የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም እንደቀደሙት አባቶቻቸው ቆፍጣና ስራ ሰሩ

መስከረም 17 2209 ዓ ም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ለዓመታት በገዥው ቡድን ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር እንደወደቀ ፤ መንፈሳዊ ግልጋሎት ከመስጠት በላቀ ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ቅጥ ባጣ አኳኋን እያገለገለ እንዳለ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው። ከዚያው ጋር ተያይዞ የሲኖዶሱ አባላት በአመዛኙ ወይ በፍርሃት ወይ በፖለቲካ የጥቅም ትስስር ተተብትው በኢትዮጵያውያን ላይ ተደጋጋሚ ግፉ ሲደርስ ድምጻቸውን […]

በጎንደር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ቃጠሎ ሊያደርሱ ነበር የተባሉ ሰዎች ተያዙ

ኢሳት መስከረም 12 2009 ዓ ም ላለፉት 4 ቀናት የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ በምትገኘው ጎንደር ከተማ ትናንትና ዛሬ የገበያ ቦታዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችን እንዲሁም መስሪያ ቤቶችን ሊያቃጥሉ ነበር የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ግለሰቦቹ በህወሃት የተላኩ መሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ከትግራይ ክልል እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት የይለፍ ወረቀት እንዳላቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል። የአንዲት ሴትና የአንድ ወንድ ወጣት […]

በጎንደር ከተማ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጎልታ ትታይ የነበረች ወጣት በህወሓት መንግስት ታጣቂዎች ታፈነች

መስከረም 9 2009 ዓ ም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአማራ ተጋድሎ ጋር የተያያዙ ዜናዎችን በመዘገብ የሚታወቀው ሙሉቀን ተስፋው እንደዘገበው በጎንደር ከተማ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጎልታ ትታይ የነበረች ወጣት በህወሓት መንግስት ታፍና ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደተወሰደች ዘግቧል። ስሟ ንግስት ይርጋ እንደሚባል የጠቆመው የሙሉቀን ዘገባ ፤ እድሜዋ ገና በሃያዎቹ መጀመሪያ ሲሆን የወያኔ መንግስት ታጣቂዎች ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ […]

ነጋዴዎች ለቅዳሜ ገበያ ቃጠሎና ንብረት ውድመት ተጠያቂው መንግስት ነው ይላሉ ( ቪኦኤ)

በጎንደር ከተማ በቅዳሜ ገበያ ላይ ለደረሰው ቃጠሎ ንብረት ውድመት ተጠያቂው መንግሥት ነው ሲሉ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ተናገሩ። የክልሉ መንግስት እሳቱ የጠፋው ሕዝብና መንግስት ባደረገው ርብርብ ነው ብሏል።

መስከረም 6 2009 ዓ ም የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ዋሽንግተን ዲሲ — ጎንደር ከተማ ውስጥ በመገበያያ ቦታነት ረጅም ጊዜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለትና በተለምዶ “ቅዳሜ ገበያ” ተብሎ የሚጠራው የገበያ ቦታ ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ ወደ 420 ሱቆች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተገለጸ። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎች ሆን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸው እሳቱን […]

20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ

መስከረም 2 2009 ዓ ም ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቦሌ አየር መንገድ ሕገ ወጥ የእጽ ዝውውር ላይ አንድ ሻለቃ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሃያ የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ክደው ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ ያለው መቆሚያ ያጣ ፍጅት ነው ተብሏል፡፡ በፌደራል […]

ዘማሪት እማዋይ ብርሃኑ የህወሓት የግፍ ግድያ ሰለባ

ጳጉሜ 5 2008 ዓ ም ህወሓት በአማራ ላይ ያለው ጥላቻ እስከምን ድረስ እንደሆነ ከተገለጠባቸው ሁኔታች አንዱ የሐምሌ ወር መጀመሪያ ጅምሮ በአማራ ክልል ሰላማዊ ተቃውሞ ላይ የወያኔ ሰራዊት ሰራዊት የወሰደው የግፍ ርምጃ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ጎንደር ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ሰልፍ ከምንም ነገር በላይ ሰላማዊ እንደነበር ዓለም ዓቀፍ የዜና ተቋማት ሳይቀሩ በስፋት የዘገቡበት ጉዳይ ነው። ህዝቡ ያለውን […]

ኢትዮጵያ ገባ ስለተባለው “የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር የጦር መሪ” ቶውት ፖል ቾይ ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ

ጳጉሜ 1 2008 ዓ ም ቪዲዮ ምንጭ ኢቢሲ “የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር የጦር ክንፍ ዋና አዛዠ ቶውት ፖል ቾይ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመቀበል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመስራት ተስማማ” በሚል ዛሬ የህወሃት መንግስት ዛሬ በቴሌቭዥን እንዳሰራጨ ይታወቃል። ጉዳዮን ከበድ አድርጎ ለማቅረብም ቶውት ፖል ቾይ አስው ስለተባለው ሰራዊት ፤ ተደረገ ስለተባለው ድርድር እና ስለ ፖለቲካ ማንነቱ ቦርከና […]

ቅሊንጦ እስር ቤት ተቃጠለ ፤ ሃያ ያህል ሰዎች ከተኩስ ሩምታ ጋር በተያያዘ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተሰምቷል

ነሃሴ 28 ፤ 2008 ዓ ም ዛሬ ጧት ላይ ቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት እንደተቃጠ በሰዓቱ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ኢሳት ዘግቧል። ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት ወገኖች በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ሩምታ እንደነበረም ጨምረው ገልጸዋል። ከኢሳት ቪዲዮ እንደሚታየው መረጃ የሰጡት ሰዎች ከእስር ቤቱ በቅርብ ርቀት ነበሩ፤ ሆኖም በነበረው የተኩስ ሩምታ እና በአካባቢው በነበረ የፖሊስ ኃይል ምክንያት ወደ […]

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መንግስት በአማራ ነገድ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ አፋፍሟል

ነሃሴ 25 2008 ዓ ም የፖለቲካ ድጋፍ መሰረቱ ትግራይ ላይ የሆነው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መንግስት ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ በ”ፌደራል” መንግስት በኩል የማደናገሪያ ውሳኔ ካስሰነ በኋል በታላቁ የአማራ ነገድ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ አፋፍሞ ቀጥሏል። ከትላንትና ወዲያ የአማሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛ አገልግሎት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጂት (መኢአድ) እና የአይን ምስክሮችን ጠቅሶ በዚህ ሳምንት […]

በቡሬ ጎጃም እና በሰሜን ጎንደር ጠንካራ ህዝባዊ አመጽ ተቀስቅሷል

ነሃሴ 19 2008 ዓ . ም   በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የወራትን ዕድሜ ካስቆጠረው ህዝባዊ አመጽ ጋር የተያያዘ ጠንካራ ተቃውሞ በቡሬ ጎጃም እና በሰሜን ጎንደር የተለያዮ ከተሞች እንደተከሰቱ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ምንጭ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድረ ገጽ ከዘገቡት እና ከኢሳትም ዘገባ ለማወቅ ተችሏል። በቡሬ የተከሰተው አመጽ ከብአዴን ጋር ንክኪ ያላቸውን የንግድ ተቋማት ኢላማ በማድረግ ጥቃት እንዳደረሰም ለማወቅ […]