
ቦርከና ዜና
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር የፖሊስን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዙ አነፍናፊ ውሾችን (K9) ከእስራኤል ፖሊስ በድጋፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የሆኑት ም/ኮ ጀነራል መላኩ ፋንታ ድጋፉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት አነፍናፊ ውሾቹ በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት በኩል ከተለያዩ የውጪ ሀገራት ወደ አገሪቱ የሚገባውንና የሚወጣውን አደገኛ ዕፅ ለመከላከል እና ዝውውሩንም ባደገ ሁኔታ ለመቆጣጠር እንደሚያስችሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም በኬ ዘጠኝ በመታገዝ ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውንና የሚወጣውን አደገኛ ዕፅ በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፀረ-ፈንጂና የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር መምሪያ ባለሙያዎች በእስራኤል ሀገር ቴል አቪቭ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰው አነፍናፊ ውሾቹ ሰልጥነው ወደ አገሪቱ ሲገቡ ለ39ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልፀዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከእስራኤል ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ዕፅ ዝውውር በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
Ethiopian News–Borkena English
ኤክስ ፡ @zborkena






