የፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት

የፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት

ሜይ 31 2015 ሶከር ኢትዮጵያ ላይ የወጣ የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫውን ሲቀበል ሙገር ሲሚንቶ ደግሞ ወልድያን ተከትሎ ወደ ብሄራዊ ሊግ ወርዷል፡፡ ወደ ቦዲቲ ያቀናው ኤሌክትሪክ ወላይታ ድቻን 1-0 በማሸነፍ ለከርሞ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል፡፡ የኤሌክትሪክን የድል ግብ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች የኤሌክትሪክ ወሳኝ ተጨዋች መሆን የቻለው ሄይቲያዊው አማካይ ሳውረን ኦልሪስ ከመረብ አሳርፏል፡፡ […]

ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ (አዲስ አድማስ)

ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ (አዲስ አድማስ)

ቅዳሜ ሜይ 30 2015 የወጣ ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ጠቅሰው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ442 የምርጫ ክልሎች ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ መግለጹን ተክትሎ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና መኢአድ የምርጫውን ውጤት […]

ተፈጥሮ :”ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች” [ ተነከሰች]

እናት ጎሽ ልጇን ከአናብስት ለማዳን ብቻዋን አንበሶችን እየተዋጋች እያለች ፤ ጥጃዋ በአንደኛዋ አንበሳ ተነጥቃ ተወሰደች። እራሷንም ጭምር እየተከላከለች ተስፋ ሳትቆርጥ ጥጃዋን ለማዳን አናብስቱን ማሳደድ ጀመረች። ሸሽተው የነበሩ ጎሾች የእናትየውን ቁርጠኝነት ሲያዮ ተመልሰው ውጊያውን ተቀላቀሉ። እናት በስኬት ልጇን አዳነች። ትይንቱ የመሪነት ሚና እና ተስፋ ያለመቁረጥን ፋይዳም ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ከአይሲስ አዲስ ምልምሎች ውስጥ ደቡብ አፍሪካዊ ቤተሰቦችም ይገኙበታል

ከአይሲስ አዲስ ምልምሎች ውስጥ ደቡብ አፍሪካዊ ቤተሰቦችም ይገኙበታል

ከአይሲስ አዲስ ምልምሎች ውስጥ ደቡብ አፍሪካዊ ቤተሰቦችም እንደሚገኙበት አልጃዚራ ዘገበ። ቢያንስ ሃያ ሶስት የሚሆኑ ደቡብ አፍሪካዊያን አይሲስን ለመቀላቀል ወደ ኢራቅ እና ሶሪያ ተንቀሳቅሰዋል ሲል (ህጻናት ሳይቀሩ) የዘገበው አልጀዚራ ዜናው ከተለያዮ ምንጮች እንደተረጋገጠ ይናገራል።

በሃመር ወረዳ ከፍተኛ እልቂት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

በሃመር ወረዳ ከፍተኛ እልቂት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

ኢሳት ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ካለፈውሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ሲታኮሱ መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሻለቃ ጦር እና የፌደራል አባላት ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት […]

የአፍሪቃ የልማት ባንክ አዲስ ፕሬዚደንት መምረጡ

የአፍሪቃ የልማት ባንክ አዲስ ፕሬዚደንት መምረጡ

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ የአፍሪቃ የልማት ባንክ ባለፈው ሀሙስ ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሚገኝባት በኮት ዲቫር የአቢዦ ከተማ ባካሄደው ስብሰባ ላይ አዲስ ፕሬዚደንት መረጠ። ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን የያዘው ይኸው ባንክ በአህጉሩ ድህነትን ለመታገል እና የአህጉሩን ሕዝቦች ኑሮ ለማሻሻሉ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ ተንቀሳቅሶዋል። የአፍሪቃ የልማት ባንክ ባለፈው ሀሙስ ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሚገኝባት በኮት ዲቫር የአቢዦ ከተማ ባካሄደው ስብሰባ […]

የዮጋንዳው መከላከያ ሚኒስተር ከተባበሩት መንግስታት የማዕቀብ ኮሚቴ ጋር ተወያዮ

የዮጋንዳው መከላከያ ሚኒስተር ከተባበሩት መንግስታት የማዕቀብ ኮሚቴ ጋር ተወያዮ

ሺኑዋ የዮጋንዳው መከላከያ ሚኒስተር ከተባበሩት መንግስታት የማዕቀብ ኮሚቴ ጋር እንደተወያዮ የቻይናው ሜዲያ ሺኑዋ ዘግቧል። የመከላከያ ሚኒስተሩ ክሪስፕስ ኪዮንጋ ፤ እና የዮኤን 1553 ማዕቀብ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና በዮርዳኖስ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ ተወካይ ዲና ካዋር ውይይት ያተኮረው በጎረቤት ጎንኮ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ወርቅ ንግድ ዙሪያ ነው። ችግሩን ለመቅረፍ ዮጋንዳ የምትጫወተውን ሚና ካስታወሱ በኋላ ፤ ኪዮንጋ የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ […]

በናይጀሪያ አጥፍቶ ጠፊ በመስጊድ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 18 ያህል ሰዎች ሞተዋል

በናይጀሪያ  አጥፍቶ ጠፊ በመስጊድ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 18  ያህል ሰዎች ሞተዋል

በናይጀሪያ  አጥፍቶ ጠፊ በመስጊድ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 18  ያህል ሰዎች እንደሞቱ አልጃዚራ ዘግቧል።  ጥቃቱ የደረሰው ማይዱጉሪ በሚባለው የናይጀሪያ  ከተማ ሲሆን  ይሄኛው የአጥፍቶ ጠፊ አደጋ ከመድረሱ ከአስራ ስምንት ሰዓት ቀደሞ ብሎ  በከተማዋ ዙሪያ ቦኮ  ሃራም ባደረሰው  ጥቃት አስር  ያህል ሰዎች ተገድለዋል። አጥፍቶ ጠፊው ባደረሰው ጥቃት ሌሎች ሰላሳ ያህል ሰዎች ህይወታቸው  አልፏል።      

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ

‹‹በኃይል የተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተቀባይነት የለውም››

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ

• ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል • ‹‹የአፍሪካ ህብረት ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል የእንጨት ድስት ነው›› አቶ ስለሽ ሰማያዊ ፓርቲ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን እንደማይቀበለው አሳወቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ግንቦት 21/2007 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ምርጫው ‹‹ከዚህ […]

1 60 61 62 63 64 66