Homeዜና"ለአሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ተልዕኮ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል" ...

“ለአሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ተልዕኮ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል” ላውረንስ ፍሪማን

Advertisement
World Wide Travel Group
ላውረንስ ፍሪማን

ጀማል ሰይድ
ቦርከና

ለአሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ተልዕኮ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አሜሪካዊው የአፍሪካ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን ገለጹ፡፡

አሜሪካዊው የአፍሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት ከኢትዮጵያ ጠላቶች ድጋፍ የሚደረግለት በመሆኑ በመንግስት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ በመግፋት ዳግም ጦርነት ከፍቷል።

ከፌደራል መንግስት የቀረበለት የሰላም አማራጭ ሂደት ላይ እያለ ወደ ዳግም ጦርነት መክፈቱ ቡድኑ የውጭ ድጋፍ እንዳለው የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡ በምርጫ ስልጣን ይዞ ሕዝብ እየመራ ያለውን የፌዴራል መንግስት ባለመቀበል፥ የጦርነት አዙሪት ውስጥ የገባው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ እኩይ ዓላማ ይዞ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም የአሸባሪውን ህወሓት ሀገር አፍራሽ እቅድ የሚደግፉ አካላት የግጭቱ አባባሽና የጥፋቱ ተባባሪ ከመሆን ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የአሸባሪውን አገር የማፍረስ እኩይ ተግባር አይቶ ዝም ከማለት ይልቅ ማውገዝ እንዳለበት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ድንበሯን ጥሶ በመግባት ለአሸባሪው ህወሓት የጦር መሳሪያ ሊያቀብል የነበረ አውሮፕላን መትታ መጣሏ ተገቢ መሆኑንም ነው ላውረንስ ፍሪማን ያስረዱት።

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

__

በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News