Homeነፃ አስተያየትስለ እናንተ እኛ እናፍራለን! (በሙሉዓለም ገ/መድኀን )

ስለ እናንተ እኛ እናፍራለን! (በሙሉዓለም ገ/መድኀን )

Advertise Here
Advertise here
ሙሉዓለም ገ/መድኀን (ፋይል)

በሙሉዓለም ገ/መድኀን 

የዐቢይ አሕመድ ጥቅመኛ የኦሮሞ ልሂቃን (ጃዋር መሀመድን ጨምሮ) አሁን ላይ አንድና ወጥ የሆነ ስትራቴጂካዊ ግምገማ አላቸው፡፡ 

እሱም “ዘመኑ የእኛ ነው፤ ይህ የበላይነታችን ከኢትዮጵያ ወደአፍሪካ ቀንድ ማደግ አለበት። ማስፈፀሚያውም ጦርነትና ጉልበት ነው” ይላል። 

በስትራቴጂካዊ ግምገማቸው መሠረት፣ በሁለት ትውልዶች ቅብብል ባለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጓዘው ትግላቸው አራት ምዕራፏችን አልፏል፡፡ 

እነዚህም፡-

1) የብሔርተኝነት መነቃቃት ምዕራፍ (Revival)

2) የብሔርተኝነት መልሶ ግንባታ ምዕራፍ 

     (Reconstruction)

3) የብሔር (aka Oromia) ሀገር ምስረታ ምዕራፍ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

     (State Formation) እና

4) የሥልጣን ከፍታ (Ascendancy to Power) 

ደረጃዎችን አልፏል፤ እያለፈ ይገኛል ብለው ያምናሉ፡፡ 

እዚህ ላይ ባህላዊውን የኦሮሞ ብሄርተኝነት ማለታችን ሳይሆን፣ ከሶሪያው ባዕዝ ፓርቲ፣ ከግብፅ ፈርዖኖች፣ ከየመን ጽንፈኞች ከሱዳን አልበሽር እስከ ሐሰን አል ቱራቢ ምክርና ድጋፍ እየተቀበለ የመጣውን ጽንፈኛ አክራሪ ኦነጋዊ  ብሔርተኛ ኃይል እንደሆነ ልብ ይሏል። 

- Advertisement -

ይህ ኃይል በአሁኑ ሰዓት የሀገር ምስረታ State Formation እና  የሥልጣን ከፍታ Ascendancy to Power ለማረጋገጥ ጦርነትን የአገር ውስጥ እና የቀጠናዊ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ፖሊሲ በማድረግ ላይ ነው፡፡ 

“የሀገር ምስረታው” አዲስ አበባን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች ጋር  የገቡበት የግዛት ማስፋፋት፣ መዋጥ፣ መሰልቀጥ ጋር ይገናኛል፡፡ 

ከዚህ ቀደም እንዳልነው፣ የኦሕዴድ ብልጽግና ኢምፓየር ዕቅድ የኢትዮጵያን ‹state formation› እንደገና የመከለስ፣ የመሸንሸን፣ የመፐወዝ ፕሮጀክት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በአፋቸው ‘ኢትዮጵያ’ ቢሉም፣ በኦሮሚያ ‹state formation› ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ እንደሆኑ በተግባር በመታየት ላይ ነው፡፡ 

አጠቃላይ ቡድኑ የሁለት ሀገረ መንግሥት መንታ ልብ ነው ያለው!

ከራሱ ኃይል ውጭ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና የአገር-ግዛቶቻቸውን ከኦሕዴድ ብልጽግና የግዛት ፍላጎት የሚተርፉ ጥቅም አልባ የማድረግ ፖለቲካዊ ፍላጎት አለው፡፡ 

እነ ዐቢይ አህመድ ይዘውት ያለው የፖለቲካ ፕሮጀክት ከሌሎች ክልሎች ተነጥቀው ወደኦሮሞ በሚጠቃለሉ ግዛቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ የፖለቲካ ፍላጎት፦ ከኢትዮጵያ አጎራባች የሆኑ አገራት ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሶማሌላንድ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ እና ሌሎችም ጋር ከኢትዮጵያ አንፃር ሳይሆን ከኦሕዴድ ብልጽግና ኢምፓየር አኳያ በሚኖራቸው ፋይዳና ተጎራባችነት የማመቻቸት ማለትም የመስፋፋት፣ የመጠጋጋት እና የመጠቅለል ፖለቲካ ይዘው እየሰሩ ነው። 

ለዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ 3ኛ ወገን (እንደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያሉ) ኃይሎችን አቅም ይጠቀማሉ፡፡ አቅጣጫው ከዐቢይ አሕመድ ቢሮ ይወጣል፣ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሁሉም በየትርክት ድርሻው  “ሐገረ-መንግሥቱን ለመታደግ” በሚሉ ቃላት ዓላማውን ለማስፈጸም ርብርቡ ቀጥሏል፡፡ 

ትላንት የአፍራን ቀሎ፤ የዚያድ ባሬ ፕሮጀክት የሆነው የባሌ ገበሬዎች አመጽ፤ በምዕራቡ በኩል የታየው ከ “ጋላ ፌዴሬሽን” ምስረታ እስከ “የፕሮቴስታንት ንቅናቄ”፤ እንዲሁም በሞቃዲሾ የሬዲዮ ጣቢያ በመክፈት “ኢምፓየሯ ትፍረስ” ይል የነበረው ንቅናቄ እስከ ጃዋር መሀመድ ትውልድ ደርሶ “Ethiopia out of Oromia” መፈክር ድረስ ተሰምተናል፡፡ 

ዛሬ ሁኔታዎች ተቀይረው፣ የሥልጣን ከፍታን ለማጠናከር የማነቃቃት ምዕራፍ ሥራቸውን በቀላሉና በፍጥነት አጠናቀዋል፡፡ 

ኢትዮጵያዊያንን በምኒልክ ሃውልት ስር የዓድዋ ድል በዓልን ማክበር የከለከለው ይሄው ገዥ ቡድን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማውን በአዲስ አበባ ሰማይ ስር ይዞ መንቀሳቀስን ወንጀል አድርጎ ሲደነግግ፤ በአንጻሩ የራሱን (የብሔር) የጋራ  ምልክቶችን፤ ዓርማዎቹን፣ ባህሉንና ቋንቋውን እንዲሁም ማኅበራዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቹን በአዲስ አበባ ላይ እየጫነ ይገኛል፡፡ 

ይህ በእነ ጃዋር መሀመድ ቋንቋ የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ (Reconstruction) ምዕራፍ ይባላል፡፡ 

የትግላቸውን ዓላማ “making the people and its territory congruent” ሲሉ ይበይኑታል፡፡ “ሕዝቡንና ግዛቱን በመጠበቅ  ከባዕድ ጭቆና ማላቀቅ” የሚለው አካሄዳቸው፣ ” ጨቋኙ” የኢትዮጵያ “ኢምፓየር” መሆኑ ነው- በእነሱ ግምገማ፡፡

የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ፣ ፊደል፣ የግዕዝ ስለጣኔ መሰረቶችን በሙሉ የባዕድ አድርጎ በመቁጠር የኢትዮጵያን ሐገረ መንግሥት መገለጫዎች Deconstruct በማድረግ ላይ ያተኮረውም ለዚህ ዓላማው ነው፡፡

በ1960ዎቹ መጨረሻና በ1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከተሰራው የኦነግ የብሔርተኝነት ትርክት ጀምሮ እስከ ዐቢይ አሕመድ፣ ጃዋር መሀመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ ትውልድ ድረስ የዘለቀ ነው፡፡ 

ኦሮሞ “ኦሮሚያ” የሚባል ሀገር እንደነበረው ያንኑ ሀገር መልሶ በመቆጣጠር፣ በአፍሪካ ቀንድ የበላይነቱን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት በግብ ደረጃ የተቀመጠው በዚህ መንገድ ነው፡፡ የአሁኑ ጦርነትን ያካተተ የትኛውም የጉልበት፣ የፕሮፖጋንዳ፣ የገንዘብ እና በሥልጣን  የመደለል እንቅስቃሴ ይህን ግብ ለማሳካት የሚደረግ ጥረት አካል ነው፡፡ 

በእነሱ ግምገማ፣ “ኦሮሚያ የመገንባት ምዕራፍ” መሳካት ወደአፍሪካ ቀንድ ቁጥጥር እና የበላይነት ለማምራት ለሚደረገው ጥረት በወሳኝነት መንገድ ከፍቷል፡፡ መጀመሪያ አራት ኪሎን መቆጣጠር፣ በኢትዮጵያዊያን ላይ ሥፍን ጽንሰ-ትልም (Hegemonic Project) በመዘርጋት፣ በመቀጠል በኢትዮጵያ አቅም በአፍሪካ ቀንድ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው፡፡

“ኦሮሚያን መገንባት ደረጃ (Making Oromia state formation)” በማለፍ፣ ኢትዮጵያን በመቆጣጠር፣ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የኦሮሚያ ግንባታ አካል እንዲሆኑ ጦርነት ማስፈጸሚያ ፖሊሲ ሆኗል፡፡ ድንበር ተሻግሮ ኤርትራ ድረስ ዘልቆ “ባሬንቱ የኦሮምኛ ቃል ነው” ሲል ምን መልዕክት ማስተላለፍ እንደተፈለገ ግልጽ ነው፡፡

አሁን ዐቢይ አሕመድም ሆነ ግልጽ የዓላማው ተጋሪ ሆኖ የመጣው ጃዋር መሀመድ፣ እንደቡድን ሥልጣንን የመቆናጠጥ ብሎ ከፍታውን የማዝለቅ ምዕራፍ Ascending to Power ላይ ያላቸው ግምገማ እኩል ነው፡፡

የዘመናዊ ፖለቲካ ሳይንስ ግልጽ ትርጉም “ሥልጣን ማለት፤ አንድ አካል የራሱን ፍላጎትና ጥቅም ለማራመድ የሚጠቀምበት መንገድ (means) ነው።” ለዚህም ነው ዛሬ “Ethiopia out of Oromia” ሲል የነበረው ልጅ፣ “የሐገረ መንግሥቱ ዋና ዘብ ሆኛለሁ” ሊለን የደፈረው፡፡

በግልጽ አማርኛ፣ እነ ለዐቢይ አሕመድ አሁን በእጃቸው የገባውን ሥልጣን ማጣት ማለት፤ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ብቻ ሳይሆን “ከብሔራዊ ኬኩ የብቻ በይነት፣ ባይተዋር የሚያደርግ የሕልውና አደጋ ነው” የሚል ፖለቲካዊ ትርጉም አሲዘው፣ ከኬኩ የእጅ አዙር ተካፋዮችን እነ ጃዋር መሀመድን ከጎናቸው አሰልፈዋል፡፡

እናም ዛሬ ለጀዋር መሀመድ “ኦሕዴድ ይውደም” ያሉት ሁሉ “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚለውን እምነት መቃረን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ አልፎም “fake patriotism” ለሚል ፍረጃ ያጋልገጣል፡፡

ዚያድባሬ የጨረቃ ወታደራዊ ማዕረግ የሰጠውን ሰውየ እንደ “ብሔራዊ ጀግና” ቆጥሮ፣ ፋውንዴሽን ከፍቶ ባንዳነትን በሥርዓተ ትምህርት ደረጃ የሚያስተምር የፖለቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሁለተናዊ አገራዊ ሚስጥሮች ለኢምሬቶች አሳልፎ የሰጠ ኃይል፣ የራሱን ስም (ባንዳ) ለሌሎች መጠሪያ ሲያደርግ ማየት የዘመኑ ምጸት ነው፡፡

የነጻነት ትግል ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል የማስተካከያ ምላሽ ይሰጣል። ለጊዜው ግን ማለት የሚቻለው ‘ስለ እናንተ እኛ  እናፍራለን!’

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡ 

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ 

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News