“ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! (ክፍል ሁለት)

ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅሚያዚያ 20 ቀን 2013 ዓ. ም. “ሽብርተኝነት የሕሊና ጦርነት ነው። አሸባሪዎች፤ ፍርሃት፣ አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በማህበረሰባችን ክፍፍል በመፍጠር ሊቆጣጠሩን እና ባሕሪያችንን እንድንቀይር ለማድረግ ይሞክራሉ።” ፓትሪክ ኬነዲ መጪውን ምርጫ ሆን ብለው የሚያጣጥሉ ሃይሎች፤ ሃገራችንን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ ተግተው በሚሰሩ ብርቅዬ ዜጎቻችን ላይ እንቅፋት በመፍጠር፤ አንድም በማወቅ፤ ሌላም ደግሞ ባለማወቅ፤ የአጥፊዎች ተባባሪ እየሆኑ ነው። አውቀው… Continue reading “ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! (ክፍል ሁለት)

የአገር አድን ጥሪ!

በአሁኑ ጊዜ ያለው ተቀዳሚ ቅራኔ ኢትዮጵያ ትፍረስ! በሚሉ እና አትፈርስም!በሚሉ መካከል ያለ ፍልሚያ ነው:: ሙሉውን በፒ ዲ ኤ ፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! ክፍል አንድ

ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ ሚያዚያ 16 ቀን 2013 ከሁሉ አስቀድሜ፤ በተለያዩ አካባቢዎች፤ በወኖቻችን ላይ የተፈፀመው እና እየተፈፀመ ባለው ጭፍጨፋ የተሰማኝን ልብ የሚሰብር ጥልቅ ሃዘን እገልፃለሁ። ቸሩ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር። ቤተሰብን ወዳጅ ዘመድን፤ እንዲሁም መላው ሕዝባችንን፤ እግዚአብሄር ያጽናና። “ሽብርተኝነት የሕሊና ጦርነት ነው። አሸባሪዎች፤ ፍርሃት፣ አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በማህበረሰባችን ክፍፍል በመፍጠር ሊቆጣጠሩን እና ባሕሪያችንን እንድንቀይር ለማድረግ ይሞክራሉ።” ፓትሪክ… Continue reading “ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! ክፍል አንድ

ኢትዮጵያ – የአባይ ወንዝ ባለቤትነት ጉዳይ (በኪዳኔ ዓለማየሁ)

ኪዳኔ ዓለማየሁሚያዚያ 18 , 2021 ዓ. ም. መግቢያ፤ በጥንቱ ዘመን የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል።  እንደሚታወቀው በየድረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፣ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ… Continue reading ኢትዮጵያ – የአባይ ወንዝ ባለቤትነት ጉዳይ (በኪዳኔ ዓለማየሁ)

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች የቁርጥ ቀን ልጆቿን ትሻለች!! (በስለአባት ማናዬ )

(በስለአባት ማናዬ) የግብፅ እና የሱዳን ቤንዚንነት ! የዝሆኖቹ ርግጫ በአፍሪካ የእጅ አዙር ጦርነት እና የውክልና መዋጫወቻ ሜዳውን እያሰፋው ነው። አሁን በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ እጥረት እየታየበት ያለ ንጥረ ነገር አለ። ብረት እና የብረት ማዕድን ።አፍሪካ ደግም የዚህ ማዕድን ሃብታም ነች ባይባልም ያላትን አልተጠቀመችበትም። አሜሪካ እና ቻይና እጅግ የሚወዛገቡበት ጉዳይ ደግሞ የብረት ፖለቲካ ነው። በዚህ የሃያላኑ… Continue reading ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች የቁርጥ ቀን ልጆቿን ትሻለች!! (በስለአባት ማናዬ )

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎችና ክሶች (ሺፈራዉ አበበ)

ሺፈራዉ አበበ ሚያዚያ 14, 2013 ዓ.ም. አገራችን የምትገኝበት የሰላምና የደህንነት ሁኔታ አሳዛኝና አሳሳቢ ነዉ። ለዚህ መንስኤ በሆኑ ኃይሎች ላይ ይደረግ የነበረዉ ዉግዘት ዉጤት ባለማስገኘቱ፣ በአሁኑ ጊዜ ወቀሳዉ፣ ክሱና፣ ዉግዘቱ፣ ለተፈጠረዉ ችግር በቂ መልስ ሊሰጥ ባልቻለዉ ጠ/ሚ እና በሚመራዉ የፌዴራል መንግስት ላይ የሚያነጣጥር ሆኗል። በአንድ መሪ ላይ ክስም ሆነ ወቀሳ መሰንዘሩ፣ እንኳን በቀውስ ወቅት በአዘቦቱም አይቀሬ ነዉ። ከወቀሳም ሆነ ከክስ በላይ የሆነ መሪ ኖሮ አያዉቅም፣ ለወደፊትም አይኖርም። ጠ/ሚ አብይ ይህን እውነት ምን ያህል እንደሚረዳው አላዉቅም፣ ለወቀሳና… Continue reading ጠ/ሚ አብይ አህመድ ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎችና ክሶች (ሺፈራዉ አበበ)

በማያስፈልግ ውሸት፤ ብሔራዊ ቅሌት! ( ከጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ)

 ከጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ ሚያዚያ 8 ቀን 2013 “ሐሰትና ስንቅ፤ እያደረ ያልቅ” ሃገራዊ ብሂል። በርካታ ጥናቶች እንደሚያስረዱት፤ በተለያዩ ሃገራት ያሉ መንግሥታት፤ ሕዝባቸውን በተደጋጋሚ ስለሚዋሹት፤ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት አጥቷል። በሃገራችንም፤ ከዚህ የተለየ አይደለም። በተለይ ከደርግ የአገዛዝ ዘመን ጀምሮ፤ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት ከማጣቱ የተነሳ፤ ሕዝቡን በተለያዩ መንግስታዊ እቅዶች (ፕሮጀክቶች) ላይ ለማሳተፍ የተደረጉ ጥረቶች ከሽፈዋል። በዘመን ሕወሃትም፤… Continue reading በማያስፈልግ ውሸት፤ ብሔራዊ ቅሌት! ( ከጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ)

እንንቃ!!! (በህይወት አበበ መኳንንት)

በህይወት አበበ መኳንንት ለማንኛዉም ችግር መፍትሔ ለማግኘት በመጀመሪያ ችግሩን ማወቅ እና እዉቅና መስጠት ያስፈልጋል። ሀገራችን የገባችበት ማጥ ቀላል አይደለም። የወደፊቱም እስካሁን ከሆነው የበለጠ አስጊ ነዉ። ህዝቦቿ ተጨንቀዋል አብዛኛዉም ግራ ተጋብቷል።ትላንት በሩቅ እንሰማ የነበረዉ መጥፎ ዜና ባንድም በሌላ በራችንን አንኳክቶ እየመጣ ነዉ። ታድያ ለዚህ ሁሉ ለደረሰ መከራ እና ስቃይ ሀላፊነት የሚወስደዉ ማነዉ? ለምንስ ዓላማ ነዉ? ብለን… Continue reading እንንቃ!!! (በህይወት አበበ መኳንንት)

የአገር ወዳድነት ስሜት በጠፋበትና ክህደት በበዛበት አገር ጠንካራ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ መገንባት አይቻልም፣ ክፍል ሁለት!

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)መጋቢት 22፣ 2021 መግቢያ ይህንን አርዕስት አስመልክቶ በመጀመሪያው ጽሁፌ ወደ መደምደሚያው ገደማ በተለይም በዕድሜ የገፉ ኢትዮጵያውያኖችን ሚና በሚመለከት አንዳንድ ነገሮችን ብዬ ነበር። አንዳንዶች እንደዚህ ዐይነቱን አጻጻፍ ከተስፋ መቁረጥና ከሃሳብ ተሟጦ ማለቅ ጋር ለማያያዝ ሞክረዋል። ይህ ዐይነቱ አተቻቸት ትክክል መስሎ ቢታይም ጸሀፊው ማንንም ተስፋ ለማስቆረጥ ብሎ አይጽፍም፤  ጽፎም አያውቅም። ከዚህም ባሻገር ጸሀፊው ከ20 ዓመታት በላይ… Continue reading የአገር ወዳድነት ስሜት በጠፋበትና ክህደት በበዛበት አገር ጠንካራ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ መገንባት አይቻልም፣ ክፍል ሁለት!

የወቅቱ የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን የፖቲካ መስተጋብሮች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት አንጻር

ዳምጠው ተሰማየካቲት 11 , 2013 ዓ. ም. የወቅቱን ሁለቱን ህዝቦች ልሂቃን ፖለቲካዊ መስተጋብር ቀደም ካለው ታሪካዊ ዳራ ብጅር የተሻለ ይመስለኛል፡፡ በአማራን እና በኦሮሞ ማህበረሰብ መሃል የማይታረቅ የፖለቲካ ጸብ እንዲኖር የመፈለጉ እንቅስቃሴ ጣሊያን አድዋ ላይ በኢትዮጵያዊያን ህብረት ድል በተመታች ማግስት እንደዋነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ተደርጎ እንደተዋሰደ እረዳለሁ፡፡የአድዋ ታሪካዊ ድል ጣሊያንን ያንበረከክንበት ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ለመላው የአውሮፓ ቅኝ… Continue reading የወቅቱ የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን የፖቲካ መስተጋብሮች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት አንጻር