

“በኤርትራ መንግስት እና አጋሮቹ ላይ በጊዜ እርምጃ አለመውሰድ መዘዝ ያስከትላል” አሉ።
ጌታቸው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ኤርትራ ገብቶ እርምጃ መውሰዱ እንደማይቀር ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም የቀይ ባህር ቀጠና ልዩ መልእክተኛ አኔት ወበር እና በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ጋር በወቅታዊ የቀጣናው ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።
በውይይቱ ወቅት ለቀጠናው ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት እጅግ አስፈላጊ በሆኑ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን እንዲሁም በትግራይ፣ በኤርትራ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግልጽ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
አቶ ጌታቸው በአስመራ ኤርትራ ያለው አገዛዝ እና ስፖንሰሮቹ/ደጋፊዎቹ ቀጠናውን ለማወክ እያከናወኑት ያለውን አደገኛ ሚና አጉልተው ያሳዩ ሲሆን፣ ይህን እንቅስቃሴ በጊዜው ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ አለመውሰድ የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ እንዳስረዱ ገልጸዋል።
ውጥረቱ የበለጠ እንዳይባባስ ለመከላከል፤ የመረጃ ልውውጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲሁም በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English






ጠሚኒስተር ጌታቸው ረዳ ትእዛዝህ ተፈጻሚ ይሆናል አንተ ካልክ እንወራለን ትላንት ብርሃኑ ጁላን፤ባጫ ደበሌን፤አብይ መሃመድን የውሻ ቆዳ ስታለብስ ከርመህ ዛሬ ደግሞ ወታደራዊ ት እዛዝ ሰጭ አንተ ሁነኸል፡፡ ግማሾቻችሁ ቆላ ተምቤን ሄድን ነን አላችሁ፡፡ ግማሾቻችሁ 800 ምርጥ ምርጥ ተሽከርካረዎችና ምርጥ ምርጥ መሳሪያ ለሻቢያ አስረከባችሁ አሁን ደግሞ ሻቢያን እንወጋለን ብላችሁ ማብራሪያ ትሰጣላችሁ፡፡ መቼም እንዲህ እንደተቀለደብን አይኖርም በቃችሁ ሲለን እንደ ቴዎድሮስ አይነት የቆረጠ ሰው ከባዶ ያስነሳልናል፡፡ በየቀኑ የሚነደው የአማራ ገበሬ፤ልጅ፤ከብት ለማንም ቁብ አይሰጠውም፡፡ ደብረ ጽዮን ኢሳይያስን ሊጠይቅ ወደ አስመራ ሄደ ተብሎ ተጋሩ ካሁኑ ዘፈንና መንከባለል ጀምሯል፡፡ እንደው የአማራ ሰቆቃ መች ይሰማ ይሆን አሁን አሁንማ ተለመደ፡፡ የቀን ጅቦች የተነኩ ሲመስላቸው አፈ ጊንጥ ቴዎድሮስ ጸጋይ በሚዲያው እሪታውን ሲያቀልጠው ቴድሮስ አድሃኖም ደግሞ ባካባቢው ያሉትን ቁም ስቅል እያሳየ እሪታው ሲጨምር አብረሃ በላይ፤አረጋዊ በርሄ ደግሞ ውስጥ ውስጡን አካባቢያቸውን ያደነዝዙበታል፡፡ዲያስፖራ ትግሬም ለሙቀት የሚሆን ጃኬት እየገዛ በየመንገዱ ይንከባለላል፡፡
ነብሰ ገዳይ አራጅ የሳምሪ ቡድን ጌታቸው ረዳ ካቋቋመው ፓርቲው ጋር ወልቃይቴዎች ከርስታቸው ተፈናቅለው ወደ ቦታቸው ይመለሱ እያሉ በሞኝ ብልጠት መከላከያውን ያደነዝዙበታል፡፡ ከድፍን ኢትዮጵያ በነ ሽመልስ አብዲሳ ትእዛዝ ስለ ተባረረው፤ ሃብት ንብረቱ ለነደደው አማራ ግን የሚቆምለት አልተገኘም፡፡ አብይ መሃመድም ቢሞቱ ጥላ እንዲያገኙ ዛፍ ተክያለሁ እያለ ሲያላግጥ፤ ኢንጅነር ስመኘውን የመሰለ በረሃ ኑሮ በረሃ ሰርቶ በተቀነባበር ሴራ ለተገደለው ኢትዮጵያዊ አብይ መሃመድ ስመኘው የሚባል ሰው ብሎ አጣጥሎ ገልጾታል ዘይኑ ጀማል በወቅቱ ሲስቅም ታይቷል እንዲህ ነው እንግዲህ የአማራ ደም በኢትዮጵያ፡፡ አማራ አዳኝ ስለሌለህ ቀበቶህን አጥብቅ ዝም ብትልም ትገደላለህ ብትታገልም ትታገላለህ እንግዲህ የክብር ሞት የትኛው እንደሆነ ምርጫውን ላንተ እንተዋለን፡፡