Homeአበይት ዜናበኢትዮጵያ አካታች የሽግግር መንግስት ለመመስረት ያለመ ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ

በኢትዮጵያ አካታች የሽግግር መንግስት ለመመስረት ያለመ ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ

Advertisement
World Wide Travel Group

ቦርከና ዜና

በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የሚል ጥምረት መመስረታቸውን አስታውቀዋል።

ትብብሩን የመሰረቱት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ የኦጋዴን ህዝብ ነጻነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ እና የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንደሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።

የትብብሩን መመስረት በተመለከተ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሊቀመንበር አቶ ዘመነ ካሴ በዛሬው እለት እሁድ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውን ገልፀዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ትብብሩ ከብዙ ጥረት እና ውጣ ውረድ በኋላ መመስረቱን የጠቆሙት ዘመነ፣ የትብብሩ የመጀመሪያው ግብ በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል።

አቶ ዘመነ አዲስ የሽግግር ምዕራፍ ሲሉ የጠሩት ይህ ሂደት፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲረጋግጡ የሚያስችል እንደሆነ አብራርተዋል።

ይህ አዲስ ምዕራፍ የሚከፈተው፤ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን እና በገዢው ብልጽግና ፓርቲ የሚመራውን ስርአት በማስወገድ መሆኑን አብራርተዋል።

አማጽያን ኃይሎቹ እና የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያዋልዱት የሽግግር ምዕራፍ፤ ዋነኛ ዓላማዎቹ የህዝቦችን ህልውና እና የሀገርን ደህንነት መታደግ ነው ብለዋል።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ያሉ ሁሉንም ጦርነቶችን በማስቆም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማረጋገጥ እና ሰላምና ጸጥታን ማስጠበቅ እንደሚገባ በአፅንኦት ገልፀዋል።

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ማረጋጋት፣ ከጎረቤት ሃገር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል እና የሃገሪቱን ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ቁመና ማስተካከል ዋነኛ ዓላማ ስር ተካተዋል ነው የተባለው።

የትብብሩ ሰብሳቢ የሆኑት ዘመነ ሌላኛው ዋና ዓላማ ህዝባዊ እና ህገ መንግስታዊ ውይይት” (constitutional dialogue) ማድረግን መሆኑን አብራርተዋል።

ለኢትዮጵያ ሰላም እና ለህዝቦች ቀጣይ ህልውና ሲባል እንደሚደረግ የተገለጸው ይህ ውይይት፤ ሃቀኛ፣ ታማኝ፣ ሁሉንም ያካተተ እና ያሳተፈ እንደሚሆን አብራርተዋል።

- Advertisement -

የውይይቱ ዓላማም ወሳኝ ህዝባዊ እና ሀገራዊ ጥያቄዎችን በህዝቦች ቀጥተኛ ተሳትፎ መመለስ እንደሆነም ገልፀዋል።

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News