

(በፍቅርተሥላሴ)
ሰው በሀገሩ፣ በቀዬው፣ በሰላም መኖር ቅንጦት ሆኖበት፣ ሲሳደድ፣ እየታደነ በጅምላ ሲገደል እያዩ፣ ማዘንና መቆጣት ሲያንስ ነው። ይህ ዓይነቱ ጥቃትና እልቂት ያዘቦት ክስተት እየሆነ መምጣቱ ደግሞ፣ ከማሳዘንም በላይ ያማል፣ ያስቆጣል። ነገር ግን፣ ሰሞኑን በአርሲ የደረሰውን የንጹሐን እልቂትና መሰል ጥቃቶችን ተከትሎ በሲኖዶሱ ላይ የሚሰነዘረው ዘለፋና ማንጎጠጥ ቅጥ አላጣም ወይ? ኢላማውንስ እየሳተ አይደለም ወይ?
እርግጥ ነው፣ ሲኖዶሱ የምእመናንን ሕይወት ለመታደግና ጥቃቱን ለማስቀረት ማድረግ ሲገባውና ሲችል ያላደረጋቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚመጥን ሥራ ሳይሠራ ቀርቶም ይሆናል። ከዚህ አንጻር፣ ይህና ያ ይደረግ ብሎ ማሳሰብ፣ ፈርጅ ያለው ሐሳብ ማቅረብ፣ አቅጣጫ ማሳየት፣ ሲኖዶሱ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በአግባቡ ግፊት ማድረግ ክፋት የለውም። አስፈላጊም ነው። ችግሩ ይህን አጥር ተሻግሮ የሚደረገው ዘለፋና ውል አልባ ነቀፋ ነው።
ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ በሲኖዶሱ ላይ የሚሰነዘሩት አብዛኞቹ ነቀፋዎች፣ ሲኖዶሱ ማድረግ ሲገባው ባላደረገው፣ ወይም በአግባቡ ባልፈጸመው ተግባር ዙሪያ የሚያጠነጥኑም አይደሉም። ከዚያ ይልቅ፣ ለምን የመንግሥት አዳራሽ ሄዳችሁ፣ ለምን ይህን መረቃችሁ፣ ለምን ያንን ባረካችሁ፣ ለምን ከመንግሥት ጋር ተነካካችሁ የሚል ዘለፋ ነው የሚበዛው። ሲኖዶሱ መንግሥትን በቀጥታ እንዲያወግዝና እንዲጋፈጥ የመፈለግ አዝማሚያም ይስተዋላል።
ምንም ጥያቄ የለውም፣ ሲኖዶሱ ጥቃቱን አጥብቆ ሊያወግዝ፣ ለዜጎች ጥበቃ እንዲደረግና የተገደሉት ፍትሕ እንዲያገኙ ቀጣይነት ባለው መንገድ የሚመለከተውን አካል ሊያሳስብ ይገባል። ነገር ግን፣ ጳጳሳቱ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ሊንቀሳቀሱ አይችሉም። በዚያ ላይ፣ ቤተ ክህነቱን ከመንግሥት ጋር የሚያገናኙት ብዙ የዕለት ተዕለት አስተዳደራዊ ጉዳዮች አሉ። ከዚህ አንጻር፣ ከመንግሥት ጋር በቀጥታ እንዲላተሙ መጠበቅ ትክክል አይመስለኝም።
ይህ ማለት ግን፣ ከመንግሥት ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ለመጠበቅ ሲሉ፣ በምእመናን ላይ በሚፈጸመው ግፍና በደል በዝምታ ይለፉ ማለት አይደለም። ሆኖም፣ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የግድ ከመንግሥት ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ መግባት አይኖርባቸውም። ከመንግሥት ጋር የሚኖራቸው መስተጋብርም፣ ጥቃቱን ችላ እንደማለት፣ እንደ አለመቆርቆር መተርጎም የለበትም። ሁለቱን አመዛዝኖ መሄድ ግድ ይላል።
ከመንግሥት ጋር አምባጓሮ ውስጥ በመግባት ይመጣል ተብሎ የሚታሰበው መፍትሔም ግልጽ አይደለም። የሀገሪቱ ሁኔታ ውስብስብ ነው። ቅርጽ ባልተበጀለትና ባልተሰላ ሁኔታ፣ በስሜት ተገፋፍቶ የከረረ ተቃውሞ ውስጥ ቢገባ፣ በቀውስ ላይ ቀውስ መደረብ ነው ትርፉ። ይህ ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ይኖርበታል።
በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጸመው ጥቃት የሚፈጥረው ሰብአዊ ሐዘን፣ ቁጭትና ቁጣ እንዳለ ሆኖ፣ በሲኖዶሱ ላይ የሚካሄደው ማጥላላት ግን፣ ሌላ አጀንዳ እንዳልተቀላቀለበት እርግጠኛ መሆን የሚቻልም አይመስለኝም። ያም ሆነ ይህ፣ ባሕር ማዶ ሆኖ፣ አገዛዙን ፊት ለፊት ካልተጋፈጣችሁ ብሎ በቤተ ክርስቲያኗ አባቶች ላይ የሚሰነዘረው ለከት ያጣ ማብጠልጠልና ማንጎጠጥ፣ ጠቃሚም ተገቢም አይደለም።
በቀድሞው ኢሕአዴግ አገዛዝ ዘመን፣ በዕውቀቱ ስዩም ለትምህርት ይሁን ለሥራ ወደ አሜሪካ በመጣበት አንድ ወቅት፣ አንዳንድ ቃላቱን ልስት ብችልም፣ በግርድፉ ግን “ሰሞኑን መንግሥትን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጌ ስዘረጥጠው ብታዩኝ እንዳይገርማችሁ፣ መንግሥት የማይደርስበት ቦታ ስለሄድኩ ነው” የምትል፣ ዲያስፖራውን የምትነቁር አጭር መልዕክት በፌስቡክ ገጹ ላይ አጋርቶ ነበር።
ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦ ያለ ከልካይ፣ ያለ ገደብ፣ ባሕር ማዶ ተቀምጦ፣ አገዛዙ ላይ እንዳሻ መናገር ስለተቻለ፣ ሀገር ቤት፣ መሬት ላይ ያለን አካል ምን ዓይነት መሥዋዕትነት መክፈል እንዳለበት መበየን፣ እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ አላደረጉም እያለ ማሸማቀቅና ማንጎጠጥ ያስተዛዝባል። መፍትሔም አይሆንም።
አስቀድሜ እንዳልኩት፣ ሲኖዶሱ ጥቃቱን ለመከላከል የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ማሳሰብ፣ አቅጣጫ ማሳየትና ግፊት ማድረግ ተገቢ ነው። ሆኖም፣ ሁሉም በልኩና በሥርዓት ሊሆን ይገባል። አቅሙ ካለም፣ ከነቀፌታው ይልቅ፣ ማገዝ፣ ሲኖዶሱ ያጎደለውን መሙላት ነው የሚሻለው። በተለይም በዲያስፖራ ያለው ወገን፣ ሲኖዶሱን ከመውቀስ፣ ያለውን ነጻነት ተጠቅሞ እልቂቱ ሰፊና ያልተቋረጠ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝ የራሱን ሥራ ቢሠራ፣ ጥቃቱ እንዲቆምና ገዳዮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግሥት ላይ ጫና ቢፈጥር ነው የተሻለ የሚሆነው።
ጥቃቱን ማንም ያድርሰው ማን፣ ዞሮ ዞሮ ተጠያቂው፣ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት፣ አቅሙም ያለው መንግሥት ነው። ጫና መደረግ ካለበት፣ ጫናው ይህ ሁሉ ሰው ነጋ ጠባ በገፍ እያለቀ፣ ዕቃ የጠፋው እንኳን አልመስልህ ያለው መንግሥት ላይ ነው። ከዚያ አልፎ፣ በሲኖዶሱ ላይ የተቃጣ ዘለፋ ኢላማውን የሳተ ነው። የቤተ ክርስቲያኗን ክብርም የጠበቀ አይደለም።
__
የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረድ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን አቋም አያንጸባርቁም፡፡
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






ፍቅርተ ስላሴ በዘሃበሻ ላይ የጻፍሽውን አንብቤ ሲገርመኝ እዚሁ ደገምሽው ይህንን እንኳን ያነበብኩት እርምት አድርገሽበት ይሆናል በሚል እሳቤ ነበር እንጅ ያንኑ ተደግሚዋለሽ ብዬ አልጠረጠርኩትም ነበር፡፡ ይገርማል ሲኖዶሱ ምን ያድርጋችሁ ነው ያልሽን? የኦርቶዶክስ ምእመን ከሆንሽ የሃይማኖቱ የበላይ ጠባቂ፤ቀኖና አስጠባቂና አቅኝ፤ምእመኑን ከተኩላ ጠባቂ ይኸው ሲኖዶስ መሆን ነበረበት ነገር ግ ን ይህ አትንኩት የምትይው ሲኖዶስ ከተቋቋመ ጀምሮ ከአቡነ ጳውሎስ እስከዛሬ ቀኖና ሲጣስ፤የአንድ የክርስቶስ ቤተሰብ በምድራዊ ጎሳ ሲሸነሸን፤ ሲዳከም፤እመቤታችን ስትወገዝ፤ አንዴ ተሃድሶዎች አንዴ ካቶሊኮች ሲፈለፈሉበት፤ጳጳሳቱ ደግሞ ሳጥን ሰብረው የቤተ ክርስቲያን ወርቅ ሲዘርፉ ፤ንግድ ሲነግዱ፤ በ40 ሚሊዮን ኦቶሞቢል በከተማው ሲንፈላሰሱ፤አቡነ ማትያስን ጨምሮ እጅጋየሁ በየነ የተባለች ክፉ የሃገር ጠላት ቤት በመገኘት ልደቷን ለማክበር ፌሽታ በፌሽታ ሲሆኑ ስናይ በአንጻሩ በወለጋ፤በአሩሲ በሌሎቹም ቦታዎች ክርስቲያኖች እየተገዘገዙ ተቆራርጠው ሲገደሉ አረ አስጡልን ብሎ መጮሁ ክፋቱ ምኑ ላይ ነው? እነሱ ካልጮሁስ ማን ሊጮህ ነው እንኳን ክርስቲያኑ እስላሙም በዚህ ሁኔታ ቢታረድ አረመኔያዊ ስራውን ማውገዝ ሃይማኖታዊ ተልእኳቸው ሊሆን በተገባው ነበር፡፡
አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ የኛ ጳጳሳት የሚራኮቱበትን ምድራዊ ምቾት አሽቀንጥረው ጥለው ለፋሽስት እንዳትገዙ ብለው አውግዘው በፋሽስት ጥልያን ትእዛዝ በትግሬ አልሞ ተኳሾች ቃታ ሲሳብባቸው እያየሁ ነው የምሞት በማለት የተሸፈኑበትን ጥቁር ጨርቅ አሽቀንጥርው ሲጥሉ በቅርቡ አባ መላኩ በደርግ ጊዜ ደሞዜ ለድሃ ይሰጥ አልፈልገውም ብለው ምቾት ጠልተው ፍራሽ ላይ ሲተኙ በባሶ እግራቸው ሲሄዱ አንች የምትከላከያቸው አባቶች በምን ደረጃ እንደሚኖሩ ማስረጃ ማጣቀስ አያስፈልገንም፡፡ ምን ያድርጉ ላልሽው በመጀመሪያ ቦታው የሚጠይቀውን መስፈርት ያሟሉ፤ለስጋዊ ፈቃድ እራሳቸውን አያስገዙ፤ የነሱ ሃይል ልጆቻቸው ስለሆኑ ባለፈው ሰልፍ ሲጠሩ ተለምነው እንደቀረው ሁሉ አሁንም ሰልፍ ይጥሩ፤ በወለጋ፤በአሩሲ በሌሎቹም ቦታዎች በኦሮምያ መንግስት፤በዋሃቢ፤በጽንፈኛ ኦሮሞዎች ለሚገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ባሎበትና በቦታው ተገኝተው የሃዘን መግለጫ ይስጡ፤ ምድር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ይጥሩ፤’ይህ አልሰራ ካለ አትገዙ ብለው ያውግዙ፡፡
ወ/ሮ ፍቅርተ ሲኖዶሱ ከመንቀዙ የተነሳ በትግራይ አንደኛው ደግሞ አዲስ አበባ እነዚህ ከፍተኛ የሃይማኖቱ ምሳሌዎች በኦዲዮና በቪዲዮ ይየነውን ቀሌት ተመልክተሽ አቶ በላይ መኮንን (ሊቀ አእላፋት) የሰራውን ነውር አይተሽ ቤታችሁን አጽዱት ከማለት ፋንታ ምን ያድርጓችሁ ብሎ መጽሃፍ ትክክል አይመስልም ለሃይማኖቱም የተቆረቆርሽ አልመሰለኝም፡፡ እኔ አለማዊ ነኝ ከዚህ የባሰ የረከሰ ስራም ልሰራ እችላለሁ በነሱ ቦታ ያለ ሰው ግን የተሰጣቸው ክህነት ሊሰሩትና ሊያስፈጽሙት የሚገባ ከብዙ በጥቂቱ ከላይ የተገለጸው ስለሆነ በሰሩት ነውር ስራ እንዲጽናኑ አታድርጊያቸው፡፡ በእርግጥ ከሴት ጋር በተያያዘ ሰው ይደክማል በኦፊሴሊያዊ አግብተው ከደረጃቸው ወርደው አገልግሎት ይስጡ፡፡ እንዲህ ያለ ቅሌት ግ ን ከእለት ወደ እለት መፈጸሙ ለምእመኑ መጥፎ ምሳሌ በመሆኑ እርምት ያስፈልገዋል፡፡ ሲጀመር መነኩሴ ከተማ ምን ይሰራል ከአለም ይርቃል እንጅ? ካጠፋን ይቅርታ
ችግሩ የሲኖዶሱ አይደለም። እርግጥ ነው ሲኖዶሱ የበለጠ ሊያደርግ የሚችልባቸው ጉዳዪች ይኖራሉ። ይሁን እንጂ በየሚዲያው ሲኖዶሱን የሚተቹ ሁሉ የመፍትሄ ሃሳብ ሳይሆን የሚያጋሩን ያንኑ ያዘው ጥለፈው የፓለቲካ ስልታቸውን ነው። በመሰረቱ ጸሃፊው ከላይ እንደጠቀሰው ሲኖዶሱ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው አያሌ ጉዳዪች ስላሉ በዘፈቀደ ያን ድልድይ አፍርሶ ማዶ ለማዶ መቆም ለሃገርም ለህዝብም አይጠቅምም። ሲጀመር ሞቱ እንጂ በእነማን ሃይል እንደተገደሉ መረጃን ተመርኩዞ የቀረበ አጥጋቢ ጉዳይ አላየንም። ልክ እንደ እሳት አደጋ ሰራተኛ ለአንድ አፍታ ነገሩ ይናፈስና ውሃ ተደፍቶበት ነገሩ ይረሳል። ዞሮ ተመልሶ ደግሞ ሌላ ግድያ ሲፈጸም እንደገና የወሬ ማሟያ ይሆናል። መንግስት ጥምር የሚባለው ሃይል ነው ምዕመናኑን የገደላቸው ሲለን ቆየት ያለው ተጨባጭ ታሪክ ደግሞ የሚያሳየን የኦሮሞ ታጣቂ ሃይሎች እንደሆኑ ነው። የኦሮሞ የቁም አልቃሽ የውጭና የውስጥ የፓለቲካ ሙታኖች በየሶሻል ሚዲያው የሚያናፍሱትን ልብ ብሎ ለፈተሸ ደግሞ በሆነው ነገር ጮቤ የሚረግጡ ይመስላሉ። እዚህ ላይ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ (99.99%) የማንንም ሞት አይሻም። የኖርንበት ያየነው ስለሆነ የኦሮሞ ህዝብን ስብዕና እናውቀዋለን። እርግጥ ነው ጊዜ ብዙዎቻችን ለውጧል። ግን የሰውን ሞት የደስታ ምንጭ የሚያደርግ ህብረተሰብ ራሱ የሞተ በመሆኑ ለማንም ለምንም አይጠቅምም። በእኔ እምነት የምዕመናን ግድያ በሻቢያ/በወያኔ/በግብጽና ሱዳን የሚመራ ነው ባይ ነኝ። በተለይ ወያኔ የብልጽግናውን መንግስት ለመናድ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። እንደዚህ አይነቱን የሃይማኖት ግጭት በ 27 ዓመቱ የመከራ አገዛዝ ዘመን ተጠቅሞበታል። ሲጀመር አሁን ላለው የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ማን ሆነና ነው መሰረቱ? ወያኔዎች አይደሉም እንዴ?
ከስልጣን ከተባረረ ወዲህ በመቀሌ መሽጎ አራት ጊዜ ጦርነት ከፍቶ አሁን በኤርትራ በረሃና ከተሞች የሚርመሰመሰው ወያኔ በሃገራችን የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚው ሸረኛና አረመኔ ነው። ስለዚህ በዚህም በዚያም የሚቀጣጠሉ እሳቶች ሁሉ የወያኔ እጅ እንዳለበት በጭራሽ መካድ አይቻልም። በዚህ ላይ ፋኖ/ኦላና ሌሎችም ዘርፎ ኗሪዎች የህዝቡን መከራ ማራባታቸው በእየለቱ የምናየው ስለሆነ ከወያኔና ከሻቢያ ጋር ቂጥ ገጥመው ሃገር እያተራመሱ እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። በተደጋጋሚ እንዳልነው ብሄርተኞች ድውያኖች ናቸው። ከራሳቸው ውጭ ለሌላው አያስቡም። ስለዚህ ልብ ያለው ሁሉ ሊረዳ የሚገባው ነገር ብልጽግናን ለማሳጣትና ብሎም አዳክሞ ለመጣል ወያኔዎች እንቅልፍ አይተኙም። በአንድ በኩል እሰየው ብልጽግና ሊጎነተል ይገባዋል እላለሁ። ያሰራቸውን የ 60 ዓመታት የደም ሰዎች ፈትቶ ጽፈሃል፤ አንበሃል፤ ተናግረሃል እያለ በብሄር እየለዬ እስር ቤት የከተታቸውን ወገኖች ሳስብ እብደታችን ዘመን የማይሽረው መሆኑን መረዳት አይከብድም። ስብሃት ነጋን፤ በሰሜን እዝ ላይ ሲኖ ትራክ የነድትን ከእስር ለቆ ዛሬ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች በእነማን እንደተሞሉ ማየቱ በቂ መረጃ ነው። አሁንም የትግራይ ሰላም ገለ መሌ የሚባለውም አይሰራም። 60 ዓመታት ሙሉ ባሩድ ሲያሸትና ወንድምና እህቱን ሲገድልና ሲያስገድል የኖረ ትውልድ ለህግ ተገዥ ሆኖ ይኖራል ማለት በፍጽም ሞኝነት ነው። የትግራይ ትግልና ፍልሚያ ያኔም አሁንም ጸብ የለሽ በዳቦ እንደሆነ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል። ይህ ከራስ ጋር ግብግብም ይቀጥላል። አሁን በበራሪ ወረቀቶችና በሌላም አሻጥሩን በከተማ የጀመረው ወያኔ ፈንጅ በመቅበር፤ በሽምቅ ወታደራዊና የሲቪል ተሽከርካሪዎችን በማውደም ዞሮ ተመልሶ ወደ ሽፍትነቱ እንደሚገባ ግልጽ ነው። የዚህ ሁሉ መከራ ምንጭ ደግሞ የዶ/ር አብይ ያዝ ለቀቅ አመራር ነው። ወያኔዎች ላይ መጨከን አቅቶት ስንት ጉድ ተሰርቷል። የወያኔውን ብር ብልጽግና ሲተካ ወደ መቀሌ የተላከው 2 ቢሊዪን ብር የት ገባ? ከወሎ ከጎንደር ከሽዋ በወረራው ጊዜ የዘረፉት ሃብትና ንብረት የት ደረሰ? መልሱ በተሳከረ ፓለቲካ ሁሉም በሽፍንፍን ታልፏል? አሁን ዲ ዲ አር የሚባለውም ሁሉ ልክ እንዳለፈው የተጣለ መሳሪያ እያስረከቡ ጥቅማ ጥቅም ለመሰብሰብ እንጂ ዋናው ትጥቃቸው ተቀብሮ ነው ያለው። የሚገርመው ያኔ በዲ ዲ አር ገንዘብ እየተሰጣቸው ወደ ሰላም ተመልሰናል ያሉት ሁሉ ለሁለተኛ ጊዜ ተሰላፊ መሆናቸው አስገራሚ ነው።
እንግዲህ ከሲኖዶሱ ይልቅ እኔ የብልጽግናን መንግስት ነው በምዕመናኑ ሞት በሃላፊነት የምጠይቀው። እንዴት አንድ መንግስት ነኝ የሚል በአንድ ሥፍራ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስ ካለፈው ስህተት ተምሮ ህዝብን ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በማጣመር ጥቃቱን መግታት ያቅተዋል? ግን ያው አለማችን ሁሉ በራፋችን ደጃፍ ነው ብለው ለሚያምኑ ጠባብ ብሄርተኞች ዛሬ እንበለ ፍርድ ያረደውና የገደለው ሬሳ ነገር የራሱ እንደሚሆን አይገምትም። ሁሌም በቀቢጸ ተስፋ እኖራለሁ ባይ ነውና! ሲኖዶሱ በደሉን መርምሮ መረጃን ተመርኩዞ ለዓለም ህዝብ የሆነውን ሁሉ የማስታወቅ ሃላፊነት አለበት። በየመድረኩ ማልቀሱ ቀጣይ ለቅሶን አያቆምም። ሲኖዶሱም በአማኞች ህብረትና ትብብር ሊደገፍ ይገባል። መንግስት፤ ሲኖዶስ ወዘተ ይህን ያን ሳያረጉ ከማለት ይልቅ እኛ ከእነዚህና ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር ምን ማድረግ እንችላለን በማለት የሚሆነውን መፍትሄ መፈተሽ አስፈላጊ ነው። መንግስት ህዝብ ነው። ሲኖዶስ አማኙ ነው። ከእነዚህ ስብስቦች ድጋፍ ውጭ መንግስትም ሲኖዶስም አይጸኑም። ስለዚህ ነው መንግስትንም ሆነ ሲኖዶሱን በተናጠል መኮነን የክሱን ሃሳብ ሙሉ አያደርገውም የምንለው። ስለሆነም ዳግም ምዕመናን እንዳይጨፈጨፉ ካለፈው መከራ ትምህርት በመውሰድ ምን የመከላከያ ሃሳብና ምሽግ እየተደረገ ነው? ነው ወይስ ዝንተ ዓለም እያለቀሱ በጅምላ ቀበራ ነው? እናስብ። የሰው መኖር የሚለካው ለሌላው ሲኖሩ ነው። በዘር፤ በቋንቋ፤ ሃይማኖትን የታከከ ልዪነትን እንተው። ለሰው ሰው መሆን ብቻው በቂ ነው። በቃኝ!
አቦይ ተስፋ እዚህም መጡ? በሚችሉት ሁሉ ያሳክሩት ህዝበ አዳሙ ወደ አንድ ግብ እንዳይደርስ።ይህን መማሪያ መድረክ መደበሪያ አድርጉት።
Ignorant!
Your question form topic by itself sounds very clumsy and confusing! It tells the readers that “this synod has been doing and is doing what it can do , what else we expect to do more than this ?”
Not only the follower of the Orthodox Christianity but also any person of reasonable and rational mind knows very well the very horrible failure of the synod for many years as far as what has been going and what is going on the ground in our country is concerned!!!
Those leaders of the top body of religious belief preach us about paying any sacrifice like Jesus Christ has done if we are serious and determined enough to help millions of innocent people get out of the untold sufferings they have gone through and are going through for so many years. Sadly enough, they keep being the very opportunistic by being a typical playing cards of the very garbage and deadly palace politics!!!! I understand that religion has never been free of being part doomed political system through out history . But what we rare witnessing nowadays is extremely frustrating and dangerous! That is why we must be reasonably and rationally and constructively critical towards the synod leadership !!! Other wise our religious beliefs will be in a very serious danger!!
Sony sister, do not be unnecessarily afraid and try to wrongly defend those who are making our religious beliefs extremely under dog !!!
correction /last sentence ; It is to mean So, my sister,