ዛሬም በቀጠለው የወልድያ ግጭት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞቱ (ዶቬ)

ዛሬም በቀጠለው የወልድያ ግጭት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞቱ (ዶቬ)

ዶቬ ጥር 13 2010 ዓ ም በአማራ ክልል በወልድያ ከተማ ትላንት በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡ ዛሬም በቀጠለው ግጭት በርካቶች መጎዳታቸውን፣ ሆቴሎች እና ህንጻዎች መቃጠላቸውን ተናግረዋል፡፡ በወልድያ ግጭት የተቀሰቀሰው የጥምቀት በዓል በዋለ በማግስቱ የሚከበረውን የቃና ዘገሊላን በዓል በጭፈራ እያከበሩ የነበሩ ምዕመናን በጸጥታ ኃይሎች እንዳይጨፍሩ ከተከለከሉ […]

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦክስፋም ኖቪፕ ተሸላሚ ሆነ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦክስፋም ኖቪፕ ተሸላሚ ሆነ

ጥር 11 2010 ዓ ም (ዘ ሄግ) በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዘ ሄግ ከተማ ትናንት ምሽት በተካሄደው የ2018 የፔን እና የኦክስፋም ኖቪፕ – “ሃሳብን የመግለጽ መብት” አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን ያዘጋጁት ኦክስፋም ኖቪፕ እና ፔን ኢንተርናሽናል የተሰኙ አለማቀፍ ተቋማት ሲሆኑ ከእስክንድር ነጋ ጋር የአመቱ ተሸላሚ ሆና የተመረጠችው የቬኒዙዌላዋ ጋዜጠኛ ሚላግሮ ሶካሮም ልብ የሚነካ […]

የዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ ፤ እስከ ረቡዕ ባለው ጊዜ …

የዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ ፤ እስከ ረቡዕ ባለው ጊዜ …

ጥር 7 ፣ 2010 አፍቃሪ መንግስት የሆኑ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ የፌደራሉን ጠቅላይ አቃቢ ህግ ጠቅሰው እንደዘገቡት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ ተቃዋሚ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተቋርጧል። ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ በታወጀ ማግስት ለስራ ጉዳይ ከሄዱበት ከአውሮፖ ሲመለሱ ተይዘው ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በእስር ላይ እንደነበሩ ይታወቃል። በፌደራል ደረጃ የአንድ መቶ አስራ […]

ቴዲ አፍሮ በባህርዳር ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ፈቃድ አገኘ

ቴዲ አፍሮ በባህርዳር ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ፈቃድ አገኘ

ጥር 4 2010 ዓ ም ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በባህር ዳር ስታዲየም ሰማኒያሺህ ሰው በሚይዘው ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርቱን በጥር 12 ቀን ለማቅረብ ከክልሉ እና የከተማዋ መስተዳድር አካላት ፈቃድ አግኝቷል። የሙዚቃውን ድግስ “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ” በሚል ሰይሞታል። ትላንት በፌስ ቡክ ገጹ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል። “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ” የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር ቅዳሜ […]

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

ታህሳስ 21 ፤ 2010 የድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከታህሳስ 3 ቀን ጀምሮ ላለፉት 17 ቀናት አገራችን የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ሰፊና ዝርዝር የሁኔታዎች ግምገማ አካሂዷል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የመታደስ ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም በአገራችን የሚታዩ የቆዩና ወቅታዊ ችግሮችን ከነዝርዘር መገለጫቸው በመለየት በመንስኤና መፍትሄዎቻቸው […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጥብቅ የደህንነት ጥበቃ አድማ የመቱ የፖርላማ አባላትን አናግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጥብቅ የደህንነት ጥበቃ አድማ የመቱ የፖርላማ አባላትን አናግረዋል

ቦርከና ታህሳስ 17 ፤ 2010 ከቀናት በፊት በፌደራል ፖርላማ ያሉ የኦህዴድ እና የብአዴን የህዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በፖርላማ ቀርበው እየተከሰተ ስላለው የዘር ግጭት እና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ስላለው ቀውስ ካላናገሩን በመደበኛ የስራ ገበታችን ላይ አንገኝም በማለት አድማ መምታታቸው ይታወቃል። ይሄንኑ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰኞ ዕለት እየተካሄደ ያለውን የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በማቋረጥ […]

ከኦህዴድ የተወከሉ የፌደራል ፓርላማ አባላት “በአዲስ አበባ ልዮ ጥቅም” ላይ የተጠራውን ስብሰባ በተቃውሞ አስቆሙት

ከኦህዴድ የተወከሉ የፌደራል ፓርላማ አባላት “በአዲስ አበባ ልዮ ጥቅም” ላይ የተጠራውን ስብሰባ በተቃውሞ አስቆሙት

ታህሳስ 13 ፤ 2010 ዓ ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ አለው ስለሚባለው “ልዮ ጥቅም” ለመወሰን ዛሬ በፓርላማ በጠራው ስብሰባ ከተጀመረ በኋላ በኦህዴድ ተወካዮች ተቃውሞ እንደተሰረዘ ተሰማ። የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ኦሮሞዎች ከሱማሌ ክልል በተፈናቀሉበት ፤ ዜጎች በግጭት ምክንያት […]

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ታህሳስ 11 ፤ 2010 ዓ ም የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው አመት በድርጅታችን የተጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ አፈፃፀም በዝርዝር መገምገም ጀምሯል፡፡ በድርጅታችን ኢሕአዴግ የቆየ ባሕል መሰረት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂደው የትግል ሂደት የሚያጋጥሙትን ጉድለቶች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በጥልቀት ይገመግማል። ግምገማውን መሰረት በማድረግም ራሱን በራሱ ያርማል። እነሆም የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቀደም ሲል የስራ […]

ለማ መገርሳን ጨምሮ የኦፒዲዮ አመራሮች ላይ በህወሓት የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ እንደከሸፈ ተሰማ

ለማ መገርሳን ጨምሮ የኦፒዲዮ አመራሮች ላይ በህወሓት የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ እንደከሸፈ ተሰማ

ቦርከና ታህሳስ 10፤ 2010 ዓ ም የኦፒዲዮ አመራሮችን(ለማ መገርሳን እና አብይ አህመድን እንደሚያካትት ተገምቷል) በህወሓት የተቀነባበረ ነው የተባለ የግድያ ሙከራ እንደከሸፈ ተሰምቷል። እስካሁን ዜናውን ከሌሎች የዜና ተቋማት ማረጋገጥ ባይቻልም ተቀማጭነቱ በኔዘርላንድ የሆነ አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ ተጠርጣሪ ናቸው የተባሉትን ሁለት ግለሰቦች መታወቂያ በማያያዝ በማህበራዊ ድረ ገጽ ዘግቧል። ገረሱ “በኦሮሞ የመብት ተሟጋችነት” የሚታወቅ ሲሆን በሃገር ቤት በተለይም […]

የጠ/ሚ ኃይለማርያም ንግግር ያስከተለዉ ቁጣ

የጠ/ሚ ኃይለማርያም ንግግር ያስከተለዉ ቁጣ

ጀርመን ድምጽ ራዲዮ በመርጋ ዮናስ እና ሸዋዬ ለገሠ ታህሳስ 9 ፤ 2010 ዓ ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገሪቱ የፖለቲካ ይዞታዉ አሳሳቢ ሁኔታ ዉስጥ እንደሚገኝ በትላንትናዉ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል። በተለይም በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ህይወት እንደጠፋ፣ ሰዎች ከቀያቸዉ እንደተፈናቀሉ እና ንብረት እንደወደመም አሳዉቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም […]

1 7 8 9 10 11 13