Homeነፃ አስተያየትበቀይ ባሕር እና በመካከለኛው ምስራቅ ጂኦ-ፖለቲካዊ መድረክ ምን እየተካሄደ ነው…?   

በቀይ ባሕር እና በመካከለኛው ምስራቅ ጂኦ-ፖለቲካዊ መድረክ ምን እየተካሄደ ነው…?   

Advertisement
World Wide Travel Group
ጸሃፊው (ፋይል)

በሙሉዓለም ገ/መድኀን 

“ዓይን ላጠፋ ዓይን” በሚል ሕግጋቱ የሚታወቀው የኢራኑ ግራ እጅ ሁቲ፣ ከዓለም እጅግ ወሳኝ የንግድ የባሕር መስመሮች አንዱ የሆነውን የባብ አል-መንደብ ሰርጥን መቆጣጠሩ፣ ከሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ወደ ቀይ ባህር የተዘዋወሩትን የሳውዲ የነዳጅ ኤክስፖርት መስመሮች ላይ ቀጥተኛ አደጋ ደቅኗል። 

በቀጠናው ተንታኞች ምልከታ ስሌቱ ግልጽ ነው፤ ኢራን ሆርሙዝን ስታንቅ፣ ሁቲዎች ደግሞ ቀይ ባሕርን በማስፈራራት የነዳጅ ዋጋ እንዲንር እና የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ማድረግ ችለዋል። (የዚህ ጽሑፍ መውጫ ላይ ከዚህ ራቅ ያለ የቢሆን ዕድል ምልከታ ያስቀምጣል) የሆነው ሆኖ አሁን ባለው ሁኔታ፣ አሜሪካ ቀውሱን ትፈታለች የሚለውን የቀጠናውን ተስፋ እጅጉን አጥብቦታል። 

ተንታኞቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ ሁቲዎች በባብ አል-መንደብ አቅራቢያ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ ደሴቶችን መቆጣጠራቸው የጨዋታውን አካሄድ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። ይህ ክስተት የኃይል ሚዛኑን የሚለውጥ ከመሆኑም በላይ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በቀጠናው አገራት፣ በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ እጅግ የላቀ ጂኦፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጫና ማሳደርም ያስችላቸዋል።   

የእነዚህ ጸረ-ምዕራብ ብርቱ ታጣቂዎች ሰሞነኛ አፍ ያስያዘ ወታደራዊ ድል፣ በተቆጡ የየመን ወጣቶች ትከሻ ላይ በምታዩቸው ክላሽንኮፍ ብቻ የመጣ አለመሆኑም አንዱ የቡድኑን ብርታት የሚያሳይ ክስተት ሆኗል፤ ይኽም፣ ሁቲዎች የአሜሪካውን እጅግ ውድ አርቴፊሻል ኢንተለጀንሲ የሆነውን ክላውድ መጠቀማቸው መነገሩ ነው። አንትሮፒክ የተባለው የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ የሁቲ ታጣቂ ቡድን ለባሌስቲክ ሚሳይሎች የሚመሩ፣ መቆጣጠሪያ እና የናቪጌሽን ሲስተሞችን ለመገንባት የኩባንያውን ክሎድ የተሰኘውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት መጠቀሙን ይፋ አድርጓል። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ኩባንያው  ይፋ ባደረገው አጠር ያለ መረጃ እንዳመለከተው፣ ሁቲ የጦር መሳሪያዎች ሶፍትዌር ለማልማት ክሎድን በመጠቀም፣ ተራ ስልክ መሰል የበረራ ኮምፒዩተር በመጠቀም የሚመራ ሮኬት፣ ከሁለት ሺሕ ኪሎሜትር በላይ የርቀት ወሰን ያለው ባለብዙ ደረጃ ባሊስቲክ ሚሳኤል፣ እንዲሁም ሃይፐርሶኒክ ሚሳይልን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ ሚሳይሎችን ለማበጀት ሞክሯል። ይህ የታጣቂ ቡድኑ ጥረትም፣ በርካታ ወታደራዊ መሐንዲሶችን ይፈልግበት የነበረውን እጅግ ውስብስብ ስራ በቀላሉ እንዲያከናውን አድርጎታል።   

ይሄን የሁቲዎች ያልተገመተ እና አስደናቂ የተባለ ወታደራዊ እርምጃ ለቀጠናው አገራት የሚያሰጋ ነው፡፡ በመስል የጎረቤት አገራት እንቅስቃሴ መነሳሳት፣ ለመናገር ቀናት ትፈልግ የነበረችው አሥመራ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኦስማን ሳላህ በኩል ድምፆን አሰምታለች። 

የየመን ቀውስ በጦር መሣሪያ ኃይል ሊፈታ እንደማይችል እና የውጭ ኃይሎችም የየመንን ሕዝብ ጽናት ሰብረው ሊረቱት ፈጽሞ እንደማይችሉ በመግለጽ አሥመራ ሰላምን ሰብካለች፡፡ ኦስማን ሳላህ፣ የየመን ሕዝብ ከረጅም ጊዜ መከራው አርፎ ሰላም እንዲያገኝ ሰፊ ዕድል ሊሰጠው እንደሚገባ ጠንከር ባሉ ቃላት ተናግረዋል። 

ሰባት መቶ ማይል የሚረዝም የቀይ ባሕር ጠረፍ ያላት ኤርትራ፣ ከየመን ጋር በጠባቡ የባብ አል-መንደብ ሰርጥ ላይ የ20 የባሕር ማይል ርቀት ብቻ በመጋራት እጅግ ወሳኝ በሆነ ጂኦ-ፖለቲካዊ ምዕራፍ ላይ መገኘቷን ልብ ለሚል የቀጠናው ተንታኝ፣ ይሄን የአሥመራ አቋም ምን ማለት እንደሆነ መረዳት አይከብደውም። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የየመንኗ ሁቲዎች፣ በቀይ ባሕር ጠረፍ በኩል ባደረጉት መብረቃዊ እና ፈጣን ወታደራዊ ዘመቻ፣ ከኤርትራ እና ከጅቡቲ አዋሳኝ መስመሮች ፊት ለፊት የሚገኙትን የየመን የባሕር ዳርቻዎች እና ስትራቴጂካዊ ደሴቶች በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ማዋላቸው በቀጠናው ያለውን ሚዛን ሙሉ በሙሉ መቀየሩን ማስተዋል ይቻላል፡፡

በዚህ ረገድ አሁን ላይ በይፋ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥሩ ውጭ በመሆኑ ሀገሪቱ በተግባር እንደሌለች ይቆጠራል የሚለው የአሥመራ የንግግር/ውይይት ጥሪ ይሄን እውነታ ያገናዘበ ነው፡፡ 

ኢራን በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ላይ እንዳደረገችው ሁሉ፣ ሁቲዎችም በቀይ ባሕር ውስጥ ከሚያልፉ መርከቦች ላይ ክፍያ ሊጠይቁ ይችላሉ ለሚለው ሐሳብ ሲመልሱም፣ ኢራን አነሳች ማለት ኤርትራም ትጠይቃለች ማለት አይደለም በማለት አገራቸው ለዚህ የተለየ አቀራረብ እንደሌላት ኦስማን ሳላህ ጠቁመዋል። 

የቀይ ባሕር ደህንነት ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ከሚደረገው ሰፊ የኢራን ጦርነት ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል ገልጽ ነው፡፡ 

- Advertisement -

የባብ አል-መንደብ እና ሆርሙዝ የአንድ ሰንሰለት ሁለት ጫፎች በመሆናቸው ቀውሶቻቸው ተያያዥ ናቸው። 

በዚህ ረገድ፣ አሥመራ  በቀጣናው ሰላምን ብትጣራም፣ በአካባቢው ሰላም በቀላሉ የሚመጣ አይመስልም፡፡     በርግጥ ኤርትራ ከየመን ጋር ታሪካዊ፣ የዘር፣ የሐይማኖት እና የባህል ትስስር ያላት አገር መሆኗ አሁን የያዘችው የሰላም አቋም ኃላፊነት የሚሰማው ነው፡፡  

ሁለቱ የቀይ ባሕር ዳርቻዎች ለዘመናት የቆየ ግንኙነትም አላቸው። በ1990ዎቹ በሃኒሽ ደሴቶች ቀውስ ምክንያት በኤርትራ እና በየመን መካከል የተፈጠረው መራራቅ፣ ሳይዘነጋ የኤርትራ ደሴቶች ለአካባቢው ሚዛን ማስጠበቂያ፣ የባህር ደህንነት መከበር የማይናቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡   

የሆነው ሆኖ፣ ትራምፕ ኢራንን አሸንፈናል ብለው ባሰቡበት ቅጽበት፣ የየመን ሁቲዎች የባብ አል-መንደብ ሰርጥን በመቆጣጠር የቀጠናውን የኃይል ሚዛን ገለባብጠውታል። እስካለፈው ሳምንት ድረስ የኢራን ጦርነት ለአሜሪካ በከባድ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ወጪ ቢሆንም ቅሉ፣ አሸናፊ እና ተሸናፊ ወደማይታይበት አቅጣጫ እየተቀየረ ያለ ይመስል ነበር። 

ያ እየሆነ ሳለ እንኳን፣ የየመኑ ፕሬዝደነት “የሁቲዎች የተሳሳተ ስሌት ወደ ሙሉ ውድቀታቸው የሚመራ በር ይከፍታል” በማለት በድል አድራጊነት ስሜት መግለጫ ጭምር አውጥተው ነበር። 

የሁቲ ኃይሎች፣ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ወሳኝ የባሕር መተላለፊያዎች አንዱ በሆነው የባብ አል-መንደብ ሰርጥ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞችን እና ደሴቶችን በቁጥጥራቸው ሥር ካዋሉ ስደተኛ ሌሊቶች ተቆጥረዋል። 

ይህ ሽንፈት የሆርሙዝን ሰርጥ ከኢራን ቁጥጥር ሥር ለማስመለስ ሲተጉ የቆዩትን ፕሬዝደነት ዶናልድ ትራምፕን፣ እጅጉን ከባድ የተባለ መራራ ሁኔታ ላይ ጥሎቸዋል። ስለምን ቢሉ፣ አሁን ጠላቶቻቸው በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙትን እና በየቀኑ የዓለምን አንድ ሦስተኛ ያህል የነዳጅ ጭነት የሚያስተላልፉትን ሁለቱንም ወሳኝ የባሕር ሰርጦች በቁጥጥራቸው ሥር አውለዋልና።   

ይህ ያልተጠበቀ ክስተት፣ ሌላ አንድ የማይናወጥ እውነትን በግልጽ አሳይቷል። ባለፉት አንድ ሁለት ዓመታት ውስጥ የኢራን የመቋቋም ዘንግ ወታደራዊ ክንፎች የሆኑት እነ ሃማስ እና ሁቲ፣ የደረሰባቸው መሠረታዊ ውድቀቶች ቢኖሩም፣ ኃይሎቹ ተቃራኒው ወገን ላይ ፈጽሞ የማይታየውን ጠንካራ የርዕዮተ ዓለም እሳት እና የቡድን መንፈስ ይዘው ቀጥለዋል። 

የባህር ሰርጡ አገራት በሁቲዎች ላይ በጋራ የመሠለፍ አቅም ማጣታቸው ትልቅ አሳዛኝ ውድቀት መሆኑም፣ ፕሬዝደነት ትራምፕ በኢራን ላይ የተቀናጀ ስትራቴጂ ለመንደፍ ያሳዩትን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ድክመት በግልጽ ያሳየ ኩነት ሆኗል። 

የመካከለኛው ምስራቅ ተመራማሪዎች እንደሚያነሱትም፣ ሁቲዎች በቀይ ባሕር ውስጥ የባሕር ማጓጓዣ መስመሮችን የመያዝ አቅም የነበራቸው ቢሆንም፣ ባብ አል-መንደብን መያዛቸው ግን በቀጥታ በባሕር ዳርቻው ላይ ተቀምጠው፣ በቀይ ባህር በሚያልፉ መርከቦች ላይ እንዳሻቸው መተኮስ ያስችላቸዋል።  

ሳውዲዎች በድንበራቸው ላይ የተጋረጠውን የሁቲ ስጋት ለማብረድ ለዓመታት ሲዋጉ የቆዩ ቢሆንም፣ አሁን ግን ሁቲዎች ሕጋዊ እውቅና ካለው የየመን መንግሥት እየሸሹ ያሉ ኃይሎች የተውትን እጅግ ብዙ የሳውዲ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና አቅርቦቶችን በቁጥጥራቸው ሥር አውለዋል።     

የሁቲዎቹ ጥቃት፣ እንደቀደመው የሳውዲ እና የሁቲዎች መለስ ቀለስ የሚል ውጊያ በየመን ውስጥ ብቻ ላይገደብ ይችላል የሚለው ስጋት እንዲቀሰቅስ ያደረገው፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሳውዲ ከሌሎች ወዳጆቿ ጋር የመሰረተችው የ”ኢስላሚክ ኔቶ” እየተባለ የሚጠራው ስብስብ መኖር ነው። ሴራው የሚጀምረው እዚህ ግድም ነው፡፡ (ይህን ጥምረት እስራኤል በቀላሉ እንደማትመለከተው ልብ ይሏል)

የቀጠናው የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚገልጹት፣ ባለፈው ነሐሴ ወር በሳውዲ አረቢያ፣ በቱርክ (ዬ) እና በፓኪስታን መካከል የተፈረመው የመካ የጋራ መከላከያ ስምምነት በሁቲዎች ጥቃት ትልቅ ፈተና ውስጥ ወድቋል። 

ስምምነቱ ሲቋቋም የጋራ መከላከያን እና የቀጠናውን ጸጥታ በጋራ የመጠበቅ ኃላፊነት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ በሳውዲ አረቢያ ቀዳሚ አደራጅ መሆኗም፣ ይህ የሁቲዎች ጥቃት አስፈሪ መዘዝ እንዳያመጣ ቢያሰጋ ብዙም የሚያስገርም አይመስልም። 

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ፓኪስታን ወይም ቱርክ ለሁቲዎች ጥቃት ምን ምላሽ ይሰጣሉ የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ አንድ ሳምንት ተቆጥሯል፡፡ 

ሁለቱም ሀገራት ከኢራን ጋር ከሚኖር ግጭት መጠንቀቃቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ሳውዲ አረቢያ ከ2015 ጀምሮ የኢራን ደጋፊ ከሆኑት ሁቲዎች ጋር ስትዋጋ ቆይታለች። 

አሁን ላይ ሪያድ የየመን መንግሥት ወታደሮች ሁቲዎችን መክተው ድል እንዲቀዳጁ ተስፋ ብታደርግም፣ ሁቲዎች ባለፉት ወራት በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ መጥቷል። 

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሁቲዎችን ጥቃት ቢያወግዝም ለስለስ ያሉ ቃላትን መጠቀም መርጧል።  

ቱርክ በሶማሊያ አካባቢ በሚደረጉ የጸጥታ ማስከበር ሥራዎች ምክንያት፣ በየመን አቅራቢያ ወታደራዊ መሠረቶችን መገንባቷን ልብ ይሏል። የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍም የሁቲዎችን ጥቃት አጥብቀው ቢያወግዙም ወታደራዊ ድጋፍ ላይ ከድርጊት ተቆጠበዋል፡፡

ግጭቱ ወደ ሳውዲ ድንበር ተሻግሮ (ቢያንስ) በሚሳይል እና ድሮን የገባ ቢሆንም በሪያድ፣ በአንካራ እና በኢስላማባድ መካከል የተደረገው የጸጥታ ስምምነት ሥራ ላይ መዋል አልቻለም፡፡ 

ስምምነቱ  በአንዱ አገር ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሦስቱም ላይ እንደተፈጸመ ይቆጠራል የሚል ቢሆንም፣ ሁለቱ አገራት ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አልቻሉም፡፡ 

አሜሪካም በልዩ ጥንቃቄ ይዛው የዘለቀችውን ከሳዑድ አረቢያ ጋር የነበራትን የውጭ ግንኙነት በተለይም የደህንነት ጉዳዮች የተመለከተውን ታሪኳን የማይመጥን እጅግ ያልተለመደ ዝምታን መርጣለች፡፡ 

በዚሁ ሁሉ መሀል ሁቲዎች እጅግ ያልተለመለደ ቃልና ድርጊት እኩል አሳይተዋል፡፡ የባብ ኤል መንደብ ሰርጥን ከተቆጣጠሩ በኋላ የአሜሪካና እስራኤል መርኮቦችን አናጠቃም፤ ኢላማችን የሳዑዲ መርከቦች ናቸው ብለዋል፡፡ 

ይህን ቃላቸውን አክብረው ሳምንቱን ዘልቀዋል፡፡ 

ትላንት ሮይተርስ ባወጣው መረጃ ደግሞ የሁቲ ልዑካን ቡድን ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ሚስጥራዊ ውይይት አድርገዋል፡፡ 

እናስ ጎበዝ፣ አማራጭ ያጣችው ሳዑዲ እስራኤልን ከጀርባ ልትማጸን የምትችለበት ጊዜ አልደረሰምን…? 

ከዚህ ፈጣን የሁቲዎች ማጥቃት ጀርባስ አንዳች ውስብስብ የመረጃና ድጋፍ ቅንብር ከአይሁዶቹ መንደር አይሸትም ትላላችሁ… ? 

የሁቲ ታጣቂ ቡድን ለባሌስቲክ ሚሳይሎች የሚመሩ፣ መቆጣጠሪያ እና የናቪጌሽን ሲስተሞችን ለመገንባት የአሜሪካው ኩባንያ ክሎድ የተሰኘውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለመጠቀም የበቃው በምን መንገድ ይሆን ? የሚለው ጥያቄ በእኛ አቅም የሚመለስ አይደለም፡፡  

 (በቅንፍ አንድ ጥያቄ፡- አሁን በርግጥም የሁቲዎቹ “ቀዩ ሞት” በቀይ ባሕር አድማስ ላይ ጥላውን አጥልቷል። ሆኖም ይህ ስጋት የሚመነጨው ከዘመናዊ ሚሳኤሎች ወይም ከከበዱ የጦር መሣሪያዎች አይደለም፤ ይልቅስ ቡድኑ ላለፉት ወራት በማይታክት ጥረት ሲያዘጋጃቸው ከቆዩት የየመን ወጣቶች የደም መስዋዕትነት እንጂ። ከጀርባ አንዳች የመረጃ ቅንብር እንዳለ የሴራ ትንተናውን አንጣጥለውም፤ በሌላ በኩል ግን እነዚህ በሸዓ ርዕዮተ ዓለማዊ ተምኔት ተሞልተው ወደ ቀጠናው እሳት የሚገቡት ወጣቶች፣ ለሁቲዎች ዓላማ እስከመጨረሻው ይዋጋሉ ወይስ…  ሳዑዲ ለእስራኤል ገብራ በልዩ ሁኔታ ተመተው ያፈገፍጋሉ?  መቼም እንዲህ በአጭር ጊዜ ሳዑዲ የአብርሃን ስምምነትን ባትፈረምም፤ ሪያድ ቴል አቪቭን ደጅ እንድትጠና የሚያስገድድ የጓዳ ስምምነት አይኖርም ማለት፣ የሚቻል አይመስልም- አንድም ከአሜሪካ ማድፈጥ፤ አንድም ከአይሁዶቹ ውስብስብ የሴራ ቅንብር አኳያ! የቀጥታ ድጋፍ ባያገኙ እንኳ ሁኔታዎችን የሚቀይር ክስተት ሊፈጠር ይችላል) 

በቀጣዮቹ ውጥረት በተሞሉ ቀናት ውስጥ በሚገለጡ እውነታዎች እና የቀጠናው የኃይል አሰላለፎች የምናያቸው ለውጦች ይኖራሉ፡፡ 

የማይቀየረው ነገር የእስራኤል የባህር ዳርቻው አገራትን የመቆጣጠር ፍላጎት ኃይልን፣ ዲፕሎማሲን፣ ደህንነት እያፈራረቀ የመቀጠሉ እውነታ  ነው፡፡  

ይህ የማስገበሪያ መንገድ ሺዓውንም ሱኒውንም እንደየሜዳው በረቀቀ ሁኔታ ማጫወትን ይጨምራል፡፡ የዓለም ግማሽ ችግር፤ አይሆዶቹ መሆናቸውን እነሱ ቢያስተባብሉ የሚያውቅ ያውቃቸዋል፡፡ ግማሽ መፍትሔ አይሆኑም አላልኩም! ቅንነቱ ያላቸው ግን አይመስለኝም!!

__

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News