የኢፌዲሪ የብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የፌዴራል መንግስት የጸጥታ አካላት አሰማራ

የኢፌዲሪ የብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የፌዴራል መንግስት የጸጥታ አካላት አሰማራ

ቦርከና ኅዳር 23, 2011 ዓ.ም. የኢፌዲሪ የብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋሉትን የጸጥታ ችግሮች በመፍታት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ክልሎቹ የፌዴራል መንግስት የጸጥታ አካላት በህገ መንግስቱ መሰረት ጣልቃ ገብተው ችግሩን እንዲያረጋጉ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ምክር ቤቱ የጸጥታ አካላቱ በአካባቢው ተሰማርተው የህግ የበላይነት እንዲያስከብሩ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቤትና ንብረታቸው በመመለስና በማቋቋም ሰላም […]

በትግራይ ዘጠኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

በትግራይ ዘጠኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ቦርከና ኅዳር 16 ፤ 2011 ዓ. ም. ዛሬ በትግራይ ዘጠኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደተካሄደ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በአድዋ፣ አክሱም፣ ኮረም፣ አዲ ሽሁ፣ አላማጣ፣ መኾኒ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ዓብይ ዓዲ እና ራያ የተካሄዱት ሰልፎች የህግ የበላይነት እንዲከበር ፤ በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ብቻ እንዲዳኝ ፤ እና መሰል ጥያቄዎች ተስተጋብተዋል -እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ። […]

ብርቱካን ሚዴቅሳ ምርጫ ቦርድን ለማደራጀት ምክር ቤቱ እምነት ጣለባቸው

ብርቱካን ሚዴቅሳ ምርጫ ቦርድን ለማደራጀት ምክር ቤቱ እምነት ጣለባቸው

ቦርከና ኅዳር 14 2011 ዓ.ም. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው ስብሰባ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጩነት ያቀረቧቸውን ብርቱካን ሚዴቅሳን ሹመት አጽቋል። ሹመቱ በአብላጫ ድምጽ በአራት ተቃውሞ እና በሶስት ድምጽ ተአቅቦ ነው የጸደቀው። የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ተቃዋሚ ፓርቲ (በአሁኑ አጠራር ተፎካካሪ) መሪ የነበሩት ብርቱካን ሚዴቅሳ በፖለቲካ አመለካከታቸው ያለ አግባብ ታስረው ኢሰብዓዊ የሆነ […]

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሰባት ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ኢትዮጵያ ገብታለች

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሰባት ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ኢትዮጵያ ገብታለች

ቦርከና ጥቅምት 29 2011 ዓ ም ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሰባት ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ከሰዓታት በፊት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ ያመለክታል። በህግ ትምህርት ከአዲስ አባባ ዮኒቨርሲቲ ዲግሪዋን የወሰደችው ብርቱካን ሚዴቅሳ በፌደራል ፍርድ ቤት በዳኝነት ከማገልገሏም ባሻገር ፤ በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ በአመራር ደረጃ እንዳገለገለች ይታወቃል። የምርጫ 97ትን ተከትሎ የቅንጂት ለአንድነት መሪዎች በታሰሩበት […]

የህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ

የህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት መዓዛ አሸናፊን  የፌደራል ጠቅላይ ፍ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ

ቦርከና ጥቅምት 22 ፤ 2011 ዓ.ም. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በነበረው ውሎው መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟቸዋል። ከሶስት ቀናት የአውሮፖ የስራ ጉብኝት የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፓርላማው ለማጸደቅ ካቀረቧቸው በኋላ ነበር በሙሉ ድምጽ የተመረጡት። ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ተቋማት በህብረተሰቡ ውስጥ ያጡትን ተዓማኒነት መመለስ ተቀዳሚ ተግራባቸው እንደሚሆን ተናግረዋል። ከፋና […]

በአውሮፖ የስራ ጉብኝት ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳይ ፤ ከጀርመን እና ኦስትሪያ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል

በአውሮፖ የስራ ጉብኝት ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳይ ፤ ከጀርመን እና ኦስትሪያ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል

ቦርከና ጥቅምት 20 ፤ 2011 ዓ.ም. በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ትላንት በፈረንሳይ የአንድ ቀን ኦፊሲየላዊ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ፓሪስ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ደሞ የስራ ጉብኝታቸውን በጀርመን ቀጥለዋል። በፓሪስ ኤሊሴ ቤተ መንግስት ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙት ላይ በመምከር ስምምነት ላይ እንደደረሱ ታውቋል። በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኢምባሲ ይፋ […]

ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

ቦርከና ጥቅምት 14 ፤ 2011 ዓ.ም. በአፍሪካ ሕብረት የተባባሩት መንግስታት ተወካይ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ባደረጉት የጋራ ልዮ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል። ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ለምክር ቤቶቹ የመልቀቂያ ደብዳቤ አቅርበው ተቀባይነት ካገኘላቸው በኋላ ነበር ሳህለወርቅ ዘውዴ በፕሬዝዳንትነት […]

ሳህለወርቅ ዘውዴ በነገው እለት የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን እንደሚሾሙ ተሰማ

ሳህለወርቅ ዘውዴ በነገው እለት የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን እንደሚሾሙ ተሰማ

ቦርከና ጥቅምት 13 ፤ 2011 ዓ.ም. በነገው ዕለት የፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመን የመልቀቂያ ጥያቄ ለማጽደቅ የተጠራው የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ልዮ ስብሰባ (በዚህ ዓመት ሁለተኛው ልዮ ስብሰባ መሆኑ ነው) በሚለቁት ፕሬዝዳንት ምትክ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን ይሾማል ተብሎ እንደሚጠበቅ በአፍቃሬ ህወሓትነት የሚታወቀው የሆን አፌይርስ ዛሬ ዘግቧል። ዜናው እውነት ከሆነ ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ […]

በአላማጣ ከተማ ሰባት ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ

በአላማጣ ከተማ ሰባት ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ

ጥቅምት 12 ፤ 2011 ዓ.ም. በትላንትናዉ ዕለት በደቡብ ትግራይ አላማጣ ከተማ ከራያ ህዝብ ማንነት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት በጥቂቱ ሰባት ሰዎች በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸዉን በስፍራዉ የነበሩ የአይን እማኞች ለቦርከና ገልፀዋል፡፡ የራያ ህዝብን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በተጠራዉ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድምፃቸዉን ለማሰማት በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢዉ ነዋሪወች ረፋድ ላይ ወደ አደባባይ መዉጣታቸዉንና የትግራይ […]

መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ! (አገሬ አዲስ)

መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ!  (አገሬ አዲስ)

ጥቅምት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በይዘቱ መርዘኛ የሆነውን ፈሳሽ “ጠበል” ወይም “የወይን ጭማቂ” ቢሉት፣መርዝነቱን አይለቅም። ኮሶን በወርቅ ዋንጫ ውስጥ አሳምረው ቢያቀርቡትና ማር ነው ቢሉት ኮሶነቱን አይለውጥም፣ ያው ኮሶ ነው።በተመሳሳይም በማንኛውም አካል የሚደረግ ውጫዊ አቀራረብና ስያሜ ውስጣዊ ይዘትና ጸባዩን ወይም ማንተቱን አይቀይረውም።ፉንጊትን ቆንጂት ቢሏት፤ ያው ፉንጊት ነች።ስሟ ስለተለወጠ ቆንጆ አትሆንም። በዚህ እርእስ ይህንን ጽሁፍ ለማዘጋጀት የገፋፋኝ […]