ተፈጥሮ :”ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች” [ ተነከሰች]

እናት ጎሽ ልጇን ከአናብስት ለማዳን ብቻዋን አንበሶችን እየተዋጋች እያለች ፤ ጥጃዋ በአንደኛዋ አንበሳ ተነጥቃ ተወሰደች። እራሷንም ጭምር እየተከላከለች ተስፋ ሳትቆርጥ ጥጃዋን ለማዳን አናብስቱን ማሳደድ ጀመረች። ሸሽተው የነበሩ ጎሾች የእናትየውን ቁርጠኝነት ሲያዮ ተመልሰው ውጊያውን ተቀላቀሉ። እናት በስኬት ልጇን አዳነች። ትይንቱ የመሪነት ሚና እና ተስፋ ያለመቁረጥን ፋይዳም ፍንትው አድርጎ ያሳያል።