Homeአበይት ዜናጋዜጣዊ መግለጫ‹‹ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ››

‹‹ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ››

Advertisement
World Wide Travel Group
ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር

ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የአደራ ቃል ነው፡፡

(የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት የትግል ሰማዕታት መታሰቢያ አስመልክቶ ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር የተሰጠ መግለጫ)

ከ1983 ዓ/ም እስከ 2013 ዓ.ም. የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብ የትህነግ ኢህአዴግ መዋቅራዊ የአገዛዝ ጭቆና ሳይበግረው ሕጋዊ እና ሕገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ የአማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በማደራጀት ጥያቄውን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረቡ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ዓ.ም. አንስቶ በትህነግ የደረሰበትን የዘር ማፅዳት ወንጀል ተከትሎ በአማራዊ ማንነቱ ምክንያት ግድያ፣ ስደት፣ ንብረት መወረስ፣ መፈናቀል ወዘተ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ተፈጽሞበታል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማንነት እና ወሰን ትግል በሁለት ትውልድ ቅብብሎሽ ምዕራፍ እዚህ የደረሰ የፍትህ ጥያቄ ነው፡፡ እንዲሁም የአማራ ህዝብ የትግል አስኳል ምልክት ሆኖ በመውጣት ሚሊየኖችን ለትግል ማሰለፍ የቻለ በትውልዶች የመስዋዕትነት ቅብብል ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ፍትሐዊና እውነተኛ የሕዝብ ትግል አጀንዳ ነው፡፡

ከዚህ የትግል ታሪካዊ ምዕራፍ አንዱ ትህነግ ከተፈጥሯዊ ባህሪው በመነሳት ሐምሌ 05/2008 ዓ.ም. የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አመራሮችን በጉልበት አፍኖ በመውሰድ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ደብዛቸውን ለማጥፋት ያደረገው ሙከራ በጎንደር ህዝብ አንድነት፣ የአርበኝነት ውርስ እና አኩሪ ተጋድሎ መራራ የሽንፈት ጽዋ የተጎነጨበት ክስተት ነበር፡፡ በመሆኑ ሐምሌ-05 ትግሉ ከነባሩ ወደ አዲሱ ትውልድ ታሪካዊ የትግል አደራ የተላለፈባት የአማራ ህዝብ ልዩ የትግል ቃልኪዳን እና የአንድነት ሚስጢር የሆነች ከቀን ባሻገር ናት፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ከዚህ ቀጥሎ በመላው የአማራ ክልል ወጣቶች አዲስ የአማራ ተጋድሎ ምዕራፍ በመክፈት ‹‹ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ›› የሚል መፎክር አንግበው ከሐምሌ 24/2008 ዓ/ም ጀምሮ በተለያ ከተሞች ማለትም ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ….. ወ.ዘ.ተ. በትህነግ ኢህአዴግ አንባገነናዊ አገዛዝ አፈሙዝ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ በተለይም ነሐሴ 1/2008 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ የትውልዱ አካል በሆኑ የአማራ ወጣቶች ደም እንደውሃ ፈስሶ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ነፃነት በሰማዕታት የደም አሻራ ማህተም ያረፈበት ታሪካዊ ክስተት መሆኑን እየተዘከረ ይቀጥላል፡፡

ይህ የትግል መስዋትነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ነፃነት የተከፈለ ብቻ ሳይሆን የመላ አማራ ህዝብ አንድነት የተረጋገጠበት፣ በወቅቱ የነበሩ የአማራ ክልል መሪዎች የተፈተኑበት፣ የትህነግ-ኢህአዴግ እብሪት እና አንባገነናዊ አገዛዝ የተገታበት እና ሕዝባዊ ትግል ምንግዜም አሸናፊ መሆኑን የተረጋገጠበት ወርቃማ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ይህ ትውልድ ስለ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ነጻነት ለከፈለው መስዋዕትነት፣ በዚህች ቀን ‹ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ› በማለት ደረታቸውን ለስናይፐር ሰጥተው ከተሰው ወጣቶች አንዱ የሆነውን ወጣት አበበ ገረመው የሰማዕታቱ ምልክት በማድረግ በሥሙ መታሰቢያ ት/ቤት በአብክመ ወ/ጠ ሰ/ ሁመራ ዞን በቃብቲያ ሁመራ ወረዳ እየተገነባ ይገኛል፡፡

የዚህ ዘመን አማራ ወጣት የትግሉ ሰማዕታት በቋሚነት መዘከር፣ የትግላችን የድል ትሩፋቶች መጠበቅ፣ የትግል ቃልኪዳን ማደስ፣ የወቅቱ ፈተናዎች በውል መገንዘብ እና የተከዜ ዘብ ተልዕኮዎቻችን ከዳር ማድረስ እንደሚጠበቅበት እንገነዘባለን፡፡ እንዲሁም ዝክረ ሐምሌ-05 10ኛ ዓመት መታሰቢያ ‹የማይታጠፍ ቃል፣ የማፈይታ ትጥቅ!› በሚል መሪ ቃል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን፣ ሁመራ ከተማ በድምቀት የተከበረው የድል ቀን የዚህ ውጤት ነው፡፡

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ የተከፈለው ዋጋ በአግባቡ መረዳት፣ ታሪክ ሰርተዉ ያለፉት ጀግኖችን ማወደስ፣ በህይወት ያሉ ጀግኖችም ማክበር እና አርአያነታቸውን መከተል አስፈላጊ በመሆኑ ይህን የትውልድ አደራ ከዳር ለማድረስ እና ለመጠበቅ አንድነታችን በማፅናት፣ የትግል ቃል ኪዳናችን በማደስ እንዲሁም የተከዜ ዘብ ተልዕኮዎችን ለመፈፀም ዝግጁ በመሆን ዝክረ ነሐሴ-01 በአማራ ክልል ሁሉም አከባቢዎች ታስቦ እንዲውል ስንል በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ስም ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ማህበረሰብ በመላ የአማራ ሕዝብ እና በፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ትግል የተረጋገጠው ነጻነት በዘላቂነት ለማፅናት በቀደሙት የትግሉ ሰማዕታት ስም የሚከተሉትን የትግል ቃል-ኪዳኖች እንጠብቃለን፡፡

1.   የትግሉ ሰማዕታት በአንድነት ሕይወታቸውን የሰጡለትን የአማራ ሕዝብ የትግል አስኳል ሆኖ ለቀጠለው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን ትግል በዘላቂነት ለመቋጨት እስከመጨረሻው በቁርጠኝነት ፀንተን እንቆማለን!!

2.   ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አንድ እውነት፤ አንድ ማንነት፤ ምንግዜም አማራነት ፅኑ ኢትዮጵያዊነት በሚለው አቋማችን ታምነን፤ እንደ አማራ በአንድ ቤተሰብ፤ እንደ ኢትዮጵያ በአገር ልጅነት በአብሮነት አብረን እንኖራለን! ከአማራዊ አንድነታችን ሊከፋፍሉን፤ ለዘመናት ዋጋ ከከፈልንበት የትግል መሠረታችን ሰበብ እየፈጠሩ ሊያደናቅፉን የሚሞክሩ ኃይሎች ያለምህረት እንታገላቸዋለን!

3.  እልፍ የነጻነትና የፍትሕ ታጋዮች የማይተካ የሕይወት ዋጋ ከፍለውበት በእጃችን የገባውን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ነጻነት በመስዋዕትነታችን እናፀናዋለን እንጂ የሰማዕታትን አደራ አሳልፈን አንሰጥም፡፡

- Advertisement -

4.   ሁሉም ትውልድ የራሱ የዓድዋ ድል አለው፤ ለእኛ ትውልድ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ነጻነት የዘመናችን የዓድዋ ድል ነው፡፡ ይህ ድል ለማፅናት በዚህ መርህ በመታመን ታሪካዊ ኃላፊነታችን ለመወጣት ዝግጁ ነን።

5.   የአባቶቻችን የአርበኝነት ውርስ በመጠበቅ፤ ትሩፋታችን ታሪካዊነት ነውና የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ነጻነት በዘላቂነት ለመቋጨት እንተጋለን።

የማንነት ትግል ታሪካችን በደም የተፃፈው፤ በመስዋዕትነት ያሸበረቀው የአማራ ወጣቶች ዋጋ ከፍለውበት ነው!!!

የማህበረሰባችን ዘርፈብዙ ችግሮች ለመፍታት እንተጋለን!!!

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር
ነሐሴ 01/2018 ዓ/ም 
ሁመራ

የኤዲተሩ ማስታወሻ : በዚህ አምድ ላይ የሚወጡ መግለጫዎች የቦርከናን አቋም ያንጸባርቋሉ ማለት አይደለም፡፡

_

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

ኤክስ ፡ @zborkena 

1 COMMENT

  1. ጀግና ሕዝብ ጀግና ያከብራል

    ያ በለጋ እድሜው የተቀጩዉ አበበ ፎቶ ታይኔ አይጠፋም። ቆራጥ ጀግና ነበር።

    ተባረኩ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News