። በ2024 መጨረሻና በ2025 መጀመሪያ በታወቁ የመብት ድርጅቶች ላይ እገዳ መጣሉን የመብት ተቋማት ዘግበዋል።

6. የሕዝብን ችግር ወደ “ሁሉም ወይም ምንም” የብሔር ጦርነት መቀየር አደገኛ ሂደት ነው።

“ሁሉም ኦሮሞ፣ ሁሉም ትግራዋይ፣ ሁሉም አማራ” ብሎ የሚፈርጅ የጅምላ ትርክት የሕዝብን ደህንነት አያስጠብቅም። ወንጀል የግለሰብ፣ የቡድን ወይም የተቋም ተጠያቂነት ነው፤ ለመላው ብሔር ሊጫን አይገባም።

ተራው፤ በተለይ ድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌላው ጋር አልተጣም። ቢጣላ ኖር ኢትዮጵያ እስካሁን ትፈርስ ነበር። ጥላቻውን አፍ ከፍተው የሚቀስቅሱት እኮ እነ ዐብይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ ወዘተ ናቸው። ይህ አስተሳሰብ እስካልተቀየረ ድረስ የፈለግነውን ያህል ሮሮ ብናሰማ ሁኔታው አይቀየርም። 

ኢትዮጵያዊያን ከዘውግ ፖለቲካ መጥቀው ወደ ዜግነት ፖለቲካ ካላመሩ ሰላምና እርጋታ ሊኖር አይችልም።

የአማራ ሕዝብ እንዴት ቢታገል ይሻላል?

1. ትግሉን በግልጽ የሲቪል መርሕ ላይ ማቆም

የትግሉ ዋና ጥያቄዎች እነዚህ መሆን አለባቸው፦

በኢትዮጵያ የትም የሚኖር አማራ እንደ ሙሉ ዜጋ እንዲጠበቅ፤

በማንነት ምክንያት ግድያና መፈናቀል እንዲቆም፤

ጦርነት ያለ ቅደመ ሁኔታ እንዲቆም፤

ተፈናቃዮች በደህንነት፣ በፈቃዳቸውና በክብር እንዲመለሱ፤

የጥሰት ፈጻሚዎች በግለሰብ ደረጃ እንዲጠየቁ፤

ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና ሚዲያዊ ተሳትፎ እንዲሰፋ።

2. ከታጠቀ መበታተን ይልቅ የጋራ የሲቪል ቻርተር ማዘጋጀት

ይህ የሁሉም ግዴታ ነው።

የአማራ ማኅበራት፣ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ ተፈናቃዮች፣ ሴቶችና ወጣቶች የሚፈርሙት አጭር የመርሕ ሰነድ ያስፈልጋል። 

ምን የሚል ሰነድ?

በሲቪሎች ላይ ጥቃትን ይከልክል፤

የብሔርና የሃይማኖት ጥላቻን ይቃወም፤

የሀገሪቱን ችግር በሕግና በድርድር ለመፍታት ቃል ይግባ፤

የማንኛውንም ሌላ ሕዝብ እኩል መብት ያክብር፤

የውጭ መንግሥት ተኪ የመሆንን አደጋ ይከልክል።

3. ማስረጃን የትግል መሣሪያ ማድረግ

ጥሰቶች በተጎጂዎች ክብርና ደህንነት ተጠብቀው መመዝገብ አለባቸው። ቀን፣ ቦታ፣ ተጎጂ፣ ተጠርጣሪ አካል፣ ምስክሮችና የሕክምና መረጃዎች በሙያተኞች ይሰብሰቡ።

ያልተረጋገጠ የሟቾች ቁጥር፣ የተቀነባበረ ምስልና የቆየ ቪዲዮ ማሰራጨት ለጊዜው ስሜት ሊቀሰቅስ ቢችልም የሕዝቡን ታማኝነትና የፍትሕ ጉዳይ ያዳክማል።

4. የሕግና የፖለቲካ አቅም መገንባት

የሕግ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ ዲፕሎማቶችና የፖሊሲ ባለሙያዎች ያሉበት ገለልተኛ ምክር ቤት ሊቋቋም ይገባል። የሕዝብ ጥያቄ ከቁጣ መግለጫ ወደ ተግባራዊ የፖሊሲ አማራጭ መቀየር አለበት።

5. ሰላማዊ ጫናን ማጠናከር

ሕጋዊ ሰልፎች፣ የሕዝብ እምቢተኛነት፤ የፊርማ ዘመቻዎች፣ የፍርድ ቤት ክሶች፣ የፓርላማ ጥያቄዎች፣ የምርምር ሪፖርቶች፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችና ሰላማዊ የኢኮኖሚ ትብብሮች ከጦርነት የበለጠ ዘላቂ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ። ጦርነት በተናጥል ወደ ፍትህ፤ ወደ ሰ፤አም፤ ወደ እኩልነት፤ ወደ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አያሸጋግርም። ተዛማጅ ሕዝብዊ ስራዎች መተግበር አለባቸው።

ከማን ጋር መተባበር ይገባል?

መተባበር በብሔር ስም ሳይሆን በመርሕ ላይ መመሥረት አለበት። ህዝብ ከህዝብ ጋር እንዲገናኝ፤ እንዲተሳሰብና እንዲሰራ ከፍተኛ ጥረት መደረግ አለበት። ሥልጣን የሕዝብ ነው ማለቱ ብቻ በቂ አይደለም፤ ይተግበር።

1. ከሌሎች ተጎጂ ማኅበረሰቦች ጋር

ሕዝብ ከሕዝብ ጋር አልተጣላም። ሁሉም ተጎድቷል። የኦሮሞ፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የሶማሌ፣ የጉራጌ፣ የአገው፣ የቅማንትና የሌሎች ማኅበረሰቦች ሲቪሎችም በግጭት፣ በመፈናቀልና በመንግሥታዊ ወይም በታጣቂ ጥሰቶች ተጎድተዋል።

የአማራ ደህንነት የሌሎችን ደህንነት በማዳከም ሊገኝ አይችልም። “ማንኛውም ሲቪል አይገደል፣ ማንኛውም ሕዝብ አይፈናቀል” በሚለው የጋራ መርሕ ላይ ሰፊ የዜጎች ጥምረት መገንባት ይገባል።

2. ከሲቪል ማኅበራትና ከሙያ ተቋማት ጋር

ከጠበቆች፣ ከሐኪሞች፣ ከመምህራን፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሴቶችና ወጣቶች ድርጅቶች፣ ከተፈናቃዮች ማኅበራት፣ ከነጋዴዎችና ከገለልተኛ ሚዲያዎች ጋር መሥራት ይገባል።

3. ከሃይማኖትና ከማኅበረሰብ ጋር። 

4. በኦህዴድ ብልጽግና ከተጎዱትና በኢትዮጵያዊነታቸው ከማይደራደሩት ጋር፤ ለምሳሌ የደቡብ አርበኞች። 

ከማን ጋር መተባበር አይቻልም? 

የብሄር ወይንም የእምነት ጥላቻ ካላችው፤

ድብቅ አጀንዳ ካላችው፤ አንተን አጋር አድርጊ እኔ ዓላማየን አሳካለሁ ከሚሉት፤

ከኢትዮጵያ እንገነጠላለንና ዋና ግባችን የራስችን ሃገርና ሃገረ መንግሥት እንመሰርታለን ከሚሉት፤ 

ከኢትዮጵያ የውጭ አገር ጠላቶች ጋር ስልታዊ ግንኙነት (Strategic alliance with Ethiopia’s mortal enemies)/ ካላቸው። 

የአማራው ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ጋር አልተጣላም። አብሮና ተሳስሮ የመኖር ልምድ ያለው ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ባለውለታ ሕዝብ ነው። 

እኔ አማራ ላልሆኑት ሁሉ የማስተላልፍው ጥሪ የአማራው ደም ደማችን ነው በሚል ትግሉን ተቀላቀሉ ነው። አማራውንና ሌላውን በጨካኙ አገዛዝ የሚሰቃይ ሕዝብ እሮሮ ከሰማን ኢትዮጵያን ለማዳን የምንችልበት እድል አለን። ለማዳን የምንችልው ደግሞ በአንድነት ስንታገል ብቻ ነው። 

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News