Homeአበይት ዜናጋዜጣዊ መግለጫየኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) መመስረቱን አስመልክቶ  ከአማራ ማኅበራት ትብብር...

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) መመስረቱን አስመልክቶ  ከአማራ ማኅበራት ትብብር በአሜሪካ የተሰጠ መግለጫ  

Advertisement
World Wide Travel Group
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር

መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም. 

አፋብንን ጨምሮ ሰባት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ማለትም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፣ የኦጋዴን ሕዝብ ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤኔሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጉምዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ንቅናቄ ጊዜ ወስደው በመምከር በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረ-ፈጅ ጦረኛ አገዝዝ ከስር ፈንቅሎ በመገርሰስ ሁሉንም የሚያሳትፍ የሽግግር ስርዓት ለማምጣት የሚያስችላቸውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና)  በመመስርተቻው የተሰማንን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ ይህንን መግለጫ አውጥተናል። 

ይህ የኢትዮጵያ ትንሣዔ ተብሎ ሊገለፅ የሚችል ትብብር እንዲመጣ የአብዛኛው ህዝብ ምኞት እና ጥያቄ ከመሆኑ አልፎ የትብብር ንግግሩ ጭምጭምታ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮኖች በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ በዕብሪት ለማጥፋት የከፈተው ወረራ ሦስት አመታት ያስቆጠረ ሲሆን የሕልውና አደጋ ያላደረሰበት ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ለማለት አይቻልም። በዚህም ረገድ እነዚህ የሕልውና አደጋ የተደቀነባቸው ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች ትብብር ፈጥረው የጋራ ጠላታቸውን ተቀናጅተው በአስቸኳይ እና በአነስተኛ መስዋዕትነት ለማስወገድ መተባበራቸው ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው። 

ይህን ትብብር ተስፋ ሰጭ የሚያደርገው ዋነኛ አላማው በኢትዮጵያ ያለውን አስከፊ ስርዓት በጋራ ታግሎ መጣል ብቻ ሳይሆን ከስርዓቱ መወገድ በኋላ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት በመመስረት በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን፣ የህዝብ ደህንነትን እና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማክበር ብሎም በዘላቂነት ሀገረ መንግሥትን ለማፅናት የሚያስችል ህገ መንግሥት በህዝቦች ፍላጎት አማክኝነት ለመቅረጽ የሕገ መንግሥት ውይይት እንደሚደረግ ማብሰሩ ነው። በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚታዩትን ችግሮች እንዲሁምሊከሰቱ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በሰላም በውይይት እና በድርድር ለመፍታት በሚል ያስቀመጠው መርህ ወይም ዓላማ የሚደነቅ ነው። 

ትብብር ለሕልውና ለማከናወን ያቀዳቸው ጉዳዮች በታቀደላቸው መሰረት ግባቸውን ይመቱ ዘንድ በትብብሩ ውስጥ ያሉ ኃይሎች የሚወክሏቸው ማህበረሰቦች ብሎም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጵያ ከገባችበት አዘቅት ልትወጣ የምትችለው በሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ መሆኑን መገንዘብ ያሻል። በዚህም ረገድ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከፓለቲካ ፓርቲዎች በተለይም ከገዥው ስርዓት የአፈና መዋቅር የራቁ በውጭ ከሚገኙ ማኅበራት፣ ምሁራን፣ ሚዲያወች እና ባለሃብቶች ታላቅ አስተዋጽዖ ይጠበቃል። በተለይም ትብብር ለሕልውናን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ፣ አላማወቹን የማስረዳት ስፊ ስራ ውጭ ካለው የኢትዮጵያ ዲያስፓራ ይጠበቃል። ይህ ለኢትዮጵያ የመጣላት ታሪካዊ እድል በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ በውጭ ያለው ማኅበረሰብ የእርስ በርስ ግንኙነት በማድረግ እና አንድነት በመፍጠር የሚጠበቅበትን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ትብብር ለሕልውናን የመሰረቱ ስባቱ ኃይሎች መቀላቀል የሚሹ ተጨማሪ ኃይላትን በመያዝ ይህንን ኢትዮጵያን ከቅጥረኛ አገዛዝ የማዳን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ እና በዘላቂነት መወጣት እንዲችሉ በከፍተኛ ትዕግስት እና የመግባባት መንፈስ ውይይቶቻቸውን እና ንግግሮቻቸውን እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን። ኢትዮጵያ ከዚህ አስከፊ ስርዓት መገርሰስ በኋላ በጦርነት እና በግጭት አዙሪት ውስጥ ለማለፍ የሚያስችል አቅም ወይም ጦርነትን የሚሸከም ትክሻ የላትም። ኢትዮጵያውያን እንደ ማንኛውም ሌሎች ሀገሮች በሀገራቸው በሰላም መኖርን ፣ ተዘዋዉሮ መስራትን፣ በህግ ብቻ መዳኘትን፣ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መሪዎቻቸውን እና ተወካዮቻቸውን መምረጥን፣ በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ እንዲሁም የሰብዓዊመብቶች ሙሉ በሙሉ መከበርን ይሻሉ። ይህን እውን የሚያደርግ ስራ እንዲሰራ ከትብብር ለሕልውና እና ከሁሉም የባለድርሻ አካላት ብዙ ይጠበቃል። 

የአማራ ማኅበራት ትብብር በአሜሪካ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ይህንን ትብብር ለሕልውና በመመስረታቸው በድጋሜ የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን። 

በዘረ-ፈጅ አገዛዙ መቃብር ላይ የኢትዮጵያ ትንሣዔ ይረጋገጣል! 
ድል፣ ሰላም፣ ፍትህ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ኤዲተሩ ማስታወሻ : በዚህ አምድ ላይ የሚወጡ መግለጫዎች የቦርከናን አቋም ያንጸባርቋሉ ማለት አይደለም፡፡

_

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English

- Advertisement -

ኤክስ ፡ @zborkena 

1 COMMENT

  1. ሲጀመር በሰው መቃብር ላይ የሚለመልም ምንም ሃገር የለም። በመቀጠል በስም ተጠቅሰው የትብብሩ አካል ናቸው የተባሉት ሁሉ ብሄርተኞችና ለራስ ሲቆርሱ የማያሳንሱ ናቸው። ሃገርና ህዝብ በብሄር በመደራጀት ነጻ ማውጣት አይቻልም። እንግዲህ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ በውስጥና በውጭ ሃይሎች እየተደገፉ 4 ኪሎ እንደርሳለን የሚሉን ታጣቂ ቡድኖች ሁሉ በብሄርና በክልል ፓለቲካ ጢንቢራቸው የዞረ ነው። ከተሰላፊዎቹ ሁሉ በጣም የሚገርመው ደግሞ የፋኖ ከወያኔና ከሻቢያ ጋር አብሬ እታገላለሁ ማለቱ ነው። ማን ሆነና ለአማራ ህዝብ የዘመናት ሰቆቃ ምክንያቱ? ወያኔ በተደጋጋሚ በከፈተው ጦርነት ሽዋ ድረስ ገብቶ እየፈለገ ያጠፋቸው እነማን ነበሩ? እንዴት ያ ይረሳል? የማን ንብረት ነው ተጭኖ ወደ መቀሌ የተጓዘው? በቅርቡ አንድ የወያኔ ወታደራዊ ባለስልጣን ሲናገር ከወሎና ከወልዲያ ብቻ የተዘረፉ 60 ተሽከርካሪዎችን ለጄ/ታደሰ እኔ መቀሌ ላይ ሰብስቤ አስረክቤአለሁ ብሎናል። ያ ከማን የተዘረፈ ንብረት ነበር? በትምህርት ተቋማት፤ በመንግስት መገልገያ ማዕከላት፤ የግል ባለሃብቶች ንብረትን ወዘተ ያወደመው ማን ነበረ? ወያኔ አልነበረም በቀይ ቀለም በየግድግዳው እየጻፈ አማራን ይዘልፍ የነበረው? ከዚህ ድርጅት ጋር ነው ዘመነ አብሬ እሰራለሁ የሚለው። የጅል ቀኑ አይመሽ ይላሉ አበው። ከወያኔ/ከሻቢያ እንዲሁም ከግብጽና ከሱዳን ጋር ተጣምሮ ኢትዮጵያዊነትን ማጉላት ፈጽሞ አይቻልም። ለዚህ ነው እስክንድር ነጋ “ለአፋበን ፓሊት ቢሮ” በማለት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ተቃውሞውን ያሰማን።
    ይህ የ 7ትም ሆነ የእልፍ የታጣቂ ስብስብ በእኔ እይታ ሃገር ለማፍረስ፤ ህዝብ ለማስጨረስ፤ በዚህ የኑሮ ውድነት ህዝባችን ያለውን ቆርጥሞ እንኳን እንዳይሰነበት የመከራ ዶፍ ከማውረድ ውጭ አንድም ፍሬ ነገር አያስገኝም። የሃገራችን ተረት እንደሚለው “99 መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣውም”። ህዝባችን የናፈቀው ሰላም እንጂ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ በህዝባችን ስም የሚነግድ ታጣቂ ሃይል አይደለም። በተደጋጋሚ እንዳልኩት ያልተሄደበት ብቸኛ መንገድ የሰላሙ መንገድ ነውና በውይይት በሰላምና እርቅ ነገሮችን ማስከን አስፈላጊ ነው ባይ ነኝ። አዎን የስማ በለው አዋጊዎችና በብሄርና በቋንቋቸው የሰከሩ ሁሉ ይህ ሃሳብ ሰውን ከትግል ለማዘናጋት ነው ይላሉ። ግን ያለፍንበትን መንገድ የቆየና የአሁኑን በማመላከት ሲሞገቱ ዝም፤ ጭጭ ይላሉ። ይህ የሆያ ሆሄ ፓለቲካ ሃገር እንዳፈረሰና እልፍ የሃገሪቱን ምርጥ ልጆች እንደበላ ታሪክ መዝግቦ ይዞታል። ይህ አካታች ነው የተባለለት ትብብርም ፉርሽ ለመሆኑ ገና ከጅምሩ መረዳት ይቻላል። የሻቢያ ፍላጎት ጦርነቱ ትግራይ ላይ እንዲሆን ነው። የወያኔ ፍላጎት ደግሞ ውጊያው አማራ ላይ እንዲሆን ነው። ይህ የሴራ ፓለቲካ አይኑን አፍጦ የመጣበት ደግሞ የብልጽግናው መንግስት ነው። ብልጽግና እንበለ ፍርድ የታሰሩ፤ የተሰወሩትን ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት አለበት። የፈለገ አካታች ነው ከተባለው ድርጅት ጋር ይሰለፍ። ያልፈለገ በሰላም በፈለገው ስፍራ የመኖር መብቱ መከበር አለበት። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ የክልል ፓለቲካው በዚህ በዚያም እሳት እየጫረ ሰው በሰላም ገብቶ መውጣት የማይችልበት ሃገር ሆናለች። ለዚህ ሁሉ የሴራው ቀማሪዎችና ተግባሪዎች ብሄርተኞች ናቸው። ለዚህ ሁሉ ክፋትና ሽብር በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር እሳት የሚያነደውና የሚቆሰቁሰው ወያኔ ነው። ሌሎቹ ሁሉ ተለጣፊ ድርጅቶች ናቸው። ከወያኔ ጀርባ ሻቢያ/ግብጽ/ሱዳንና ሌሎችም በተዋረድ ተሰልፈዋል። ብልጽግና ለወያኔዎች ያኔም አሁንም ስስ ልብ አለው። ያኔ ፕ/መስፍን ወልደማሪያም በአንድ ወቅት እንዳሉት ወያኔዎችን ለቅሞ ለእስር ዳርጓቸው ቢሆን ኑሮ ዛሬ ላይ ሃገሪቱ ከመላ ጎደል ሰላም በሆነች ነበር። ያ ይቅር ከሁለት ሶስት ጊዜ በላይ ጦርነት ከፍተው ይባስ ተብሎ ከ20 ዓመት በላይ በትግራይ ያገለገለውን የስሜን ጦር በዘርና በጎሳ ለይተው የፈጅትን አረመኔዎች ከእስር ፈቶ ውጭ እንዲሻገሩ፤ ተራፊዎቹ ደግሞ መቀሌ ላይ ከትመው ህዝብን እያሸበሩ አሁን እንሆ በአካታች ሃይል ስም 6 የታጣቂ ሃይሎችን አሰልፈው እየተፋለሙት ይገኛሉ። ጠ/ሚሩና በዙሪያው ያሉት ሁሉ ልበ ቢሶች ናቸው። ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ እንዲሉ ነው የሆነው። ወያኔዎች ዛሬ በአዲስ አበባ በህቡዕና በይፋ ድጋፋቸውን ለወያኔ ይገልጣሉ። ሃብት ንብረታቸው አልተነካም። ብልጽግና ግን የተለከፈው አማራን በማሳደድና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንን በኦሮሞ ካድሬዎች ማሳደድና ማጨናነቅ ነው። አሁን ማን ይሙት መስከረም አበራ መታሰር ነበረባት? ለዚህ ነው የሃበሻ ፓለቲካ ጥንብ ነው የምንለው። በወረፋ መገዳደልና መታሰር። ያኔ ወያኔ ያሰራቸው የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬም በብልጽግና እስር ላይ ናቸው። ያኔ ወያኔ የገረፋቸው የአማራ ተወላጆች ዛሬም በብልጽግና ይዋከባሉ። ይህ ከንቱ ፓለቲካ አይደለም የሚሉን ሁሉ አብሾ የጠጡ ብቻ ናቸው፡፡
    በቅርቡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ብልጽግና አልቆለታል፤ የፈረንጆችን አዲስ አመት አይዘልቅም ገለ መሌ እያለ ሲለፈልፍ ማን ከየመን እንዳፈነው፤ በማን ምህረት እንደተደረገለት ረስቷል። የሽግግር መንግስት ናፋቂው አቶ አንዳርጋቸው እድሜ ልኩን የሃበሻ ፓለቲካ እንዳኘከ እንሆ ወደ መቃብር እየቀረበ ነው። ብልጽግና ይውደቅ አይውደቅ ማንም የሚያውቅ የለም። ጻድቃንስ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ጦርነቱ እኮ አልቋል አላለንም ነበር። እርሱ ዛሬ የት ነው ያለው? ፓለቲከኞች እንደ መንፈቅ ህጻን ናቸው የሚያስለቅሳቸውንም ሆነ የሚያስቃቸውን ለይተው አያውቁም። ሃገር በዘረኞች ስብስብ ህብረብ ሄራዊነትና ሰላም ሊኖራት አይችልም። ያለው የሰላም አማራጭ የጠራ የፓለቲካ ጥያቄ በማቅረብ፤ በሃሳብ ፍትጊያ ሃሳብን ተቀብሎና አካፍሎ ሰላማዊ የሆነው መንገድ ብቻ ነው። አይ በጦርነት እናሳካለን የሚሉን ካሉ እሺ መንገድን ጭርቅ ያድርግላችሁ። እንኳን 7 ድርጅት አንድ ላይ ይቅርና አንድ ድርጅት እንኳን ስንት ጊዜ ሲቀደድ ሲሰፋ አይተናል። የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል እንዲሉ ፍጻሜአችሁን ለማየት እድሜ ይስጠን። የእኔ ምክር ግን ሳይመሽ፤ ብዙ ንብረትና ህይወት ሳታጠፉና ሳታስጠፉ ሰላምን መርጣችሁ ለዳግመኛ ድርድር መንገድ ክፈቱ። ጦርነት ለራሺያና ለዪክሬንም አልበጀ። ለእስክንደር ነጋ ያለኝ መልዕክት የእስር ትዕዛዝ ከወጣብህ በዚህም በዚያም ብለው ያጠፉሃል። በጊዜ ከብልጽግና ጋር ተደራድረህ ወደ ሰላም ተመለስ! ሃሳብንና መንገድን መቀየር መሸነፍ አይደለም። ብልህ መሆን እንጂ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News