

የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት (Royal Ethiopian Trust)፣ የኢትዮጵያን ዘውድ ትዉፊትና ታሪክ ለማስቀጠል፣ የኢትዮጵያዊያንን ባህል ለማስታዋወቅና የኢትዮጵያንም ሕዝብ በትምህርትና በኤኮኖሚ ለማበልጸግ የተቋቋመ ትርፍ አልባ ድርጅት መሆኑን በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 1, 2024 ዓ.ም. (እአአ)፣ ልዑል ኤርሚያስ ሣኅለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ አስታወቁ።
ልዑል ኤርሚያስ ሣኅለ ሥላሴ፣ የግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ሲሆኑ፣ ከሶስት ሺ ዘመን በላይ ባለመቋረጥ የቆየውንና በመላው ዓለም ረጅሙን የስልጣን እድሜ ያለውን ንጉሣዊ ስርዓት ወኪልና የበላይ ጠባቂም ናቸው።
ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1974 ዓ.ም. (እአአ) የፈነዳው ኮምዩኒስታዊ አብዮት፣ የኢትዮጵያን ዘውዳዊ ስርዓት ከሥልጣን ከማስወገዱም ባሻገር፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ በግፍ እንዲገደሉና ልዑል ኤርሚያስ ከነቤተሰቦቻቸው ለስደት ኑሮ እንዲገደዱ አድርጓል። ልዑል ኤርሚያስ ትምህርታቸውን አሜሪካ በሚገኙት University of California at Santa Barbara እንዲሁም በFletcher School of Law & Diplomacy አገባድደዋል። እአአ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤትን በፕረዝደንትነት ሲመሩ ቆይተዋል።
“የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላ በመቋቋሙ እጅግ ደስ ብሎኛል። ይህ ድርጅት እንዲቋቋም ከጎኔ ሳይለዩ ለደገፉኝና ለተባበሩኝ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ” ብለዋል ልዑል ኤርሚያስ። የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ከወደፊቱ ጉዞዋ ጋር ለማቆራኘት፣ የኢትዮጵያን ዘውዳዊ ዉርስና ቅርስ ለመጠበቅና ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ ወደፊት እንድትራመድ በመላው ዓለም ከሚገኙ ደጋፊ ግለሰብና አጋር ድርጅቶች ጋር ለመስራት እንሻለን” ብለዋል ልዑልነታቸው።
ልዑል ኤርሚያስ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት በቦርድ አባላትነትና በአማካሪነት እንዲያገለግሉ የሾሙአቸውን ግለሰቦች አመስግነዋል። በንግድ ስራና በጎ አድራጎት ላይ ለብዙ ዓመታት በመሰማራት የስራ ልምምድ ያካበቱና ከንጉሣዊ ቤተሰብ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጋር ቅርበትና ትስስር ያላቸውን ግለ ሰቦች ልዑልነታቸው እንደሾሙ ተናግረዋል። የቦርዱ አባላት፣ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ያቀዳቸውን ግቦች ለማሳካት እገዛ እንደሚያደርግም ልዑል ኤርሚያስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ዋናና መሰረታዊ አላማዎች አሉት። በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ ታሪክና ባህላዊ ቅርሶች በክብር እንዲጠበቁ ማድረግ ሲሆን፣ በዋናነት ትኩረት የሚያደርግባቸው የስራ መስክና ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው
1. ትምህርት
2. የስራ ልምምድና ንግድ
3. የኢትዮጵያን ዘውድ ቅርስና ውርስ ማስጠበቅ
4. ለኢትዮጵያ ዘውድ ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ
“በእነዚህ አራት የስራ ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ለሃገራችን ብልጽግና፤ ለባህላችን ክብርና ለኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊና ቋሚ መሆኑን ያሳያል” ብለው ዲያቆን ሰለሞን ክብርዬ፣ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ገልጸዋል ። በማስቀጠልም፣ ‘ለሃገራችን ዘለቄታነት ያለው አስተዋጽኦ ለማበርከት” እንደሚፈልጉ፣ ዲያቆን ሰለሞን አስረግጠው ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም፣ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት፣ IGO Cares ከተባለው ድርጅት ጋር በመተባበር፣ ህፃናት ተማሪዎችን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የገንዘብ ዕርዳታ ሲያደርግ ቆይቷል። በተጨማሪም፣ Project Ethiopia ከሚባል ሌላ ድርጅት ጋር በመተባበር በአነስተኛ ወለድ የማይክሮ-ፋይናንስ ብድር ለገበሬዎችና ገጠር አካባቢ ለሚገኙ ሴቶች ለግሷል።
ስለ ኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት
የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት፣ የኢትዮጵያን ዘውድ ትዉፊትና ታሪክ ለማስቀጠል፣ የኢትዮጵያዊያንን ባህል ለማስታዋወቅና የኢትዮጵያንም ሕዝብ በትምህርትና በኤኮኖሚ ለማበልጸግ በልዑል ኤርሚያስ ሣኅለ ሥላሴ የተቋቋመ ትርፍ አልባ ድርጅት ነው።
የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት፣ አራት ዋናና መሰረታዊ አላማዎች ወይም የስራ መስኮች አሉት። በዋናነት የኢትዮጵያን ታሪክና ባህላዊ ቅርሶች በክብር እንዲጠበቁ ለማድረግ ሲሆን፣ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ወጣቶች የተሻለ ዕድል እንዲኖራቸው በትምህርት ማበልጸግ፣ በልዩ ልዩ የንግድና የፈጠራ ስራ ላይ ሕዝባችን ተሳታፊ እንዲሆን በሮችን በመክፈት ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም የአትዮጵያ ዘውድ የአንድነታችን ምልክትና አርማ ሆኖ እንዲቀጥል ባህላችንን፣ ውርስና ቅርሶቻችንን በክብር ለማቆየትና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እንድንችል በሁለንትናዊ መልኩ ለኢትዮጵያ ዘውድ ድጋፍ ማድረግ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ቀዳሚ አላማዎች ናቸው።
ሕዝብ ግንኙነት
ልጅ ነብያት አክሊሉ
(330) 310-6749
ndemessie@gmail.com
__
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com
Ethiopian News – Borkena English
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ







Why is the “የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት” silent about the ongoing displacement, killings, and crime against humanity on the Amhara people? Whose side are you on, Prince? What keeps you quiet from speaking against Amhara genocide?